ጣዕሞት

ዲጅታል ህትመቶች

ከዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ ክስተት በኋላ በሐገራችን ከታዩ ለውጦች ውስጥ የሕትመት ውጤቶች የአቀራረብ ለውጥ አንዱ ነው። ከታዳሚዎቻቸው ጋር የወረቀት ሕትመት ግንኙነት የነበራቸው ጋዜጦች እና መጽሔቶች ወረርሽኙን ተከትሎ በኢንተርኔት እና በ‘ሶፍት ኮፒ’ አንባቢዎቻቸውን መድረስ ጀምረዋል። ሁኔታው ችግር የወለደው ቢሆንም ለህትመት ውጤቱ አዲስ ወይም ተጨማሪ ዘውግ እያስተዋወቀ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርክተዋል። እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ሐሳብ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ቁጥራቸው እየጨመረ የሚገኘውን የዲጅታል መጽሔቶች እንደ አብነት ይጠቅሳሉ።

በተለይም በቅርብ ዓመታት ከአጀማመራቸው አንስቶ በሶፍት ኮፒ ለንባብ መድረስ የጀመሩ እየበረከቱ ነው። በአማርኛ ብቻ ሳይሆን ኦሮምኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን ጨምሮ በሶፍት ኮፒ ለንባብ እየበቁ የሚገኙት እነኚህ መጽሔቶች በቃለ መጠይቅ፣ በወግ፣ ቀልድ እና ጨዋታዎች፣ የባለሙያዎች ሙያዊ ምክር፣ ፎቶዎች እና ማስታወቂያዎችን በአምዶቻቸው አካተዋል። መጽሔቶቹ በውስጥ እና በውጭ ከግራፊክስ ቅንብሮቻቸው (ዲዛይን) በጣም ጥሩ የሚባሉ ናቸው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top