ጣዕሞት

የ8 ዓመቷ ሊያ ተስፋዬ በጀርመን የስዕል ኤግዚቢሽን አዘጋጀች

ትውልደ ኢትዮጲያዊቷ ሊያ (በጀርመን ሶዬ ተብላለች) የ3ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን በድንቅ የስዕል ተሰጥኦዋ ትታወቃለች። እድሜዋ ገና ስምንት ነው።

አምና በ2012 ዓ.ም. በጀርመን ኑርቲንገን ከተማ በሻኸር ራውም ሮር ኩንስት ኤግዚቢሽን ያቀረበች ሲሆን እያንዳንዱ ስዕሎቿ ከ250 እስከ 500 ዩሮ ተሽጠውላታል። የታዋቂው ሰዓሊ የተስፋዬ ኡርጌሣ ልጅ የሆነችው ሊያ ድጋሚ በዘንድሮው ዓመት እና በዚህ ወር ሌላ ኤግዚቢሽን (በኸቲፍቱንግ ሮፍ) አቅርባለች።

ስለባለብሩህ አእምሮዋ ህፃን እና ስዕሎቿ የጀርመን ጋዜጦች (በተለይም ኑርቲንገን ሳይቲንግ ጋዜጣ) ዘግበውላታል። እድሜዋ አስገራሚ ነገሮችን ከማድረግ ያላገዳት ይህቺ አስደናቂ ህፃን ለሀገሯም የኩራት ምንጭ መሆን ትችላለች።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top