ጸጋዬ ገ/መድህን (ሎሬት) ምነው አምቦ… የደማም አምባዎች ቁንጮ ፤ እንዳልነበርሽ የደም ገንቦ እንዳልነበርሽ ንጥረ-ዘቦ ዙሪያሽ በምንጭሽ ታጅቦ በተራሮችሽ ተከብቦ ከጠበልሽ ሢሳይ ታልቦ...
ዳዊት (የምዕራፍ አባት) ና.. ወዲህ ብቅ በል… ጠራሁህ ፈርዖንለሳቱት ልጆችህ ልቦና ብትሆን…ለአፍታ አፍ አውጥተህ… ምሥክር ብትሆንጠራሁህ ፈርዖንዲኦዶሮስ ሲኩለስ ምን ብሎ ከተበ? ለእኚህ...
በራሳችን ምድር፣ በራሳችን አፈር፣ በራሳችን እርሻ፣ በራሳችን ሞፈር፣ …ግን በሌሎች ቀምበር… በራሳችን አሐዝ፣ በራሳችን ፊደል፣ በራሳችን እውነት፣ የራሳችን በደል፣ ለራስ መንገር ሲሳን፣...
ይሄ ያገሬሰው እኮ፣ መሰላል አወጣጥ ያውቃል አንዱን እርከን ረግጦ ሲያልፍ፣ ነቅሎ ጉያው ይከታል ደሞ ቀጣዩን ይረግጣል… ነቅሎ ጉያው ይከታል… እንዲህ እንዲያ እያለ...
ለባዶ ቢሆንስ? ፀሎቴን ማብዛቴ በእምነት መበርታቴ ወደ ላይ ዕያየሁ – በታላቅ ልመና – እንባዬን መርጨቴ ለተረት ቢሆንስ? በሚነግሩኝ ገድል – ከንፈሬን ‘ምመጠው...
አያርግብኝና ገነትን ብወርሰው በምድር ገሀነም ስጨስ የኖርኩ ሰው ያንን ሁሉ ምቾት እንዴት ነው ምለምደው?
ያ ዶሮዬ ጮኸ መንጋቱን ነገረኝ በዛሬው ቀን ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ
የወጋኝን በሬ፣ ገዛሁት ለማረድ ከመውደቅ አይከፋም፣ የመሞት መዋረድ
ምን ይገርማል ይሄ በኔና‘ቺማ ‘ድሜ ምን ያስደፋል አንገት ምን ሆነሻል እቱ በኔናንቺ‘ኮ እድሜ… መሳ ለመሳ ነው እምነቱ ከእብለቱ በኔናንቺ‘ኮ እድሜ… አድናቂው ብዙ...
እሰጠው የነበር በቀን አስር ሳንቲም ያ ነዳይ ዐረፈ፤ በመስጠት የያዝኩት የመጽደቅ ተስፋዬም አብሮት ረገፈ።
ሙያዬን ታውቃለህ፤ ማጀቴን ታያለህ፤ “እንጀራሽ እንክርዳድ፤ ገበታሽ ጣዕም-አልባ!” ለምን ትለኛለህ? በል ዝም-ብለህ ብላ!! ቸርቻሪ መንግሥታት፤ ሰነፍ ገበሬዎች፤ በዝባዥ ነጋዴዎች፤ በበዙበት ዓለም፤ ጠንካራ...
የሚፈነጥቀው – የገደል ዳር ጢሱ ሳቅ ነው ስል ከርሜ ለቅሶ ነበር ለሱ በዘመናት ብሶት ስሜቱ ሲነካ እምባ እያፈሰሰ ወንዝ ያለቅሳል ለካ ዶፍ...
የክርስቲያን አምላክ እንሆ ማተብ ክር ምንም አላጠፋሁ … ልሳሳት አልሞክር … እንኳን ጥርኝ አፈር … ነውርም ይዠ አልነጎድኩ … ...
ላለመስማማት ተዋደን ላለመዋደድ ተስማምተን ላለመኗኗር ተቧድነን ላለመፋቀር ተቃቅፈን ላለመጋባት ተጫጭተን ይሄው ዙረን ዙረን… እዚያው ነን! አጀብ ዘመናችንን ቸብችበን በኪሳራችን ቶጅረን የመጠላለፍ ጽዋችንን፤...
ከዓድዋ ጦር ማግስት በቆሰለ አርበኛ የተማረከ ሰው እልፍኝ ውስጥ ሆኖ እንደዚህ ጠየቀ “ሲወጋ፣ ሲያዋጋ፣ ሲያጠቃን የነበር ነጩ ፈረስ የታል?” ይኔ… ነጭ ወራሪ...
ምነው ሰላሌ ያልለመደብህን፣ ያላደግክበትን ማደግደግ ከሳጥናዔል ጫማ ስር ወድቀህ፣ እታች ወርደህ ማሸርገድ ታዳጊ ወጣት አሳርደህ፣ አዝነህ ተቀምጠህ መንደድ ከየት መጣብህ? ከየት ለመድከው?...
ትናንትና እና እኛ ለካስ ትናንትም ይሻክራል!… አሽክላ እንደበላው ማድጋ አፈር እንደላሰው ምሳር ለካስ የድሮ ድሮ ይጓጉጣል!… ሲሶው ቢጥም፤ ቀሪው ያማል፡፡ ጨው እንደበላው...
ቢሄዱት… ቢሄዱት… ቢሄዱት… ቢሄዱት… አያልቅ ሽቅቦሹ፥ አይቆም ቆልቁሎሹ መንገድ እየሄዱ መንገድ እየበሉ መንገዱ እየጠጡ አያልቅም ቢሄዱት፥ አያልቅም ቢጠግቡት፤ አወይ አማሪካን… አወይ የሰው...
“ጨፍግጓል ዛሬ ጨልሟል ቀኑ ብርሃን ጠፍቷል፤ ከፍቷል ዘመኑ…” እያለ አንዱ እያማረረ፤ ቀንን ከዘመን እያሳበረ፣ ሲነጉድ አየኹት አንገቱን ደፍቶ፤ ባየው በሰማው እጅግ ተከፍቶ፡፡...
አደራውን ክዶ ብዕር ከሸፈተ፣ የሀቅ ነቁጡን ስቶ ዘሩን ከጎተተ፣ ከዓላማው ተጣልቶ ሚዛኑን ካደፋ፣ ስልጣኑን ሊያመቻች ቀለሙን ከደፋ፤ ዘረኛ ሊዋጋ ዘረኛ ከሆነ፤ ሚዛኑ...
…እንዲህ ቁጭ ብዬ ትላንትን ሳስብ መለስ ብዬ ትዝታሽ ውስጤን አመሰ፤ ጠረንሽ ሁለንተናዬን ዳሰሰ:: …አዝመራሽ አይነቱ፣ የጤፋ ማሳ፤ የስንዴ በቆሎ ’ሸቱ፣ የጋራ ፊፉ...
አላልኩም ነበረ!! ያቺ ፀሐይ ግባት ፀሐይ መውጫ ተብላ ሳትጠልቅ የጠለቀች በግድ ተገልላ የገባቸው ፀሐይ ግድ የተሸፈነች ፀሐይ መውጫ ተብላ ዳግም ትወጣለች አላልኩህም...