በመአዛ መንግስቴ የተደረሰው “ዘ ሻዶው ኪንግ” የተሰኘው መጽሐፍ፤ በእንግሊዘኛ የታተሙ የልበ-ወለድ መጻህፍት ተወዳድረው በሚሸለሙበት ዘ ቡከርስ ፕራይዝ (The Bookers Prize) የ2013 እጩዎች ላይ ለመካተት በቅቷል።

በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. አሸናፊው የሚታወቀው ይህ ሽልማት፤ እንደ አዘጋጆች አገላለጽ ከሆነ የመአዛ መንግስቴን መጽሐፍ በዘንድሮው የእጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ታውቋልል።
ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዳኞች የሚካፈሉበት ይህ ሽልማት፤ በደራሲያን ዘንድ ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠው ነው። የሽልማቱ የመጨረሻ እጩዎች በመጪው መስከረም 5 2013 ዓ.ም ይታወቃሉ። ዋናው አሸናፊ በጥቅምት 17 2013 ዓ.ም. የ ዘ ቡከርስ ፕራይዝ ሽልማትን እንደሚረከብ ከአዘጋጆቹ ለመረዳት ተችሏል።
የመጽሐፉ መቼት በጣልያን ወረራ ወቅት በነበረው ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥነው ይህ መጽሀፍ፤ ደራሲዋ መአዛ መንግስቴ በልዩ ጥንቃቄ ለአንባቢዎቿ የዘመኑን ታሪካዊ ሁኔታ ሳታዛንፍ ልታቀርብ መቻሏ ሊታወቅ ችሏል።
የመአዛ መንግስቴ መጽሐፍ መታጨቱ እንደተሰማ በእንግሊዝ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ እንኳን ደስ ያለሽ የሚል መግለጫ በትዊተር ገጹ ጽፏል።
