ከቀንዱም ከሸሆናውም

ቡና እና የህይወቴ ማስታወሻ

ለሚመለከተው በሙሉ፤ ታሪኩ በዚህ አያበቃም!!

መጥፎ ልማድ አላት። ወደ ቤቷ የምትሄደው ረጅሙን መንገድ መርጣ ነው። መታመን ለእሷ ትልቅ ዋጋ አለው። ከወይን ይልቅ ውሃን፣ ከጨው ይልቅ ስኳርን፣ እና ከቡናም ይልቅ ሻይን ትመርጣለች። “አንድ ጸሃፊ፤ አሳማኝ ነገርን ሳያቀርብ አያርፍም” እነሱ ያልሆኑትን እሷ ታውቃለች። “እነሱ” ማለት “እዚህ ያሉ ሰዎች” ናቸው። በሚያዩት ነገር ይመዝኗታል። እነሱ እሷ ላይ የሚያዩት እና እሷ ይለያያሉ። ማወቅ ከሚገባቸው በታች ነው የሚያውቋት። በግል ህይወቷ በጣም ታጋሽ ነች። ለምትወደው ነገር ደግሞ እብድ ናት፤ የማትሆነው ነገር የለም።

ካልፈለጉት በቀር ደስታ ከየትም አይመጣም። ነገር ግን፤ እሷ ሁሉንም ነገር የምታየው “እስከመጨረሻው ሙሉ የሆነ ህይወትን መኖር” በሚል እሳቤ ነው። ህሊናዋን በተደጋጋሚ ፀፀት ይጎበኘዋል። ከራሱ እና ከፈጣሪው በቀር ሐሳቡን የሚረዳው ያጣ ሰው ምን ይሉታል? ምክንያቱም እነሱ ብቻ ናቸውና እውነታውን ሊያውቁ የሚችሉት። ሁሉንም እንደየአመጣጡ ትመልሳለች። ግብረመልሷ እንደየሁኔታው ይለያያል። ሆኖም፤ ምንም እንኳ ልቧን ብትከፍትም፤ በቀላሉ ከእጅ የምትገባ አይደለችም። ይህች ሐሳባዊ ሴት ማን ናት?

ብልህ አእምሮ እና ደካማ ልብ አላት። ከምሽቱ 3፡47 ላይ መኪና ባጣች ጊዜ፤ ፈጣሪዋ ያዳናት ቀን ነበር። በራሷ ወደ ውድቀቷ ብትጓዝ እንኳ፤ ሁሌም ቢሆን ፈጣሪዋ ለእሷ ያሰበላት መንገድ አለው። በዛን ወቅት የጊዜን እጀታ ወደኋላ መመለስ አይቻልም… ሁሉም ሰው ለሌሎች ያልነገረው ከራሱ ጋር የሚቆዩ ብዙ ታሪኮች አሉት።

ብዙ በመጨነቅ የእግር እሳት፣ በድቡቁ ህሊና ባልሆነ መንገድ እየተመራችሁ፣ በአካሎቻችሁ ላይ የሚወጡ ጠባሶች… አዎ እነዚህን “የህይወት ትምህርት” ትላቸዋለች። እውነተኛ ሰውን በመፈለግ ብዙ ደክማለች። ቢሆንም ግን አንድም ሰው አላገኘችም… ምፅ ዕድለ-ቢስ!! ማን ነች እሷ? አሳዛኝ ህይወት ነው የኖረችው። አሁን እየዳነች ነው… እስካሁን በህይወት መቆየቷ አይገርማችሁም? መሞት ብቻ ሳለ የእሷ እረፍት። አሁን እሷ ታታሪ ናት። ስለእውነት፤ እሷ እሷን የሆነችበት ምክንያት እሷ ስለነበረች ነው። ህይወት ይቀጥላል… እሷ ግን ማን ነች?

የቅዠት ዓለም

ባለንበት ዘመን፤ በአንዳንድ ዝግጅቶች ላይ አልኮል መቀማመስ ተለምዷዊ ባህሪ ነው። በ2010 ዓ.ም. አካባቢ የማውቃት አንዲት ልጅ ነበረች። ጨዋ የምትባል። ስርዓት ያላት ልጅ መሆኗ፤ መጨረሻዋን ሊያዩ ለሚፈልጉ ሰዎች ተጋላጭ እንድትሆን አድርጓታል። ከዚያም የማያስፈልጓትን ነገሮች ማድረግ ጀመረች። መጠጥ በደጋገመች ቁጥር የበለጠ እየተላመደችው መጣች። ጊዜው ሲነጉድ ብዙ መጠጣት ጀመረች። በመጨረሻም የመጠጥ ሱሰኛ ሆና አረፈችው።

በአጋጣሚ ሳይሆን ፈልጋ መጠጥ ማሳደድ ጀመረች። ያለችበትን ሁኔታ በደንብ ሊገልጸው የሚችለው ቅጽላዊ ሐረግ ይሄው ነው። ‹በአጋጣሚ ሳይሆን ፈልጋ…› ነገሮች በእሷ ላይ እየበረቱ ሄዱ፤ አእምሮዋ መቀላቀል ጀመረ። ከግል ህይወቷ በላይ የቢራ ጠርሙሶችን መሰብሰብ ላይ ትኩረቷን አደረገች። ስሜት የለሽና ዝንጉ ሆነች። ህይወቷ ድብልቅልቁ ወጣ። ሁሉም ነገር ከእሷ ቁጥጥር ውጪ ሆነ። ከመጠጥ ጋር በተያያዘ መሻሻሎችን ማሳየት እችላለሁ ብላ ታስብ ነበር። ነገር ግን ያሰበችውን ሁሉ መጠጡ ውሸት አደረገባት። ስሜት-የለሽ ሆና ቁልቁለቱን ተያያዘችው…

መጠጡ ያልሆነችውን እስክትሆን ድረስ ግራ የምታጋባ ሰው አደረጋት። በዙሪያዋ ያሉትን ሰዎች ግራ በሚያጋቡ ድርጊቶቿ ማበሳጨቱን ተያያዘችው። ልቧን ስትከተል ህሊናዋን ረሳችው። ይሄ ነገር ሊላቀቃት አልቻለም። በተደጋጋሚ እየተመላለሰ ይይዛት ጀምሯል። አንድ የተገነዘበችው ትልቅ ነገር ቢኖር፤ ጓደኝነት እንዳከሰራት ነው። ትክክለኛ ያልሆነውን ነገር ነበር ለጓደኝነት የመረጠችው። በህይወቷ ውስጥ ያሉ ውድ ነገሮችን በአልኮል የተነሳ አጥታለች። ከዚህ ልማዷ በመነጨ ህመም የተነሳ ብዙ ተጎድታለች። …ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ እንዴት እንደሆነች ትጠይቁ ይሆናል። ካለችበት አዘቅት ውስጥ ለመውጣት እየተጣጣረች ነው። በህይወቷ ውስጥ እየተከሰቱ ባሉ ነገሮች ላይ ታጋሽ እና ቆራጥ ሆናለች። ከእሷ ጋር በሚመሳሰል ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች የምታስተላልፈው መልእክት አላት። “በወጣትነታችሁ በመዝናናት እና የወደፊት ህይወታችሁን በማበላሸት መካከል ያለውን ልዩነት ተረዱ” ትላለች። ምክሯን አስተውሉት።

ዝንጉነት፤ አልኮል በአእምሯችን ውስጥ ባሉ ውስብስብ አሰራሮች ላይ ከሚያመጣቸው ችግሮች መካከል አንዱ ነው። ነውጠኛ ባህሪ፣ የተወላገደ አነጋገር፣ የማስታወስ ችግር፣ ፈዛዛነት… አልኮል ከሚያመጣቸው ችግሮች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። አልኮል ሙሉ በሙሉ የሰዎችን ባህሪ ላይለውጥ ይችላል፤ ነገር ግን ሰዎችን ከራሳቸው ውጪ ላለው ነገር በተጋነነ መልኩ ትኩረት እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል። አንዳንድ ባህሪዎቻችንን በተጋነነ መልኩ እንድንረዳ ሊያደርገን ይችላል። መሠረታዊ ስብዕናችንን ግን ሊለውጠው አይቻለውም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top