በላ ልበልሃ

ወረርሽኝ፡ ታሪካዊ እና ሳይንሳዊ ይዘት

መግቢያ

በዘመናችን የደረሰውን አስጊ ወረርሽኝ መንስዔ በማድረግ፣ “ወረርሽኝ” በሚል ርዕስ በዚህ ዓመት (በ2013 ዓም) አንድ መጽሐፍ ለንባብ አቅርቢያለሁ፡፡ አሁን የማቀርበውም ይኸንኑ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ “ወረርሽኝ” በሰው ልጅ ላይ ምን ለማድረስ እንደሚችል፣ ብሎም በዚሁ ሳቢያ “ወረርሽኝን”፣ በተለይ የ”ኮቪድ-19” ወረርሽኝን እንደምሳሌነት ወስዶ፣ «ሳይንሳዊ አስተሳሰብ»ን ለማኸዘብ ነው («ሳይንሳዊ አስተሳሰብ» ማለት በሳይንሳዊ አስተሳሰብ ዘዴዎች መጠቀምን እንጅ፣ የዕውቀት ዘርፍን አያመላክትም)፡፡

ወረርሽኞች የሚከሰቱ በበሽታ አምጭ ተዋስያን(አቸንፋሪ/pathogens) ለከፋ ነው፡፡ በዓለማችን በተካሄዱ ጦርነቶች ከሞቱት ግለሰቦች ቁጥር በጣም በላቀ መጠን፣ በወረርሽኝ ያለቀው ያመዝናል። ስለሆነም ከፖለቲካ አይዲዮሎጂ በማይተናነስ መጠን፣ ወረርሽኝ የዓለምን ታሪክ አቅጣጫ ቀይሷል ማለት ከእውነት የራቀ አይሆንም። በጥይት፣በቦምብ፣ በታንክ፣ በመድፍ፣ ከተጠቃው፣ በቅማል እና በቁንጫ የተጠቃው ይልቃል ሊባልም ይቻላል። እንዲሁም ከውጭ የመጣ ጠላት፣ አካባቢን ተጋርቶ የሚኖር፣ ጎረቤት (ቁንጫ፣ ቅማል፣ አይጥ) ያይላል ቢባልም ከእውነት የራቀ አይደለም።

ሳይንስን ለማኸዘብ በሚሞከርበት ጊዜ አንዱ ዋና ተግዳሮት ለሳይንሳዊ ትንተና የሚያገለግል የአማርኛ ቋንቋ ውስንነት ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን በአማርኛ ቋንቋ የሳይንስ ማኸዘብ ጥረት መቀጠል አለበት የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ በዚህች ጽሑፍ ዝግጅት ለሳይንስ ቃላት ትርጉም የተጠቀምኩት፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ በ1989 ዓ.ም. ባሳተመው «የሳይንስና ቴክኖሎጅ መዝገበ ቃላት (እንግሊዝኛአማርኛነው፡፡ ለአንዳንድ መዝገበ ቃላት ውስጥ ላልተካተቱ ቃላትም የአማርኛ ትርጉም ሰጥቻለሁ፡፡ ያም ሆኖ ግን ለቃላት ትርጉም መስጠቱ ቀላል አልነበረም፡፡ ለምሳሌ ወረርሽኝን በምሳሌነት ወስደን ችግሩን ለመረዳት እንሞክር፡፡

የ”ወረርሽኝ” ተመጣጣኝ እንግሊዝኛ ቃል፣ “ኤፒዴሚክ” (Epidemic) ወይም “ፓንዴሚክ” (Pandemic) ሊሆን ይችላል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት “ኤፒዴሚክ”ን ወረርሽኝ ብሎ ይተረጉማል፣ ለ”ፓንዴሚክ” የሰጠው ትርጉም ደግሞ “ወራሪ በሽታ” የሚል ነው፡፡ በሁለቱ ትርጉሞች መኻከል ያለው ልዩነት ግልጥ አይደለም፡፡

በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ምርምር ማእከል የተዘጋጀው መዝገበ ቃላት፣ ለ”ወረርሽኝ” የሰጠው ትርጉም፣ ” ከአንድ ወደ ሌላው እየተላለፈ በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎችን የሚያጠቃ እንደ ጉንፋን፣ ተስቦ——ያለ በሽታ ነው” ይላል፡፡ በደስታ ተክለወልድ የተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ የ”ወረርሽኝ” ትርጉም፣ “የጉንፋን ወይም የወባ በሽታ አንዳንድ ዘመን አየር ሲለወጥ ከክረምት ውጭ እየተነሣ አገርን የሚወር፣ ኅዳር ሲታጠን የሚቀር”፣ ከዚያ ቀጠል አድርጎ፣ “ራሔሎን ተመልከት” ይላል፡፡ “ራሔሎ”ን ሲተረጉም፣ ” የልጆች በሽታ ወረርሽኝ ክረምት ሲመጣ የሚመጣ ጉንፋን ትክትክ ባንዳንድ ዘመን እየበረታ ልጆችን ይገድላል፡፡ ባላገሮችም ራሔሎ፣ ኺጂ ቶሎ ቶሎ እያሉ ንፍሮ ይበትናሉ፡፡ ይህም ስም የማቴዎስ ወንጌል (ም ፬ ቁ ፲፰) ራሔል ስለልጆቿ አለቀሰች፣ መጽናናትም አልቻለችም፣የሉምና ካለው ንባብ የተያያዘ ነው” ይላል፡፡ጉዳዩን ወደ “ብሉይ ኪዳን” የመሳብ አባዜ መስሎ ታዬኝ:: በትግራይ አንዲሁም በወሎ፣ “ራሔሎ” እንደ መንፈስ (ዛር) ነው የመትወሰደው፡፡

ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ፣ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ከሚሰፍሩት ቃላት አንዱ “ፕሌግ” (Plague) ነው፡፡ “ፕሌግ” የአማርኛ ቀጥተኛ ትርጉሙ፣ ትልቅ ጥፋት የሚያደርስ ኩነት ነው፡፡ የእንግሊዝኛ መዝገበቃላትን ስንፈትሽ “ፕሌግ” የአንበጣ ወረራን፣ የበሽታ ወረርሽኝን ያካትታል፡፡ ስለሆነም የ”ችግር” ገላጭ እንጅ፣ የችግር ምክንያት ገላጭ አይደለም፡፡ ለ”ፕሌግ” ቀጥተኛ ትርጉም ማግኘት ያስቸግራል፣ ከተገኘም “እምነት” ነክ ይሆናል፣ ያም ቃል “መዓት” ነው፡፡ ምክንያቱም “መዓት” በተመሳሳይ መንገድ ችግር ገላጭ ቃል ነው፡፡ የ”መዓት” መንስዔ መጥፎ ድርጊት ሆኖ፣ በሰው ልጅ ላይ በመጥፎ ድርጊቶች መንስዔ የሚሰነዘር መለኮታዊ ቅጣት ነው፡፡ ያም ሆኖ ለ”ፕሌግ” ከ”መዓት” የተሻለ ትርጉም አላገኘሁለትም፡፡ ከዚህ የምንረዳው ግልጥ ያልሆነ ትርጉም፣ ግንዛቤን አወዛጋቢ ሊያደርገው እንደሚችል ነው፡፡

ይህን ካልኹ ኋላ፣ አንድን በሽታ፣ ወረርሽኝ ተብሎ እንዲሰየም የሚያደርገው ልዩ ሁኔታ ምንድን ነው? የሚለውን ላብራራ፡፡ በአንድ ጊዜ፣ በብዙ አካባቢ፣ ብዙ ሰው፣ በአንድ ዓይነት በሽታ ሲለከፍ (ሲጠቃ) ነው ወረርሽኝ የሚባል ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ በሽታው አዲስ ወይም ነባር ወራሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ወረርሽኝ የሚያሰኘው በሽታው በፊት ከሚታወቅበት ሁኔታ በተለየ መልኩ፣ ከተለመደው ሁኔታ በላቀ መልኩ፣ በከፋ ሁኔታ በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎችን ሲያጠቃ ነው፡፡ የወረርሽኝ መንስዔዎች አብዛኞቹ ቫይረሶች እና ባክቴሪያዎች ናቸው (ለምሳሌ ኩፍኝ፣ ፈንጣጣ፣ ጆሮ ደግፍ፣ ጉንፋን፣ የሳምባ ምች፣ ተስቦ )፣ ነጠላ ሕዋስም የወረርሽኝ መንስዔ ሊሆኑ ይችላሉ (ለምሳሌ የወባ በሽታ መንስዔ ነጠላ ሕዋስ ናት)፡፡

ወረርሽኙ ድምበር ዘለል ሆኖ ሲሰራጭ፣ ወይም ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ሲዛመት እና ዓለምን ሲያጥለቀልቅ፣ ከአጥናፍ አጥናፍ ሲያንሰራራ (እንደ ዘመኑ “ኮቪድ-19” /Covid-19) ፣ የበሽታው ዓይነት “ወራሪ በሽታ” (ፓንዴሚክ/ pandemic) ይባላል፡፡

የወረርሽኝ ሳይንሳዊ ይዘት

ከላይ እንደተወሳው የወረርሽኝ መንስዔዎች ቫይረሶች፣ ባክቴሪያዎች እና ነጠላ ሕዋስ ናቸው፡፡ ይህም የሰው ልጅ መታመምን ብቻ ግንዛቤ ውስጥ ካስገባን ነው፣ ምክንያቱም የአንበጣ ወረራም ሆነ የተምች ወረራ “ወረርሽኝ” ይባላል፡፡ የወረርሽኝ መንስዔ የሆኑት ደቂቅ ዘአካል (ተዋስያን)፣ የሰው ልጅን በብዛት ማጥቃት የጀመሩ፣ ምድርን ከተቆጣጠረ ከዘመናት በኋላ እንደነበረ ይገመታል፡፡ ወረርሽኝ በብዛት ማንሰራራት የጀመረው፣ የሰው ልጅ ከብት አርቢ ከሆነ በኋላ እንደሆነ ብዙ የታሪክ ምሁራን ይገምታሉ፡፡

በዘመናችን ወረርሽኝን በጣም አስጊ ከሚያደርጉት ዋናዎቹ ምክንያቶች አንዱ፣ ረጅም ርቀትን ባጭር ጊዜ ውስጥ በፈጣን ጉዞ ማዳረሱ ነው፡፡ ዝግምተኛ ሊባል የሚችለው የመርከብ ጉዞም፣ በአንድ ጊዜ በሽዎች የሚቆጠሩ ተሳፋሪዎች ይዞ ስለሚጓዝ ለወረርሽኝ አመች ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ሌላው ዋናው ምክንያት በዘመናችን የተከሰተ፣ በተለይ በታዳጊ አገሮች፣ ተፋፍጎ መኖር፣ እንዲሁም የፀጥታ መደፍረስ ነው፡፡

የዓለማችን ሕዝብ ብዛት በጣም በመጨመሩ የተነሳ፣ አዳዲስ ሰው የሚሰፍርባቸው ቦታዎች፣ ነባር የዱር እንስሳት መናኸሪያ የነበሩት ላይ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሰው ልጆች እና የዱር እንስሳት የመኖሪያ አካባቢዎችን መጋራት ጀምረዋል፡፡ ይህም ሁኔታ፣ ነባር የዱር እንስሳት ገላ ውስጥ የሚገኙ የቫይረስ ወይም የባክቴሪያ ዝርያዎች (እነኝህ “ተዋስያን” የዱር እንስሳትን ላያጠቁ ይችላሉ) ባህርያቸውን ቀይረው፣ የሰው ልጅ ገላን ለመውረር ይበቃሉ፣ ብሎም የበሽታ መንስዔዎች ይሆናሉ፡፡

በወረርሽኝ መልክ ባይሆንም፣ ተጠጋግቶ መኖር ከእንስሳት ጋር ጥገኞችን ለመጋራት ይዳርጋል፡፡ ለምሳሌ በገጠር የቤት እንስሳት ከሰው ጋር መኖሪያ ይጋራሉ፡፡ በተለይ ዶሮ የቤት አጋር ናት፣ ለመኝታ ቆጥ ተዘጋጅቶላት ነው ቤት ውስጥ የምትኖር ፡፡ የዶሮ ቅማል፣ ከቆጥ እየወረደ፣ ከታች የተኛን ሰው፣ እንቅልፍ የሚነሳበት ሁኔታ ብዙ ጊዜ ያጋጥማል፡፡ የዶሮ ቅማል፣ የዶሮ “ቅንቅን” በመባል ነው የሚታወቅ፣ ያም ከእንጨት “ቅንቅን” (እነጨት ሲነቅዝ፣ በጢንዚዛ ተቦረቡሮ ሲደቅ፣ ወደ ዱቄት መሰልነት ሲቀየር) ጋር መልኩ (የወተት ዱቄት መሰል) ስለሚመሳሰል ነው ያ ስያሜ የተሰጠው፡፡ ይህ እኔን በግል ደጋግሞ አጋጥሞኛል፡፡

የዘመኑ ወረርሽኝ፡ ኮቪድ-19 (COVID-19)/ጉንፋን መሰል ወረርሽኞች

ኮቪድ -19 ቫይረስ በጥቅሉ ኮሮና በመባል ከሚታወቁት የቫይረስ ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡ ቫይረሶች ሕያው አይደሉም፣ ውስብስብ “የኬሚካዊ ወሁድ ፕሮቲኖች” ናቸው፣ አብዛኻኙ “አር ኤን ኤ” (RNA- Ribonucleic Acid) ሲሆኑ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ “ዲ ኤን ኤ” (DNA Deoxyribonucleic Acid) ናቸው፡፡ ሆኖም ሕያው አካል ውስጥ ከገቡ፣ የሕያው አካል መሰናዶን ተጠቅመው እንደ ሕያው ሁሉ ራሳቸውን ለማራባት ይችላሉ፡፡

ኮቪድ -19 በ”አር ኤን ኤ” ታንፆ በስብ መሰል አካል የተሸፈነ ነው፡፡ ይህ ውስብስብ ሞሊኪውል አፍንጫ ንፋጭ ላይ ወይም አፍ እንዲሁም ዓይን ላይ ሲያርፍ ወደ አካባቢ ሕዋሳት ዘልቆ የመግባት አቅም አለው፡፡ ከዚያም የሕዋሳቱን በራሄዎች (genes) በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ራሱን ተኪ ፋብሪካ መሰል መዋቅር ያደርጋቸዋል፡፡ ዋናው ተግባራቸው ቫይረሱን ያለገደብ ማባዛት (ማራባት) ይሆናል፡፡ ቫይረሱ ጤናማ ቆዳን ሰርስሮ መግባት አይችልም፡፡

ቫይረሶች ከሕያው አካል ውጭ የውስብስብ “የኬሚካዊ ወሁድ ፕሮቲን” ባህርይ ተጎናጽፈው፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አካላቸው ይፈራርሳል፣ ብሎም ውስብስብ “የኬሚካዊ ወሁድ ፕሮቲን” መሆናቸው ያከትማል፡፡ ሕያው ስላልሆኑ፣ እነሱን “በፀረ-ሕይወት” (“በአንቲባዮቲክ”/Antibiotics) ማጥፋት አይቻልም፤ ሕይወት የሌለውን በሕይወት አውዳሚ ልናስወግድ አንችልም፡፡ ከአካል ውጭ ህያው ሆነው የሚቆዩበት ጊዜ በሙቀት መጠን፣ በአየር ውሃ አዘልነት ሁኔታ እና በሚገኙበት (ባረፉበት) አካል ባህርይ (ብረት፣ እንጨት፣ ፕላስቲክ፣ ወዘተ) ይወሰናል፡፡

“ኮቪድ-19” በቀላል ለመበታተን (ለመበስበስ) ተጋላጭ የሆነ ቫይረስ ነው፣ ከአደጋ የሚታደገው፣ “ስብ-መሰል” (ጮማ) ሽፋኑ (አልባሱ) ነው፡፡ ስለሆነም ነው በቆሻሻ አስወጋጅ በሆኑ ኬሚካሎች (ሳሙና፣ ወዘተ) በቀላሉ ለመበታተን የሚዳረግ፡፡ ሳሙና እና ሳሙና መሰል ውሁዶች፣ የቫይረሱን ልባስ (ስብ፣ ጮማ) ስለሚያሟሙ፣ ሳሙና ሲነካው ቫይረሱ ከለላ አልባ (አልባስ አልባ) ይደረግና በቀላሉ ይበታተናል፡፡

ሙቀት ጮማን፣ ስብን፣ ስለሚያቀልጥ፣ አካባቢው ሙቀት ከሆነ፣ ቫይረሱ ልባሱ ቀልጦ፣ ሽፋን አልባ ይደረግና፣ “ቫይረሱ” ይፈራርሳል፡፡ ስለሆነም ነው በሙቅ ውሃ እጃችሁን በሚገባ ታጠቡ ተብሎ ምክር የሚሰጥ፡፡ በተጨማሪ ሙቅ ውሃ የሳሙናን አረፋዊ ሁኔታ ያጎላል፣ የሳሙና አረፋ ደግሞ ፍቱን የቫይረስ አፍራሽ መሣሪያ ነው፣ ስለሆነም ነው በሙቅ ውሃ እና በሳሙና መታጠብ የሚመረጥ፡፡

አልኮል፣ ወይም የአልኮል መጠኑ ከስድሳ አምስት ከመቶ (65%) ገደማ የሆኑ ፈሳሾች፣ የቫይረሱን ሽፋን ስለሚከሉ፣ ቫይረሱን ለመበታተን ይዳርጉታል፡፡ “ኢያቅላሚ” (bleaching agent) አንድ እጅ፣ ውሃ አምስት እጅ የሆነ ፣ የውሃ እና የ”ኢያቅላሚ” ቅልቅል (ብርዝ) ዋናውን የቫይረሱን ማዕከላዊ መዋቅር (“አር ኤን ኤ”) ያፈራርሰዋል፣ ብሎም ቫይረሱን በቀላሉ ለመክላት ያስችላል፡፡ አቸቶም ሆነ ቮድካ ለቫይረስ ማጥፊያነት አያገለግሉም፡፡ በጥናት እንደተደረሰበት፣ ቫይረሱ በተለያዩ አካላት ላይ ካረፈ፣ በአማኻኝ በጨርቅ ላይ ሦስት ሰዓት፣ በመዳብ እና በእንጨት ላይ አራት ሰዓት፣ በክርታስ ላይ ሃያ አራት ሰዓት፣ በብረት ላይ አርባ ሁለት ሰዓት፣ እና በፕላስቲክ ላይ ሰባ ሁለት ሰዓት ለካፊ (infective) ሆኖ ሊቆይ ይችላል፡፡

የአካባቢው ሙቀቱ ዝቅተኛ (ቀዝቃዛ አካባቢ)፣ ጨለማ፣ እንዲሁም አየሩ ውሃ አዘል ከሆነ፣ ቫይረሱ ረዘም ላለ ጊዜ ለካፊ ሆኖ ሊቆይ ይችላል፡፡ አካባቢው በብርሃን የተሞላ፣ ብሎም ደረቅ እና ሞቃት ከሆነ፣ የቫይረሱን መፈራረስ (መበስበስ) ሂደት ያፋጥነዋል፣ ስለሆነም ይህ ዓይነት አካባቢ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ያገለግላል፡፡

እንዲሁም አካባቢው በተፋፈገ መጠን፣ የቫይረሱ የመሰራጨት አጋጣሚ በጣም ከፍ ያለ ይሆናል፣ በአንፃሩ ነፋሻ፣ ግልጥ የሆነ ቦታ የቫይረሱን የመሰራጨት እድል ይቀንሰዋል፡፡ የሚመከረው እጅን በሚገባ በሳሙና መታጠብ (ከተቻለ በሙቅ ውሃ)፣ ከጥፍሮች ስር ቫይረሱ እንዳይሸሸግ ጥፍርን መከርከም፣ መዳፍን ማድረቅ፣ ወዘተ፣ መሰል ተግባሮችን መፈጸም፣ እንዲሁም በየጊዜው የሚሰጡ ምክሮችን በጥሞና ማክበር ይገባል፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው የዘመናችን ወረርሽኝ “ኮቪድ-19” (COVID-19) ሲባል የበሽታው መንስዔ የሆነው ቫይረስ ልዩ ስሙ “ሳርስ ኮቭ-2” (SARS‑CoV‑2) ይባላል፡፡ “ኮቪድ-19″ በሽታው ወደ ወረርሽኝነት መዛመት የጀመረ ከ”ውሃን” (Wuhan City) ከምትባል (ቻይና) ከተማ ገበያ አካባቢ እንደነበረ ይታወቃል። በዚህ የበሽታው መነሻ ከተማ ገበያ ውስጥ የተከለከለ የአራዊት ሥጋ ሁሉ ይሸጣል (ለምሳሌ የእባብ፣ የሸለምጥማጥ ዝርያዎች፣ የጥርኝ፣ ወዘተ)።

የሥጋ ገበያው በተፋፈገ ሁኔታ ላይ ስለሆነ የሚያስተናግድ፣ የአንድ እንስሳ ዝርያ ቫይረስ ወደ ሌላ እንስሳ ዝርያ የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም የአንዳንድ የዱር እንስሳት (ለማዳ ያልሆኑ የእንስሳት) ቫይረሶች ወደ ሰው መሸጋገር ስለሚችሉ፣ ይህም ቫይረስ ወደ ሰው የተላለፈው በዚህ መንገድ እንደሆነ ይገመታል።

የዓለም ጤና ድርጅት፣ “ውሃን ከተማ” (Wuhan City) “ሁቤ ክፍለ ሃገር” (Hubei Province) ቻይና (China)፣ በ 31 ዲሴምበር (2019)፣ ወረርሽኙ መከሰቱን ለዓለም አስታወቀ። የወረርሽኙ መከሰትም በኮቪድ-19 (COVID-19) መንስዔ እንደሆነ ገለጠ። ቫይረሱም በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ተደረሰበት፣ ሆኖም በቫይረሱ ከተለከፉት ሰዎች መኻከል ለሞት የሚዳረጉት ቀደም ሲል ተከስቶ ከነበረው ከሳርስ ኮቭ (SARS-CoV) ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ እንደሆነም ታወቀ።

አፋችን፣ የአፍንጫችን ቱቦ እና የዓይናችን የቆዳ ሽፋን በውስጥ በኩል በንፋጭ ገለፈት (mucus membrane) የተሸፈነ ነው፡፡ በሽታው ከአንድ ግለሰብ ወደ ሌላ ግለሰብ የሚተላለፍ አፍ፣ አይን ወይም አፍንጫ አካባቢ በቆዳ፣ ካልተሸፈነ ንፋጭ ገለፈት (mucus membrane) ላይ፣ በንክኪ እዚያ ከደረሰ፣ በንፋጭ ገለፈት ዘልቆ የሰውን ውስጥ አካል ለመውረር ይችላል።

አንድ የታመመ ግለሰብ “ሲያስል”፣ ወይም “ሲያስነጥስ”፣ ወይም “ሲተነፍስ”፣ “ሲነጋገር”፣ “ሲስቅ”፣ “ሲቧርቅ”፣ ከአፉ ወይም ከአፍንጫው፣ ጥቃቅን የእርጥበት ነጠብጣቦች፣ “ጠብታ ብናኝ” (droplets) በኮቪድ-19 ቫይረስ ተበክለው፣ በአካባቢው ይሰራጫሉ፡፡ ከእስትንፋስ ጋር የሚወጡ ነጠብጣቦች፣ ፍንጣቄዎች፣ ከአራት ሜትር በላይ እንደሚወረወሩ የሚገልጥ መረጃ አለ፡፡ እንዲሁ ሰው ሲነጋገርም ጠብታዎች በአካባቢው ሊሰራጩ ይችላሉ፡፡ “የኮሮና ቫይረስ” አካል በጣም ውስን ስለሆነ፣ በምራቅ ጠብታ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቫይረሶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

እነኝህም ዓይነት ጠብታዎች ከጤነኛ (በበሽታው ያልተለከፈ) ሰው አፍ፣ አፍንጫ ውስጥ (ቱቦ) ወይም ዓይን ላይ ሲያርፉ፣ ቫይረሶች ካረፉበት ዘልቀው ወደ ገላ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ከዚያም በደም አማካኝነት ወደ ሁሉም የገላ አካላት ይሰራጫሉ፡፡ የቫይረስ ጥቃት መጀመሪያ ላይ የሚስተዋለው “በሥርዓተ መተንፈስ” (በሳምባ እና በሳምባ ቱቦዎች አካባቢ) ነው፡፡ ቫይረሱ ወደ ገላ ዘልቆ የሚገባበት ስልት (ዘዴ) ከሌሎች ዘመዳሞች ቫይረሶች ጋር ይመሳሰላል፣ ለምሳሌ “ከሳርስ ኮቭ” (SARS CoV) ጋር፡፡

በሽታው ብዙ መገለጫዎች አሉት፣ ትኩሳት፣ ድክመት፣ ደረቅ ሳል፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የመመገብ ፍላጎት መቀነስ፣ ድካም፣ ጣዕም መለየት እና ማሽተት መሳን፣ ወዘተ፣ መሰል ናቸው፡፡ በሽታው በአጠቃላይ ሲታይ የመተንፈስ ችግር፣ የኩላሊት ተግባር መቃወስ፣ ድካም መሰማት፣ ያስከትላል፡፡ በበሽታ መንስዔ ሕይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች አስከሬኖች ሲመረመሩ፣ በአንጎል፣ በደም ሥርዓት፣ በመተንፈሻ ሥርዓት፣ በኩላሊት፣ በጉበት፣ በልብ (በሠራ አካላት ማለቱ ይቀላል)፣ በሽታው ብዙ ጉዳት እንደሚያደርስ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

“በኮቪድ-19” (COVID-19) የተያዘ በሽተኛ፣ ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው፣ ከመቼ ጀምሮ እስከ መቼ ድረስ፣ ሊያጋባ፣ ሊያስተላልፍ እንደሚችል እርግጠኛ መረጃ ገና አልተገኘም፡፡ ሆኖም አንድ የታመመ ሰው፣ “ቫይረስን” እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ ለሌላ ሰው ሊያስተላልፍ (ሊያጋባ) እንደሚችል ይገመታል፡፡

በበሽታው የተያዘ ግለሰብ ጠብታ ብናኞች፣ ፍንጣቂ፣ አካባቢ ቁስ ላይ አርፈው፣ አካባቢውን ሊበክሉ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች ከእስትንፋስ ነጠብጣቦች ውስጥ ሆነው ያረፉበት ከዚያም በንክኪ በሽታ ሊያስከትሉ ይችላል፡፡ ያም ከቁሱ፣ በእጅ አማኻኝነት፣ ወደ አፍ፣ አፍንጫ ወይም ዓይን ላይ ሲያርፉ ነው፡፡ የበሽታው መንስዔ የሆነውን የቫይረስ ዝርያ ከአካባቢ ከምንነካቸው ቁሳቁስ፣ እቃዎች ወደ ሰውነታችን ሊገባ የሚችል፣ ያን የተበከለ አካባቢ፣ ቁስ፣ በእጃችን ነክተን፣ እጃችንን ሳንታጠብ አፋችንን፣ አፍንጫችንን ወይም ዓይናችንን ስንዳስስ ነው፡፡ ስለሆነም እጅን ደጋግሞ በደምብ በሳሙና ማፅዳት አንዱ ፍቱን የመከላከያ ዘዴ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

“ቫይረሶች” ከገላ ውጭ ሆነው፣ በሽታ የማስከተል አቅማቸው ሳይኮላሽ፣ እስከ ስንት ጊዜ እንደሚቆዩ በእርግጠኝነት ባይታወቅም፣ በእጅ የሚነካ አካባቢን ደጋግሞ ማጽዳት ይበጃል፡፡ ለምሳሌ የበር እጀታን፣ ከፎቅ መውረጃ እጅ ድጋፍን፣ የምግብ ቁሳቁስን፣በአጠቃላይ በጋራ የምንጠቀምባቸውን ቁሳቁስ ሁሉ በተደጋጋሚ ማጽዳት ያሻል፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው፣ የወረርሽኙን መዛመት ለመግታት በየግላችን ማድረግ የምንችል እና መፈጸም ያለብን የሚከተሉትን ተግባራት ነው። እጆቻችንን በሚገባ አጽድቶ መታጠብ፣ እንዲሁም “ጀርም” አምካኝ በሆኑ ፈሳሾች ማጽዳት፣ ስናስል፣ ስናነጥስ እጃችን ላይ ሳይሆን ክርናችን አካባቢ እንዲሆን፤ አፍና አፍንጫን በ”ማስክ” መሸፈን፣ ፊታችንን በተለይ ዓይንን፣ አፍንጫን፣ አፍን፣ በእጃችን አለመንካት፤ አለመጨባበጥ፣ ተራርቆ መቆም፣ ተራርቆ መቀመጥ፣ በብዛት የሚነኩ ቁሶችን (የበር እጀታ፣ የፎቅ መውረጃ ድጋፍ (ሃዲድ)፤ ደጋግሞ ማጽዳት፣ ወዘተ ናቸው፡፡

ማስታወስ የሚገባው፣ ሁሉንም ምክራዊ ተግባሮች፣ አንዱን ከአንዱ ሳይለዩ፣ ማከናወን ማስፈለጉን መረዳት ነው፡፡ የሚሰጡ ምክሮችን ሁሉንም በጋራ መተግበር የሚያስፈልገው፣ ቫይረሱ አንዱን የጥንቃቄ (መከላከያ) ረድፍ ሾልኮ ቢያመልጥ፣ በሌላው የመከላከያ ስልት እንዲገታ ለማድረግ ስለሚያስችል ነው፡፡ ከተቻለ ከሁሉም ፍቱን መከላከያ የሚሆነው፣ ከቤት ሳይወጡ፣ ከቤተ ሰብ ሌላ፣ ሌሎችን ግለሰቦች ሳያገኙ መዋል፣ መሰንበት፣ ነው፡፡

እንዲሁም በስብሰባ አለመሳተፍን፣ ትምህርት ቤቶችን መዝጋትን፣ የመንገድ ጉዞን መቆጣጠርን ያካትታል፡፡ በአገር ደረጃ የተጠናከረ ምርመራ ማካሄድ (ብዙ ሰዎች በብዙ አካባቢ እንዲመረመሩ ማድረግ)፣ በበሽታው የተለከፉ ግለሰቦችን (ቫይረሱ የተገኘባቸው) የመታመም ስሜት ባይኖራቸውም፣ ከእንቅስቃሴ እንዲገቱ፣ የታመሙት እስኪያገግሙ ድረስ ፣ በሆስፒታል፣ በቤት ውስጥ፣ ተወሰነው እንዲቆዩ የማድረግ ተግባራት ናቸው፡፡

በቀላሉ ሊተገበሩ የሚችሉ ተግባራት ከላይ የተጠቀሱት ሲሆኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ የመከላከል እርምጃዎችም ሊወሰዱ ይችላሉ። “ኮቪድ-19” የሚሰራጭ በእስትንፋስ ስለሆነ ነው፣ አፍንጫ እና አፍ በጭምብል (“ማስክ”) ሸፍኑ የሚል ምክር ደጋግሞ የሚለገሰው፡፡

የበሽታው ሁኔታ ከጉንፋን ካልከፋ ሁኔታ እስከ ሕይወት ማውደም ድረስ የተለጠጠ ነው፡፡ ቫይረሱ ከለከፋቸው ግለሰቦች ብዙዎቹ ከበሽታው ለማገገም ሲችሉ፣ ሌሎች ጥቂቶች ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ በበሽታው ተይዘው ለሞት ስለሚዳረጉት ግለሰቦች፣ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ አህዛዊ ግምቶች ተሰንዝረዋል፣ ግምታዊ ስሌቱ ከሁለት ነጥብ ሦስት በመቶ (2.3 %) እስከ አምስት በመቶ (5 %) የተለጠጠ ነው፡፡ ታመው የዳኑ ግለሰቦች፣ በበሽታው እንደገና ሊያዙ ወይም እንደክትባት ተቆጥሮ ሁለተኛ ላይያዙ መቻላቸው ገና አልተረጋገጠም፡፡

ያም ሆኖ ግን በሽታው ከታመመ ግለሰብ ወደ ጤነኛ በቀላሉ ስለሚጋባ፣ ስርጭቱ በጣም ፈጣን እና ሰፊ ነው፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊለከፉ፣ እንዲሁም ወረርሽኙ ብዙ ቦታዎችን (አገሮችን) ሊያዳርስ ይችላል፣ ብሎም ብዙ ሰዎችን ያጠቃል፡፡ ለህልፈት የሚዳረጉት ሦስት በመቶ (3 %) ናቸው ብለን ግርድፍ ግምት ብንወስድ፣ የሚሞቱትን ልንገምት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ 10 ሚሊዮን (አሥር ሚሊዮን) ሰዎች በበሽታው ቢለከፉ፣ ከነኝህ በአማኻኝ 300,000 (3 %) ለሞት ይዳረጋሉ ማለት ነው፡፡

እስካሁን የተገኘው ማስረጃ እንደሚያመለክተው፣ በበሽታው ለህልፈት የሚዳረጉት (በበሽታው ተይዘው እስከ መሞት የሚደርሱት) አብዛኻኙ ቀደም ሲል በሌሎች በሽታዎች፣ ለምሳሌ የልብ በሽታ፣ የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ ከመተንፈስ ጋር የተቆራኙ ህመሞች (ሳል፣ አስም)፣ የካንሰር በሽተኞች፣ የኩላሊት ታማሚዎች፣ ሲሆኑ፣ እንዲሁም ክብደታቸው ከመጠን ያለፈ እና የሲጋራ ማጤስ ጠባይ ያላቸውንም ያካትታል፡፡ በሽታው ከእድሜ ጋርም የተዛመደ ስለሆነ (እድሜ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ከመጋለጥም ጋር የተዛመደ ነው)፣ በብዛት የሚሞቱት እድሜያቸው ገፋ ያሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡

የወረርሽኝ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖዎች ምሳሌዎች

ወረርሽኝ የሰውን ልጅ የሚያጠቃበት መንገድ የትየለሌ ነው፣ የሕዝብ ብዛትን፣ ባህልን፣ ፖለቲካን፣ ስልጣኔን፣ የሃብት ማካበትን እና የተፈጥሮ ክብካቤን ጭምር ሲያቃውስ የኖረ፣ ያለ፣ ወደ ፊት የሚኖር፣ ተፈጥሯዊ ጠላት መሆኑ ይታመናል።

የመንግሥታትን መዳከም

በወረርሽኝ መዛግብት፣ ከሁሉ በፊት የሚወሳው፣ “የፔሉስየም” (Pelusium) ወረርሽኝ፣ በ541 ነበር የተከሰተ፡፡ ተውሳኩ በ542 “ቆስጠንጥንያን” ወረረ። “ቆስጠንጥንያ” በዚያን ዘመን፣ በንጉሠ ነገሥት “ጁስቲንያን” (Emperor Justinian) የሚመራው የሮማውያን ምሥራቅ ግዛት መናኸሪያ ከተማ (ዋና ከተማ) ነበረች። ወረርሽኙ እየጠነከረ ሲሄድ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ልዩ የበጎ አድራጎት ተግባር ፈጸመ ይባላል፡፡ ያም ድርጊት ለሞቱ ደሃዎች ሁሉ ለቀብር ሥርዓት የሚያስፈልገውን ወጭ መሸፈን ነበር። ወረርሽኙ ከዓመት በኋላ “ሮማን” አጠቃ፣ ብዙ ሳይቆይ በ 544 “ብሪታንያ” ደረሰ። ከዚያ በኋላ የንጉሠ ነገሥቱ የበላይ የጦር መኮንኖች የምዕራቡን ግዛት ሮምን ጭምር መቆጣጠር ተሳናቸው።

ወረርሽኙ እንደገና “ቆስጠንጥንያን” በ 558፣ በ 573 እና በ 586 ደጋግሞ አጠቃ፤ የወረርሽኙ ጥቃት እስከ 750 ድረስ ዘለቀ። ያም ሁኔታ የታሪክን አቅጣጫ ለመቆጣጠር በቃ ይባላል፡፡ የሮማን የተንጣለለ ግዛት በተከታታይ ወረርሽኞች መንስዔ እንደተዳከመ ይገመታል፡፡ ከዚህ ወረርሽኝ በኋላ ነበር የሮማን የተንጣለለ ግዛት ሰላም ያጣው እና በመጨረሻም ለመንኮታኮት የበቃ፡፡ በወረርሽኝ በተዳከመ ግዛት፣ መንግሥት ደካማ በነበረበት ዘመን ነበር ክርስትናም በሮማን ግዛት ውስጥ መስፋፋት የቻለ፡፡ የክርስትና እምነት፣ የወረርሽኝን ኮቴ ተከትሎ፣ በጭንቀት ላይ የነበሩ የማህበረሰቡ አባላትን በብዛት፣ በአጭር ጊዜ፣ ተስፋ አጎናጽፎ፣ አሰንቆ፣ ለአማንያን ለማበርከት የበቃ፡፡ በተጨማሪ በዚያን ወቅት አዲስ የዓለም ሥርዓት እየተገነባ ነበር፡፡ ጠንካራው የእስልምና ሃይማኖት በአካባቢው ማንሰራራት የጀመረ በዚያን ዘመን ነበር።

ማህበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ ቀውስ

“የፕሌግ” ወረርሽኝ በ1348 እንግሊዝ አገር አንሰራርቶ ስለነበረ እና፣ ብዙ እልቂትም ስለአስከተለ፣ የእንግሊዝ አገር ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መንስዔ ሆኖ ነበር። ብዙ ሕዝብ በወረርሽኙ ምክንያት ስለሞተ፣ በእንግሊዝ አገር ከፍተኛ የሠራተኛ እጥረት ተፈጥሮ ነበር። ወረርሽኙ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋን አናረው፣ ቀደም ብሎ እንደነበረው በቀላል ደመወዝ ክፍያ፣ ሠራተኛ ቀጥሮ ማሠራት አልተቻለም ነበር። አንዳንድ የታሪክ ምሁራን፣ ይህ ታሪካዊ ክስተት ለእድገት እና ለለውጥ እንደ አንድ ዓቢይ ምዕራፍ ሆኖ መወሰድ አለበት ብለው ያምናሉ።

ይኸው ወረርሽኝ በአውሮፓ ውስጥ ያልታሰበ ማህበራዊ ቀውስም አስከስቶ ነበር። አብዛኻኙ የአውሮፓ ማህበረሰብ ወረርሽኙን አምላክ እንደላከባቸው መቅሰፍት አድርገው ሲመለከቱት፣ ሌሎች ደግሞ በተለይ በፈረንሳይ፣ በስፓኛ የነበሩ መንግሥታት እና የክርስትና ሃይማኖት አባቶች፣ ይሁዲዎች በውሃና በምግብ ላይ በጨመሩት መርዝ መንስዔ ነው በሽታው ያንሰራራ ብለው ያምኑ ስለ ነበር፣ የአካባቢው ሕዝቦች በመንግሥት እገዛ፣ ይሁዲዎችን በጅምላ መግደል ላይ ተሰማርተው ነበር። በዚያን ዘመን በስፓኛ እና በፈረንሳይ አገር ሕፃን፣ ሽማግሌ፤ ወንድ፣ ሴት ሳይለይ፣ አሰቃቂ የይሁዲዎች ግድያ ተካሄደ። ከዚያም ቀደም ሲል፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በሰሜን አፍሪካ (በ1290 አካባቢ)፣ በአውሮፓ የተካሄደውን ዓይነት የይሁዲዎች ጅምላ ግድያ ተካሂዶ እንደነበረ ይወሳል።

የሥልጣኔ መውደም

በአዲሱ ዓለም (አሜሪካ) የፈንጣጣ ወረርሽኝ መጀመሪያ የተከሰተ በ1518 ነበር። ይህም “ክርስቶፎር ኮለምበስ” (Christopher Columbus) የዚያን አካባቢ በጐበኘ ከሩብ ምዕተ-ዓመት በኋላ ነበር። በ1519 ሁለት የዘመኑ የካቶሊክ መነኮሳት፣ ለስፓኛው ንጉሥ፣ “ለቀዳማዊ ቻርልስ” (Charles I) በጻፉት ደብዳቤ ሁኔታውን ሲያብራሩ፣ “አምላክ ይህንን የፈንጣጣ ወረርሽኝ በነባር ኗሪዎች መዓት አውርዶ፣ ቅጣቱን ተግባር ላይ ስላዋለ፣ እና ወረራው እንዳይገታ ስላደረገ፣ ምስጋና ይገባዋል” ብለው ነበር። በዚያ ወረርሽኝ መንስዔ ሕዝቡ ተዳክሞ ስለነበረ፣ በ1519 “የአዝቴክ” ዋና ከተማ “ቴኖኪቲላን” (Tenochitilan) በቀላሉ በስፓኝ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ለማዋል በቃች። እንዲሁም በ1532 ሌላው የአካባቢ ዝነኛው “የኢንካ” መንግሥት፣ በስፓኞች የተጠቃ፣ በወረርሽኝ የተዳከመ ስለነበረ ነው፣ ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንደሚባለው።

ከወራሪው ጦር ጋር ወደ አዲሱ ዓለም በመጡ በሽታዎች መንስዔ (ፈንጣጣን ጨምሮ)፣ ስንት ያካባቢው ሕዝብ እንዳለቀ በርግጥ ባይታወቅም፣ ከ10 ሚሊዮን ያላነሰ ሕዝብ በተላላፊ በሽታዎች ለህልፈት እንደተዳረገ ይገመታል። ከሁሉም አሰቃቂ የነበረውና አብዛኻኙን ነባር የክፍለ ዓለሙን ሕዝብ ለሞት የዳረገ፣ ፈንጣጣ ነበር ይባላል። ያም ስለሆነ፣ ወራሪዎች ግዛት በሚመሠርቱበት ዘመን፣ የሰው ኃይል እጥረት ስለገጠማቸው፣ አፍሪካውያንን በባርነት መልክ፣ ወደ አዲሱ ዓለም አግዘው በጉልበት ሥራ ላይ እንዲሠማሩ አደረጓቸው። ይህም የታሪክን አቅጣጫ እንደቀየረ ይታመናል፡፡ ያ የታሪክ ጠባሳ፣ ጠባሳ ነውና፣ ይሸፈን፣ ይለባበስ ይሆናል እንጅ፣ የመወገጃ መንገድ ያለው አይመስልም፡፡

ከዚያም የፈንጣጣው ወረርሽኝ ወደ ደቡብ ዘምቶ፣ ወራሪው የስፓኛ ጦር ገና እዚያ አካባቢ ሳይደርስ፣ ጠንካራ እና ዝነኛ የነበረውን “የኢንካን” (Inca) መንግሥት አመሰቃቀለው። የወረርሽኝ መንስዔዎች ሁሉ ከወራሪው የስፓኛ ጦር እንዲሁም በባሪያ መልክ በአካባቢው ወራሪዎች ባሰማሯቸው አፍሪካውያን ጋር ነበር ወደ አዲሱ ዓለም የዘመቱት፡፡ ነባር የአካባቢ ሕዝቦች ለበሽታው እንግዳ ስለነበሩ እና ሰውነታቸው (አካላቸው) ለነኛ ዓይነት በሽታዎች ምንም የመከላከል መሰናዶ ስላልነበረው ነበር በሽታውን ሊቋቋሙት ያልቻሉት፡፡ በዚያ ምክንያት በፈንጣጣ ከተለከፉ ሰዎች ዘጠና በመቶ (90%) ለሞት ይዳረጉ ነበር፡፡

ከዚያም በኋላ የአውሮፓ መንግሥታት ወታደሮች ወደ አሜሪካ ክፍለ ዓለም ሲዘልቁ፣ በዚያ የነበሩ መንግሥታት እያንዳንዱ ሥርዓቱ የተዛባበት፣ ሠራዊቱ የተዳከመበት፣ ጠላት፣ ወራሪ የማይመክት፤ እያንዳንዱ የአካባቢ ማህበረሰብ አባል፣ በጠኔ የተሰበረ፤ በበሽታ የተወረረ፣ አሞቱ የፈሰሰ፣ ጉልበቱ የኮሰሰ፣ ነበር። እንደ ቋያ እሳት የተቀጣጠሉ፣ ደጋግመው የተከሰቱ ወረርሽኞች፣ የዚያን አካባቢ ታሪክ አዲስ አቅጣጫ ቀየሱ።

ከዚያ በኋላ፣ በዚያ አካባቢ የተከሰተው “ኮኮሊዝትሊ ወረርሽኝ” (Cocoliztli) በሚባል የሚታወቀው ከ1545 እስከ 1548 ነበር በመካከለኛው አሜሪካ የተከሰተ። ቃሉ “ኮኮልዝትሊ” በአዝቴክ (Aztec) ቋንቋ “ቸነፈር” ማለት ነው። በዚህ ወረርሽኝ 15 ሚሊዮን (አሥራ አምስት) ሕዝብ በሜክሲኮና በሌሎች መኻከለኛው አሜሪካ ለህልፈት እንደተዳረጉ ይገመታል። በበሽታው ብዙ ሰው የሞተ፣ ቀደም ሲል የአካባቢው ማህበረሰብ በድርቅ መንስዔ ለቸነፈር የተጋለጠ ስለነበረ መሆኑ ይታመናል።

ከዘመናት በኋላ ”ኮሌራ” በአሮጌው ዓለም (አፍሪካ፣ እስያ እና አውሮፓ) ለተከታታይ ወረርሽኞች መንስዔ ሆኖ ነበር፡፡ የኮሌራ” ወረርሽኝ በሕንድ አገር ከ1829 ጀምሮ፣ ወደ ሩስያ ከዚያ ወደ ምዕራብ አውሮፓ እና ወደ አሜሪካ ዘለቀ። ኮሌራ ከፈንጣጣ የሚለየው ኢኮኖሚያዊ ይዘት ስላለው ነው፡፡ እየመረጠ ደሃ ነው የሚገድል። የበሽታው መንስዔ በሰገራ የተበከለ ምግብ ወይም መጠጥ ስለሆነ፣ እና ያ ደግሞ የደሃዎች እንጅ የሃብታሞች ችግር ስለአይደለ ነው፣ በሽታው ሃብታም የማያጠቃው፡፡

በ19ኛው ምዕተ ዓመት፣ በተከታታይ ዓመታት፣ በተከሰቱ የ”ኮሌራ” ወረርሽኞች፣ “በብሪታንያ” (“በሊቨርፑል” /Liverpool)፣ በስኮትላንድ (“በግላስጎ”/Glasgow) እና አየርላንድ (በደብሊን/ Dublin) ረብሻ ተቀስቅሶ ነበር። ሃኪሞች ታማሚዎችን ለሞት እየዳረጓቸው ነበር ብሎ በማመን ነበር፣ የሕዝብ አመጽ የተቀሰቀሰ፡፡ በዚያው ዘመን፣ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በተለያዩ የሩስያ አካባቢዎች ረብሻ ተቀስቅሶ፣ ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ብሎም የንግድ ቤቶች ለክስረት ተዳርገዋል።

በሩስያ ከተቀሰቀሱት አለመረጋጋቶች (ረብሻዎች)፣ አመጹ ጐልቶ የታየ “ቅዱስ ፒተርስበርግ” (St. Petersburg) አካባቢ ነበር። የከተማዋ ባለስልጣኖችም፣ የረብሻው አቀንቃኞች ናቸው ያሉዋቸውን ግለሰቦች፣ ከባድ ቅጣት መቅጣት ጀመሩ፡፡ ያም ሁኔታ ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዲቀሰቀስ ጋባዥ ሆነ፣ መንግሥት ክንዱን ባጠናከረ መጠን፣ አመጹ እየገነፈለ ሄደ። ከዘመናት በኋላ ለተከሰተው፣ ለታላቁ የሩስያ አብዮት እንደ “እርሾ”፣ እንደ “ጥንስስ” እንዳገለገለ ይገመታል፡፡ ማለት “ኮሌራ” በ1917 ለተከሰተው ታላቁ የሩስያ አብዮት መድረክ አዘጋጀ፤ ከዚያም ወቅቱ ሲመቻች፣ አብዮቱ ፈላ፣ ገነፈለ፣ ተቀጣጠለ፣ መሰል ግምት ነው።

ወረርሽኝወደፊት ሊከሰት ይችላል ወይ?

ወደፊት ወረርሽኝ ይመጣል ብሎ ማመን ታሪክን ያገናዘበ ሀቅ ነው፡፡ በሃያኛው ክፍለ ዘመን፣ በተለያዩ አከባቢዎች የተከሰቱ “የፍሉ” ዓይነቶች፣ ምንም መሠረታዊ ሳይንሳዊ መዋቅሮቻቸው ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ የሚያስከስቷቸው የበሽታ ዓይነቶች ይለያያሉ፣ ስለሆነም የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥቷቸው፣ የ”ስፓኛ ፍሉ”፣ የ”እስያ ፍሉ”፣ የ”ሆንግ ኮንግ ፍሉ”፣ ወዘተ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ቫይረሶች ባህሪዎቻቸውን ቀይረው፣ የወፍ ዘር ወራሪ፣ ወይም የሌት ወፍ ወራሪ ወዘተ የነበሩ ሰውን ማጥቃት የሚችሉ አሁን እንዳሉ ሳይንሳዊ ሀቅ ነው፡፡

ከልልዩአካባቢዎችሊከሰቱየሚችሉተላላፊበሽታዎችየሰውንልጅስጋትላይእየጣሉትነው፡፡ ከላይእንደተጠቀሰውእነኝህየወረርሽኝመንስዔሊሆኑየሚችሉሕያውአካል፣ ኑሯዋቸውሰውበሌለበት፣ከሰውጋርግንኙነትለመፍጠርበማይችሉበትሁኔታ የተከለለ ነው፡፡ለሰውልጅ የበሽታ መንስዔ፣ ሊሆኑየሚችሉማይክሮቦችበተለያዩቦታዎችሊገኙይችላሉ፡፡ ሆኖም ከሰው ጋር ካልተገናኙ የሰው ልጅ የበሽታ መንስዔ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

በዓለም ላይ በየጊዜው የሚከሰቱ አዳዲስ በሽታዎች የሰው ልጅ የራሡን ድንበር ዘልሎ ወደ ዱር እንስሳት መኖሪያ ሲዘምት የተከሰቱ ናቸው ይባላል፡፡ በመሠረቱ እነዚያ የአዳዲስ ወረርሽኝ መንስዔ የሆኑ ጀርሞች (ለምሳሌ” ኢቦላ” ፣ ሳርስ ወዘተ)፣ ከጠፈር፣ ከዓለም ውጭ፣ በ ‘ኮሜት’ ተሳፍረው የመጡ አይደሉም፣ የዚህ የኛው ዓለም ነባር ኗሪዎች ናቸው። ሆኖም የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም መዛባት፣ ወይም ተፈጥዊ ጊዚያዊ (የባህር እና የአየር ነውጥ) ከባድ አደጋ ካልተከሰተ በቀር፣ እነዚህ ሕያው ወረርሽኝ አስከታይ አካላት ከሰው ጋር የመገናኘት ሁኔታ አይፈጠርም።

እነኝህ ሕያው አካላት የዱር እንስሳት ጥገኞች ሆነው ሲኖሩ፣ ድንገት ያልተለመደ ግንኙነት በሰው ልጅ እና በነዚህ የዱር እንስሳት መካከል ሲከሰት፣ እነዚህ በሽታ አስከታይ ማይክሮቦች፣ ከዱር እንስሳት ወደ ሰው ልጅ ገላ ይገባሉ፣ ብሎም ብዙ ሕይወት ያጠፋሉ፣ እያጠፉም ናቸው።

እነኝህ ወራሪዎች አገር ድምበር አይለዩም፣ ድምበር ዘለል ናቸው፡፡ አገራት በነጠላ ተከላክለው ወረርሽኙን ሊገቱ አይችሉም። ወረርሽኙ በአጠቃላይ የሰው ልጆች የጋራ ችግር ስለሚሆን፣ መፍትሄውም በጋራ መፈለግ አለበት። ይህንንም ለመተግበር የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አሉ።

ዓለምን የሰው ልጅ ከሌሎች እንስሳት ጋር ተጋርቶ ነው የሰፈረባት፡፡ በመሠረቱ የዱር እንስሳት፣ ስያሜያቸውን፣ ያገኙ ከሰው ጋር በቅርበት አካባቢን ለመኖሪያነት ስለማይጋሩ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዱር እንስሳትን መኖሪያ ሲጋራ፣ የበሽታ መንስዔ የሆኑ “ማይክሮቦች”፣ ድምበር ዘለል ሆነው፣ የሰውን ልጅ ለበሽታ ሊዳርጉት ይችላሉ፡፡ ለነዚህ ዓይነት “ማይክሮቦች” ምሳሌዎች ብዙ ናቸው፣ እነ “ኢቦላ” ( Ebola)፣ “ኤች አይቪ ኤድስ” ( HIV/AIDS )፣ “ሳልሞኔላ” (Salmonella )፣ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ይህን ጉዳይ የበለጠ ለመረዳት እንድንችል የሌሊት ወፍን እንደ ዱር እንሰሳ ወስደን፣ ከዚያች እንስሳ ወደ ሰው ልጅ ሊጋቡ የሚችሉ በሽታዎችን እናውሳ፡፡ በዓለማችን ብዙ የሌሊት ወፍ ብቸኛ ዝርያዎች (species) አሉ፡፡ የሌሊት ወፍ ብቸኛ ዝርያዎችን በጥቅሉ ብንወስድ፣ ብዙ የቫይረስ ዝርያዎች (ወደ አንድ መቶ ሰላሳ የሚገመቱ) ገላቸው ውስጥ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም የሌሊት ወፎች፣ እንደ ቫይረሶች ጎተራ (ቋት) ሆነው ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡

በሌሊት ወፎች ገላ የሚገኙ ቫይረሶች፣ ጥቂቶቹ የሰው ልጅ በሽታ መንስዔዎች ናቸው (ለምሳሌ የውሻ በሽታ፣ ኢቦላ)፡፡ በሽታው የሌሊት ወፎችን አያጠቃም፡፡ ዋናው ምክንያት፣ የሌሊት ወፎች በቫይረሶች ከመጠቃት የሚታደጓቸው ልዩ የሆኑ የመከላከያ መሰናዶዎች ስለአሏቸው ነው፡፡ ስለሆነም፣ ምንም የበሽታ መንስዔዎች በገላቸው ውስጥ ቢገኙም፣ ለሞት ስለማይዳርጓቸው፣ የሌሊት ወፎች በሕይወት እስካሉ ድረስ የበሽታ ጎተራ (ቋት) ሆነው ይዘልቃሉ፡፡

የሌሊት ወፎች ነባራዊ ባህርይ ለበሽታ ማስተላለፍ ሁኔታ የተመቻቸ ነው፡፡ ለዚህም የበሽታ ማስተላለፍ ተግባር የጎላ ሚና እንዲኖራቸው ያስቻላቸው ሁኔታዎች ብዙ ናቸው፡፡ አንደኛ በበሽታው ለህልፈት አለመዳረጋቸው፣ ሁለተኛ የረጅም ዕድሜ ባለፀጐች መሆናቸው፣ ሦስተኛ በጣም ከተለያዩ አካባቢዎች (በርሃ፣ጥሻ፣ ዋሻ፣ ቤት አካባቢ፣ ወዘተ). መኖር መቻላቸው (መገኘታቸው)፣ አራተኛ በየቀኑ በመቶዎች ኪሎሜትሮች የሚቆጠር ርቀት፣ ለምግብ አሰሳ፣ መጓዛቸው፣ አምስተኛ በጣም በተፋፈገ ቦታ ተሰባስበው መኖራቸው፡፡ በአንዳንድ ዋሻዎች ውስጥ ከሚሊዮን በላይ የሌሊት ወፎች ተፋፍገው ይኖራሉ፣ ይገኛሉ፡፡ ይህም ለቫይረስ መባዛት፣ ካንድ የሌሊት ወፍ ወደ ሌላ የሌሊት ወፍ፣ ሁኔታውን አመች ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም ነው አዲስ ወረርሽኝ በተነሳ ቁጥር፣ ሁሉም ተመራማሪ ጣቱን ወደ ሌሊት ወፍ አቅጣጫ የሚቀስር፣ እሷ ናት የበሽታው፣ የወረርሽኙ፣ ቋት ብሎ፡፡

ዋሻ፡ በዓለም ላይ በየጊዜው የሚከሰቱ አዳዲስ በሽታዎች በተፈጥሮ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው፡፡ ከዋሻአካባቢለወረርሽኝመንስዔሊሆኑየሚችሉሕያውአካላትአሉ፣ ለምሳሌ ሂስቶፕላዝሞሲስ” (Histoplasmosis)፣ የውሻበሽታ(Rabies)፣ እናበመዥገርየሚተላለፍ፣ዋሻውስጥከሚኖሩእንስሳትወደሰውልጅሊተላለፉ የሚችሉ፣ የሚተላለፉ፣ የከባድ ትኩሳት መንስዔ የሆኑ ሕያው አካላት አሉ፡፡ እነኝህ በሽታዎች የሰው ልጅን የሚያጠቁ፣ የሰው ልጅ በዚያ አካባቢ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡

ደኖች፡ እንዲሁም በደኖች ውስጥ የበሽታ መንስዔ የሆኑ ሕያው አካላት አሉ፡፡ በሙያውየተሰማሩምሁራንደጋግመውእንደሚያወሱት ሁሉ፣ ደን፣ጫካ፣ በመነጠርንመጠንእናአካባቢውንደኑን፣ እጽዋትአልባስናደርግ፣የወረርሽኝመንስዔ የሆኑ ቫይረሶች፣በደኑውስጥካሉእንስሳትወደሰውልጅየመተላለፉሁኔታእየተመቻቸይሄዳል፡፡ ደኑ፣ ጫካውእንደበሽታመከላከያ፣ መጋረጃሆኖየሚያገለግለው፣ደንውስጥያሉትበሽታአስተላላፊእንስሳትከሰውልጅጋርሳይገናኙደንውስጥተጠልለውእስከኖሩድረስ ብቻ ነው፡፡ የሰውልጅድንበርጥሶ፣ ጫካበመጨፍጨፍ፣ የእንስሳቱንነባርመኖሪያከወረረ፣የደኑእንስሳትየበሽታመንስኤየነበሩቫይረሶችን፣ባክቴሪያዎችንአብሮይረከባል፡፡

በሽታ ለየት ባለ መንገድም ከደን ተነስቶ፣ በአቀባባይ እንስሳት ታግዞ፣ ሰውን ማጥቃት ይችላል፡፡ ለምሳሌ በብራዚልየጫካ መመንጠር እና የወባ መዛመት ቁርኝነት እንዳላቸው መረጃ ተገኝቷል፡፡ መረጃው እንደሚያመለክተው አስር በመቶ (10%) የደን ሽፋን ሲከላ፣ ከዚያ ጋር ተዛምዶ የወባ ስርጭት በዓመት ሦስት በመቶ (3%) እየጨመረ እንደሚሄድ ተመዝግቧል፡፡

እንዲሁምበላይቤርያ” (Liberia) ፍራፍሬ ለማልማት ደኑ፣ ጫካው ሲመነጠር፣ ደን ውስጥ ነባር ኗሪዎች የሆኑ፣ የአይጥ ዝርያዎች፣ ከግብርና ከለማው ፍራፍሬ ለመመገብ ከአካባቢው ጐረቤት ጫካ እየወጡ ወደ ፍራፍሬው ማሳመዝመት ጀመሩ፡፡ እግረ መንገዳቸውን ከሰው ልጅ ጋር፣ ከዚያ በፊት ያልነበረ ግንኙነት፣ መሠረቱ፡፡ ይህ ያልታሰበ ግንኙነት በአይጥ ገላ ውስጥ የሚገኙ ቫይረሶች ወደ ሰው ልጅ መተላለፍ እንዲችሉ አደረገ፡፡

የሰውልጅ፣ በጫካ አይጦች ሽንት፣ ወይም ሰገራ፣ የተበከለ ምግብ፣ መጠጥ፣ ወይም ፍራፍሬ ሲነካ፣ ሲመገብ፣ በበሽታው ይለከፋል፡፡ አንዱ እና ዋናውላሳቫይረስ” (Lasa virus) ሲሆን፣ ይህም ቫይረስ የሰውን ልጅበኢቦላመሰል በሽታ ይለክፋል፡፡ በዚህ ቫይረስ ከሚለከፉ ግለሰቦች በአማኻኝ ሰላሳ ስድስት በመቶ (36%) ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ቫይረስ አስተላላፊ የሆኑየአይጥ አስተኔዎች” (Rodents) “በፓናማበቦሊቪያበብራዚል፣ ታይተዋል፡፡

ፈንጣጣለመጀመሪያ ጊዜ ሰውን ማጥቃት የጀመረው በሩቅ ምሥራቅ እንደነበረ ይታመናል፡፡ የሰው ልጅ ከብት አርቢ እና ገበሬ መሆን ሲጀምር፣ መንደር ሲመሠርት ጫካ መመንጠር ጀመረ፡፡ የሚያረባቸው ከብቶች እና የዱር እንስሳት (ጫካ ውስጥ የሚኖሩ)፣ አካባቢ መጋራት ጀመሩ፡፡ በዚያን ጊዜ፣ አካባቢ ሲጋሩ፣ የዱር እንስሳት ቫይረስ ወደ ቤት እንስሳት ተጋባ፡፡ ለነገሩማ፣ ለማዳ የተደረጉት እንስሳትም፣ ቀደም ሲል የዱር እንስሳት የነበሩ ናቸው፡፡ ከዚያም ለማዳ እንስሳት ቫይረሱን ወደ ሰው ሰፈር ይዘውት መጡ፡፡ ከዚያም ቫይረሱ ባህርይውን ቀይሮ፣ ወደ ሰው ተጋባ ይባላል፡፡

ከደንጋርየተቆራኙየወረርሽኝመንስዔዎችብዙናቸው፡፡ እንደምሳሌነትከቫይረሶች፣ ቢጫወባደንጊ“፣ “ኢቦላ“፣ “ሳርስየውሻበሽታ፣ ሊወሰዱይችላሉ፡፡ የተላላፊ በሽታ መንስዔ የሆኑ የባክቴሪያ ዝርያዎች አሉ፡፡ ከነጠላ ሕዋሳት የተላላፊ በሽታ መንስኤዎች ወባ ፣ ቁንጭር፣ ሊወሰዱ ይችላሉ፣ ሌሎች እንዲሁም ኤች አይ ቪ ኤድስ” (HIV/AIDS)፣ ከዱር እንስሳትየዝንጀሮነገዶች፣ ወደ ሰው እንደተዛመተ ይገመታል (ይጠረጠራል)፡፡ሕይወት ሰላቢ የሆኑ ብዙ ዓይነት በሽታዎች መነሻቸው የአፍሪካ ክፍለ ዓለም ነው፡፡ ኢቦላ(Ebola) ዚካ(Zika) እናሌሎች እንደምሳሌነት ይወሰዳሉ፡፡

በተጨማሪ የባሕር ወለል ጨለማእና በጣም ቀዝቃዛ የሆኑ አካባቢዎች(ለምሳሌ የውቅያኖስወለሎች)፣ ለማይክሮቦች እንደመሸሸጊያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ እንደዚያ ያለ አካባቢ ድንገት በከፍተኛ ማዕበል አካባቢው ሲናወጥ፣ ውሃው ሲገለባበጥ እና ባህሩ ወለል ላይ የነበሩ ማይክሮቦች ጥልቀት ውስን ከሆነ አካባቢ ሲደርሱ፣ ሰውን ለመልከፍ አመቺ ይሆንላቸዋል፡፡

በባህር መናወጥ መንስዔ፣ 1992በባንግላዲሽየተከሰተውየኮሌራወረርሽኝመሠረታዊ ሃብለበራሂ መዋቅሩንበመጠኑ ውቅያኖስ ውስጥ የቀየረ፣ እንደአዲስነገድየሚታይየኮሌራ ዝርያ ምጣቄበበሽታውየተለከፉ ብዙ ግለሰቦችንለህልፈትዳርጓል፡፡

ተላላፊበሽታዎችእናየአየርቅጥለውጥ

የዓለም ጤና ድርጅት እንደ ተተነበየ በ2030፣ የሕፃናት ተቅማጥ በሽታ፣ በአሥር በመቶ(10%) ይጨምራል የሚል ግምት አለ፡፡ የአካባቢው ሙቀት ሲጨምር በሦስት አፅቄዎች (Insects) የሚተላለፉ በሽታዎች ከአሁኑ ሰፋ ያለ አካባቢ ይደርሳሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህም የወባ ትንኝን (ቢምቢን) ያካትታል፡፡ ያም ሆኖ እያንዳንዱ የቢምቢ ዝርያ ተስማሚ የሆነለት አካባቢ ሙቀት ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ወባ አስተላላፊ ቢምቢ ምቹ ሆኖ የምታገኘው 25 oC (78 oF) ሲሆን፣ ዚካ (Zika) አስተላላፊዋ ቢምቢ የሚመቻት የአካባቢ ሙቀት 29 oC (84 oF) ሲሆን ነው፡፡

በአየር ቅጥ ለውጥ መንስዔ፣ የዝናብ መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ ሁለቱም ሁኔታዎች ለወባ ትንኝ መራባት አመች ናቸው፡፡ የዝናብ መጠን ሲጨምር፣ የዝናብ ወቅት ካለፈም በኋላ፣ ብዙ አካባቢዎች ውሃ እንዳቆሩ ለሳምንታት፣ ለወራት፣ ሊባጁ ይችላሉ፣ ብሎም የቢምቢ መራቢያ ኩሬዎች ይሆናሉ፡፡ የዝናብ መጠን ሲቀንስ፣ ለወባ መራባት የማያመቹ፣ ፈሳሽ የነበሩ ጅረቶች፣ ወንዞች፣ ፍሰታቸው ተገትቶ፣ ይፈሱበት በነበረበት ትናንሽ ኩሬዎች ይመሠረታሉ፣ ብሎም ለወባ ርቢ አመች ሁኔታን ያመቻቻሉ፡፡

ተላላፊ በሽታ በሰው ልጅ ላይ አሁንም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ በዓለማችንለህልፈትከሚዳረጉሰዎችሩብ(25%) ያህሉ በተላላፊበሽታመንስዔእንደሆነይገመታል፡፡ በዘመናችን በየዓመቱ በተላላፊበሽታወደ10 ሚሊዮንግለሰቦችለህልፈትይዳረጋሉ፡፡

አዳዲስየሚከሰቱተላላፊበሽታዎችእንዲሁምወረርሽኞችበጤናምሆነበኢኮኖሚልማትሂደትከፍተኛአሉታዊተፅእኖያደርጋል፡፡ ለሁኔታውመባባስምክንያትየሆኑ፣ ብዙ ጊዜ የሚጠቀሱ፣ ሁለትዓብይጉዳዮችአሉ፡፡አንደኛውየተፈጥሮሀብትቀውስነው፡፡ይህምስቅልቅልሁኔታነባርይዘቱንአዛብቶታል፡፡ሁለተኛውየዓለምሕዝብየኢኮኖሚናየሶሻልመስተጋብርሁኔታነው፡፡

በአየርቅጥለውጥመንስዔየአካባቢዎችየዝናብመጠን፣የአካባቢሙቀት፣የእንስሳትስርጭት፣ የበሽታአቀባባዮች መዛመት (ለምሳሌየቢምቢዝርያዎች)፣ የሰውልጅአሠፋፈር፣ ሠፈርምስረታበበሽታተሸካሚሕያውአካላትአቀባይነትየሚሰራጩተላላፊበሽታዎች ሁኔታ ይዘትይቀየራል፡፡በአንዳንድአካባቢዎችአሁንምተቀይሯል፣ ለምሳሌየወባስርጭት፡፡ በቅርብ ጊዜ፣ ወባ ደጋ አካባቢም እየገሠገሠ ነው፡፡ ያም ሊሆን የቻለው፣ የአካባቢ ሙቀት ስለጨመረ መሆኑ ይታመናል፡፡

ወባየዓለምአርባበመቶ(40%) ሕዝብበሚኖርበትአካባቢተሰራጭቶይገኛል፡፡ በተለይ በሦስት አጽቄዎች አማካኝነትከሚተላለፋበሽታዎችሁሉሰፊአካባቢየሚደርሰውየወባበሽታነው፡፡በወባተለክፈውከሚሞቱትግለሰቦችዘጠናበመቶ(90%) የሚገኙትአፍሪካ ውስጥነው፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው ወረርሽኝ በተዘዋዋሪ መንገድ ከአየር ቅጥ ለውጥ ጋር ይዛመዳል፡፡ በአየር ቅጥ ለውጥ መንስዔ “አውሎ ነፋስ”፣ ከባድ ውሽንፍር ይከሰታል፡፡ ከአየር ቅጥ ለውጥ ጋር ተዛምዶ የሚፈጠረው ጎርፍ፣ የአካባቢ ፅዳት መጠበቂያ መሠረተ ልማትን ስለሚደመስስ፣ ለመጠጥ የሚያገለግል ውሃ እና የቆሻሻ ፍሳሽ ይቀላቀላሉ፡፡ የሚበላው ምግብ፣ የሚጠጣው ውሃ በቆሻሻ ይበከላል፡፡ ውጤቱም “ኮሌራ” መሰል የተቅማጥ በሽታ ይሆናል፡፡

ሕዝብን ለወረርሽኝ ከሚያጋልጡት አንዱ ዋና ምክንያት ድህነት ነው፡፡ በቅርብጊዜዚምባብዌተከስቶየነበረውየኮሌራወረርሽኝ፣ወደአንድመቶሺህየሚገመትህዝብአጥቅቶከነኝህአራትያህልለሞትተዳርገዋል፡፡ለዚህበሽታማንሰራራትዋናውምክንያትድህነትቢሆንም፣ድህነቱየሚገለጠውበጽዳትጉድለት(ፅዱ ባለመሆን)የመፀዳጃቦታበበቂሁኔታአለመኖርወይምጨርሶአለመኖርነው፡፡እነኝህሁኔታዎችምግብእንዲሁምመጠጥበቆሻሻ(“ሰገራ” /”ሽንት“) የመበከልሁኔታንያመቻቻሉ፡፡ የተበከለምግብውሀመብላትመጠጣትለኮሌራበሽታያጋልጣል፡፡ እነኝህሁኔታዎችናቸውበቅርብዚምባብዌለተከሰተውምበተደጋጋሚለሚከሰተውም(በኢትዮጽያጭምር) የኮሌራወረርሽኝምክንያትየሆኑት፡፡

ይህንሁኔታከሌላአንፃርእንመልከተው፡፡ብዙግለሰቦችለምንድነውአዳዲስወረርሽኞችበእስያወይምበአፍሪካየሚታዩትይላሉ፡፡ መልሱከሁለቱአካባቢዎችብዝሀሕይወትጋርይዛመዳል፡፡ ብዝሀሕይወትበዛማለትየሕይወትባለፀጋየሆኑአካላትብዙዝርያዎችአሉማለትነው፣ ይህም ማይክሮቦችን ያካትታል ፡፡ ይህም ማለት፣ ብዝሀሕይወት ውስን ከሆነበት አካባቢ ጋር ሲነፃፀር፣ ብዝሀይወትበበዛበት አካባቢ የወረርሽኝ መንስዔ የሆኑ ማይክሮቦች የመኖር (የመገኘት) አጋጣሚ ከፍ ያለ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ የአካባቢው ሕዝብ ቁጥር ሲንር፣ የማይክሮቦች እና የሰው ልጅ በአንድ አካባቢ መገኘት ከፍ ያለ አጋጣሚ ይፈጥራል፣ ስለሆነም በበሽታ የመያዝ አጋጣሚም ይጨምራል፡፡

የ አዳዲስ በሽታዎች መንስዔዎች የሆኑ ማይክሮቦች ከደን ውስጥ ከሚኖሩ እንስሳት ወደ ሰው እንደሚጋቡ ቀደም ሲል ተወስቷል፡፡ ይህም የሚሆነው የሰው ልጅ እና የዱር እንስሳት መኖሪያዎች እየተጠጋጉ ሲሄዱ ነው፡፡ ይህም ከከተሞች ምሥረታ ጋር ይቆራኛል፡፡ ከተሞችበሰፉቁጥር፣የዱርእንስሳትመኖሪያከሰዎችመኖሪያየነበረውርቀትእየቀነሰ(እየጠበበ) ይሄዳል፡፡ ሄዶ ሄዶመጨረሻላይየዱርእንስሳትእናየሰውልጆችመኖሪያ በመጀመሪያ ጎረቤት፣ ከዚያ አካባቢ መጋራትድረስይለጠጣል፡፡ በፊትያልነበረግንኙነት(በሰውልጅእናበዱርእንስሳት) በዚህ መንስዔ ሲከሰት፣ማይክሮቦችበተለይቫይረሶችበቀላሉዱርእንስሳትወደሰውልጅይተላለፋሉ፡

በአፍሪካ የበሽታ መሰራጨትን አመች የሚያደርጉ ብዙ ሁኔታዎች አሉ፡፡ አንዱ መድኃኒት በአግባቡ አለመጠቀም ነው፡፡ መድኃኒት መቋቋም የሚችሉ ማይክሮቦች መከሰት፣ መድሐኒት በአግባቡ ካለመጠቀም የመነጨ ነው፡፡ የአየር ቅጥ ለውጥ በአፍሪካ ብዙ አስከፊ ሁኔታዎች እንደሚያስከትል ይገመታል፡፡ አፍሪካብዙአካባቢየአየርርጥበቱምሆነሞቃትነቱ፣ለብዙበሽታተሸካሚህያውአካል፣ ብሎም ለተለያዩ በሸታዎች መጋለጥ ምቹቦታ ይሆናል፣ ለምሳሌለወባለቢልሃርዚያኦንኮሴርካለቁንጭርለፕሌግለስምጥሸለቆትኩሳትእንዲሁምለቢጫወባ፡፡ በተፈጥሮ ሃብት በአግባቡ ባለመጠቀም፣ የከፍተኛ ችግር መንስዔ፣ ብሎም በተዘዋዋሪ መንገድ (ረሃብ) ለበሽታ መጋለጥን እያስከተለ ነው፡፡ ለዚህ ችግር በጣም ተጋላጭ ከሆኑት አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡

በዓለም ላይ፣ በአፍሪካ ጭምር፣ የሕዝብ እንቅስቃሴ ጉዞ፣ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህም ሁኔታ በተጓዳኝ ወረርሽኞች፣ በአጭር ጊዜ፣ ከአጥናፍ አጥናፍ እንዲያንሰራሩ ሁኔታውን አመቻችቷል፡፡ አፍሪካም የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑት የዓለም አካባቢዎች አንዷ ናት፡፡ ሁኔታውን አፍሪካ ውስጥ የከፋ የሚያደርገው፣ የጤና አገልግሎት በጣም ውስን በመሆኑ ነው፡፡

ከዘመናት በኋላ ”ኮሌራ” ለአሮጌው ዓለም (አፍሪካ፣ እስያ እና አውሮፓ) ለተከታታይ ወረርሽኞች መንስዔ ሆኖ ነበር፡፡ የኮሌራ” ወረርሽኝ በሕንድ አገር ከ1829 ጀምሮ ወደ ሩስያ ከዚያ ወደ ምዕራብ አውሮፓ እና ወደ አሜሪካ ዘለቀ። ”ኮሌራ” ከፈንጣጣ የሚለየው ኢኮኖሚያዊ ይዘት ስላለው ነው፣ እየመረጠ ደሃ ነው የሚገድል። የበሽታው መንስዔ በሰገራ የተበከለ ምግብ ወይም መጠጥ ስለሆነ እና ያ ደግሞ የደሃዎች እንጅ የሃብታሞች ችግር ስለአይደለ ነው፣ በሽታው ሃብታም የማያጠቃው፡፡

በ19ኛው ምዕተ ዓመት፣ በተከታታይ ዓመታት፣ በተከሰቱ የ”ኮሌራ” ወረርሽኞች፣ “በብሪታንያ” (“በሊቨርፑል” /Liverpool)፣ “በስኮትላንድ” (“በግላስጎ”/Glasgow) እና “አየርላንድ” (“በደብሊን”/ Dublin) ረብሻ ተቀስቅሶ ነበር። ሃኪሞች ታማሚዎችን ለሞት እየዳረጓቸው ነው ብሎ በማመን ነበር፣ የሕዝብ አመጽ የተቀሰቀሰ፡፡ በዚያው ዘመን፣ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በተለያዩ የሩስያ አካባቢዎች ረብሻ ተቀስቅሶ፣ ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ብሎም የንግድ ቤቶች ለክስረት ተዳርገዋል።

“በሩስያ” ከተቀሰቀሱት አለመረጋጋቶች (ረብሻዎች)፣ አመጹ ጐልቶ የታየ “ቅዱስ ፒተርስበርግ” (St. Petersburg) አካባቢ ነበር። የከተማዋ ባለስልጣኖችም፣ የረብሻው አቀንቃኞች ናቸው ያሉዋቸውን ግለሰቦች፣ ከባድ ቅጣት መቅጣት ጀመሩ፡፡ ያም ሁኔታ ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዲቀሰቀስ ጋባዥ ሆነ፣ መንግሥት ክንዱን ባጠናከረ መጠን፣ አመጹ እየገነፈለ ሄደ። ከዘመናት በኋላ ለተከሰተው፣ “ለታላቁ የሩስያ አብዮት” እንደ “እርሾ”፣ እንደ “ጥንስስ” እንዳገለገለ ይገመታል፡፡ ማለት “ኮሌራ” በ1917 ለተከሰተው “ለታላቁ የሩስያ አብዮት” መድረክ አዘጋጀ፤ ከዚያም ሁኔታው ሲመቻች፣ አብዮቱ ፈላ፣ ገነፈለ፣ ተቀጣጠለ፣ መሰል ግምት የተሰጠ።

ወረርሽኝወደፊት ሊከሰት ይችላል ወይ?

ወደፊት ወረርሽኝ እንደሚከሰት ይታወቃል፣ የማይታወቀው መቼ እና ከየት፣ እንዴት ዓይነት፣ መሰል መረጃዎች ብቻ ናቸው፡፡ አይቀሬ ነውና፣ በሽታው እንደተከሰተ፣ ዓለም በሙሉ ስለበሽታው ያለውን መረጃ በአስቸኳይ ማዳረስ (ማሰራጨት) ይጠበቅበታል፡፡ በዓለም ላይ ያለው አቅም (ገንዘብ፣ የሰው ኃይል፣ ዕውቀት፣ ወዘተ) ተባብሮ፣ “ለቫክሲን” ፍለጋ ማሰለፍ አስፈላጊ መሆኑ ይታመንበታል፡፡ በተጨማሪ የበሽታ ክስተት አሰሳ ሳይዘናጉ ማካኼድ፣ ለምርመራም ሆነ “ቫክሲን” ለመፈብረክ የሚያገለግሉ በቂ የላቦራቶሪ ዝግጅቶችን ማስተናገድ፣ ወረርሽኙ መከሰቱ ከታወቀ፣ ማህበረሰቡ ራሱን ከወረርሽኙ ለመከላከል የሚያስችሉ ምክሮችን ወዲያውኑ ማበርከት፣ ሥርዓት መዘርጋት፣ ደምቦችን ማውጣት እና ማሳወቅ፣ ባለሙያዎች፣ የመንግሥት ባለስልጣን እንዲሁም የዓለም ጤና ድርጅት በቂ እና ተገቢ መረጃ ለሚመለከተው ሁሉ በአስቸኳይ ማሰራጨት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በአገራችን የአሰሳ (Surveillance) አቅመ ደካማነት አለ፣ ያንን ጠንከር ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ለሕዝብ ጤና ክብካቤ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ የሰለተ የመረጃ ፍሰት፣ ወቅታዊ ሪፖርቶች፣ የፖለቲካ ተዓማኒነት፣ ቁርጠኝነት፣ በቂ የበጀት ድጋፍ፣ ቁሳ ቁስ፣ ወቅቱን የጠበቀ መረጃ አሰባሰብ ስልት ማደራጀት፣ ማጠናከር፣ ወዘተ ይጠበቅብናል፡፡

ቅድመ ዝግጅት የቱን ያህል እንደሚጠቅም ለመገንዘብ ይረዳን ዘንድ፣ ምሳሌ ላውሳ፣ በ”ባንግላዴሽ” በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ ሁለት ማዕበሎችን፡፡ በ1970ዎች (የግሪጎሪያን አቆጣጠር) በ”ባንግላዴሽ” ተከስቶ በነበረ ማዕበል መንስዔ የደረሰ የጎርፍ አደጋ ለአንድ ሚሊዮን ዜጎች የህልፈት ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡ ተመጣጣኝ ኃይል የነበረው ማዕበል በ2020 ሲከሰት፣ በጎርፍ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከሃያ በታች ነበረ፡፡

አሁን የተከሰተውን ወረርሽኝ እንደመነሻ አድርገን፣ የዘመናችን ወረርሽኝ እና ወደ ፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞች ጠቅለል ባለ ይዘት ብንተነብይ እና ብንፈትሽ፣ የዓለማችን ኃያላንን ነባራዊ ሚዛን አዛብተው፣ ሚዛኑ “ከምዕራብ” ወደ “ምሥራቅ” ሊያዘነብል ከሚያስችሉ ግብዓቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት ጭላንጭል ያለ ይመስላል፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top