ጣዕሞት

በህወሓት እና በኢህአዴግ ላይ ትኩረቱን ያደረገው መጽሐፍ

በሙሉጌታ ገብረህይወት (ፒ.ኤች.ዲ) የተጻፈው LAYING THE PAST TO REST – The EPRDF and the challenges of Ethiopian State-Building የተባለ መጽሐፍ ለህትመት በቃ። በ355 ገፆች በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተፃፈው ይህ መጽሐፍ፤ የታተመው በእንግሊዝ ሀገር ሲ.ኸርስት አሳታሚዎች ለንደን ውስጥ በ2020 እ.አ.አ. (2012 ዓ.ም.) ነው። በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ላቲን አሜሪካ መጽሐፉን የሚያከፋፍለው ደግሞ ኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ ፕረስ ነው። የመጽሐፉ ደራሲ በኢህአዴግ እና በህወሓት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሲሆን፤ የኢህአዴግን ስኬቶች እና ድክመቶች በተብራራ መንገድ ከገለጹ በኋላ፤ እንዴት ባለ መንገድ ድርጅቱ በብረት ከታገዘ ህዝባዊ ትግል ወደ መንግስትነት ሽግግር እንዳደረገ ያስረዳሉ። በመጨረሻም ድርጅቱ በስልጣን በቆየባቸው ከሩብ ክፍለዘመን በሚበልጡ ጊዜያት ምን ዓይነት ስኬቶች እና ድክመቶች እንዳሳየ ያስረዳሉ።

Laying The Past To Rest

የመጽሐፉ የአቀራረብ ቅርፅ በአራት የጊዜ ኡደቶች የተከፈለ ነው። የመጀመሪያው ከ1967 የህወሓት ምስረታ እስከ 1977 የማሌሊት ምስረታ ያለው ዘመን ዚሆን፤ ሁለተኛው ክፍል ከ1977 እስከ 1983 የደርግ መንግስት ውድቀት ድረስ ያለው ዘመን ነው። በሶስተኛው ክፍል ከ1983 እስከ 2004ዓ.ም ያለው የኢህአዴግን መንግስት አካሄድ የተቃኘበት ሲሆን፤ በአራተኛው እና የመጨረሻው ክፍል ደግሞ ከ2004 ዓ.ም. ቀጥሎ ያለውን ዘመን ይዳስሳል።

በመጽሀፉ የገጽ ሽፋን ላይ እንደ አሌክስ ዴዋል፣ ረ/ፕ/ር ሃሪ ቨርሆቨን፣ ፕ/ር ክርስቶፈር ክላፋም፣ ፕ/ር አንድርያስ እሸቴ እና አባይ ጸሃዬ… ያሉ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ስለመፅሃፉ ያላቸውን አስተያየት አስፍረዋል።

ደራሲው የዶክትሬት መመረቂያ ጽሁፋቸውን አዳብረው ነው ለመጽሐፍነት ደረጃ ያበቁት። የመጽሐፉን ማስታወሻነትም ለትግል ጓደኞቻቸው ይኩኖአምላክ ገ/ሚካኤል እና ክንፈ ገብረመድህን አድርገውታል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top