ታዛ ወግ

ኮቪድ -19 ኮሮና ቫይረስን የቆሎ ጓደኛችን አደረግነው እንዴ

እንድርያስ ተረፈ

የመጀመሪያው የኮረና ቫየረስ ተጠቂ ከባህር ማዶ ወደ ኢትዮጵያ ገባ-ተቀላቀለ ከተባለ እንኳ መጋቢት አንድ ዓመት አለፈ፡፡

አቤት!በዚያን ጊዜ የነበረው ድንጋጤ ወከባ ግርግሩ እናሸብሩ የዛሬ አያድረገውና ልበል እንዴ! ትዝ የላችኋል አንደ የሳኒታየዘር መያዣ መርጫ ቢልቃጥ 100-120 ብር ፣አንድ ጭምብል 250 ብር ሲቸበቸብ?

ዛሬ መርጫውም ጭንብሉም አስር አስር ብር እየተባለ በአደባባይ ሊጮኽባቸው! አልኮልና ሳኒታይዘር ፈሳሾች ግን ከቀድሞ ዋጋቸው እምብዛም ፍንክች እንዳላሉ ኮቪድን እንደመሰሉ አሉ፡፡ በነገራችን ላይ በኛም አገር የወጣ ዋጋ ሲወርድ በሳኒታየዘር -አልኮሆል መያዣ ቢለቃጥ እና በጭምብል ላየ ነው በፈጣን ሁኔታ ያየሁት፡፡ እናነተስ? ቫየረሱን ፈርቶ የሆን እንዴ?

ገና የኮቪድ ወሬ የተሰማ ዕለት እና ሰሞን የከተማችን ደጆች እና አደባባዮች በውሃና በሳሙና ተጥለቅልቀው እዚህም እዚያም ታጠቡ ነው፣ መታጠብ! መታጠብ! መታጠብ! ሆነእጅንም ኪስንመ በኮረና ቫየረስ ስም፡፡ ‹‹ በመኪና የሚያልፍ ጓደኛውን ሁለት እጁን አውለብልቦ በርቀት ሰላም ያለ ሁሉ በጭንቀት ከመንዘፍዘፍ የተነሳ ከኪሱ ሳኒታየዘር መዥረጥ አድርጎ እጁ ላየ አነዠቅዥቆ የጠራርግ ነበር ›› ብላችሁ እየሳቃችሁም ቢሆን አንተ አጋናኝ ተሉኝ የሆናል፡፡ እንዳሻችሁ፡፡ ከጥንቃቄ ይልቅ ፍርሀት የሚያንቀጠቅጠው ሰው ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ በያላችሁበት በየቤታችሁ እዩት ፡፡ አንዳንዱ ሁለት ማስክ እያደረገ በመዋሉ ሳየሆን አይቀርም የማስክ እጥረት የተፈጠረው የሚሏችሁ ሃሳብ አታጣጥሉ፡፡ ‹‹ የፈሪ በትር አስር ነው›› ይላሉ አበው፤ ኧረ አንዱንመ በአግባቡ በንፅህና በተጠቀመንበት ነው የሚባለው፡፡

የማስክ(ጭምብል)ን አጠቃቀመ ታዝባችሁልኛል ግን? እንደመነፅር (ጭንቅላት ላይ) እንደሚደረገው አገጭ ላይ ዝቅ ብሎ ከአፍና አፍንጫ ርቆ የሚደረገውን አይነት አፍን ብቻ ሸፍኖ አፍንጫን የሚረሳውን አይነት ኧረ! ምኑ ቅጡ፡፡

የመቆሸሹ ለዓይን ማስጠላቱንስ… በየሜዳው ተጥሎ መዝረክረኩ ከተማውን የቅራቅንቦ መጣያ ማስመሰሉ ሁሉ ሲታሰብ ኮቪድን ተላመድነው የቆሎ ጓደኛ ማድረጋችንን ያሳብቅብናል፡፡

የዛሬ ዓመትና ከዚያም በኋላ በነበሩት ወራት ይህን ያህል ሰው ተያዘ -አገገመ-ሞተ የሚሉ ወሬዎች እንደ ቆቅ ነቅተን ጆሮአችንን ኮርኩረን ነበር የመኘሰማቸው፡፡ በየመንገዱ ፌደራሎች ማስክ ያላደረገ ሳኒታየዘር ያልያዘ ይይዛሉ፣ ይቆጣጠራሉ ሲባል ያኔ ሞባይል ቢረሳ ወደ ቤት የማይመለሰው ሰው ሁሉ ለጭምብልና ሳኒታይዘር ሲሆን አቅሉን እስኪስት ሲሮጥ ይታይ ነበር፡፡ ዛሬስ ምን ተገኘ የታማሚውም የሟቹም ቁጥር እንደኑሮ ውደነቱ እያሻቀበ ሲሄድ ጨራሽ ካለ ጭምብል ከሰው እየተቀላቀሉ ሲበክሉ እና ሲበከሉ መዋልን ምን አመጣው ጎበዝ! መብቴ ነው… አይነት መዘናጋት ዛሬም ብዙዎችን እያሳጣን ነው፡፡ ጤና ሚኒስተር ለፌደራል ፖሊስ እና ለመከላከያ የሰጥ እንዴ!? ቂ…ቂ…ቂ… ምናባቴ ላድርግ ‹‹ የቸገረው ዱቄት ከንፋስ ይጠጋል›› ሆነብኝ እኮ ነው ዘመዶቼ፡፡ ኧረ መዘናጋት በሽበሽ ሆኖአል ልብ እንግዛ!

በታክሲ ፣ በአውቶቡሱ የበሽታውን ስርጭት በሚመጥን ቁመና ጥንቃቄ እየተደረገ ላለመሆኑ የሆነ ድርጅት ጥናት ጠቅሼ መሞገት አያሻኝም ፡፡ በቀን ውሎ አመሽቶዬ እስኪታክትኝ የማየው የምሰማው ግድየለሽነት ድንብሽ እያደረገን ነው፡፡ እያወቅን እያለቅን ነው፡፡ የሕክምና ቦታም መሣሪያም በበቂው ሁኔታ የሌላት አገር ይዘን፤ የእርስበርስ ገጭታችን ዘለግ ብሎ መክረሙ ፣ በረሃብ መጎዳታችን ፣ ስራ አጥነት መንሰራፋቱ ፣ ሴተኛ አዳሪነት መበራከቱ እና ሌላው ሌለው መዓት ችግር ተደመሮ የቁም ሞቱን ስንለምደው ዋናውን ሞት ናቅ አድርጎ ይሆን ? ብላችሁ ብታስቡ አልፈርድባችሁም፡፡ ግን ደሞ ኮቪድ -19 ኮረና ቫይረስ ካለ ርሕራሄ እያቸደን ነው እና ኖረን ለማኖር ፣አገርን ለማቆየት እንጠንቀቅ፡፡ ምትክ የሌላትን ህይወት ካለ አላማ አለኮስኩሶ ማጥፋት በፍፁም ጀግንነት ሊሆን አየችልና ካለጥንቃቄ አንዋል-አንደር፡፡ ልክ እንደዛሬ አመቱ ሬድዮ ቴሌቪዥንኑ ሁሉ

‹‹ በአባቶቻችን ወግ እጄን ሳትነኪ ሰላምታዬን እንኪ
በአባቶቻችን ወግ እጄን ሳትነካ ሰላምታዬን እንካ
ሿ…ሿ…ሿ… ፍትግ ›› ን ደጋግመን ብንሰማ ምን ይለናል?
በጤና ክረሙልኝ!
ከ’ራስህ ተዋወቅ
በእንድርያስ ተረፈ
ከፈጣሪ ልቀህ ላይሆንልህ ነገር
ሰው ሆይ ! እረ ተመከር ተዘከር
ልብ ግዛ ጎበዝ !አስተውል ላፈታ
ሳትዘነጋ በቅጡ ተማር
ሌላውን ለማወቅ-ለመተዋወቅ
ዘወትር አትቸኩል አትጣደፍ
ውስጥህን ሚግት አድምጠው
‘ራስህን ማወቅ ነው ‘ምያሳርፍ፡፡
ማማር፣ መድመቅ፣ ዘውድ መጫን ማለት
ከ’ራስ ውስጥ ፈልፍሎ ‘ራስን አግኝቶ
በራስ ያጌጡ ዕለት ፡፡
ያኔ ዕውነት’ና ዕውቀት ጥበብ ከማስተዋል
እንደመለካም ሽቱ ከ’ራስ እያለፈ
ለሌላው ይተርፋል፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top