ጣዕሞት

የሂሳዊ ትንተና መጽሐፍ

የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ስራዎችን በፍልስፍና መነጽር የሚተነትን የሒስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። “የጸጋዬ ገ/መድኅን ሥራዎች እና ፍልስፍና” የሚል ርዕስ ያለው አዲሱ መጽሐፍ አምስት ምዕራፎች እና 251 ገጾች ያሉት ሲሆን በባለ ቅኔው ስድስት ቴአትሮች እና ሰባት ግጥሞች ላይ በማተኮር በስራዎቹ ውስጥ የሴቶችን ምሰላ (Depiction) ይዳስሳል።

በመጽሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስለ ደራሲው ሕይወት እና የስራ አስተዋጽኦ፤ በሁለተኛው ምዕራፍ የዓለማችን ፈላስፎች ስለ ሴቶች ያንጸባረቋቸውን ሐሳቦች ያነሳል። ከሦስተኛው አስከ አምስተኛው የመጽሐፉ ምዕራፎች ደግሞ የጸጋዬን ሥራዎች ይተነትናል።

በአፍሪካ እና በቀደምት ታሪክ ጥናት (ኢጅፕቶሎጂ)፣ በቲያትር እና በግጥም ስራዎች ላይ የራሱን አሻራ ማሳረፍ ስለቻለው ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ሥራዎች የተሰናዳው አዲሱ መጽሐፍ ለሐገራችን የስነ- ጽሑፍ ትንታኔ አዲስ ነው ተብሎለታል።

ደራሲው ደሳለኝ ስዩም በፍልስፍና የሁለተኛ ዲግሪ ያለው ሲሆን፤ በልዩ ልዩ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ላይ ከአምደኝነት እስከ ዋና አዘጋጅነት ሰርቷል። ወደ ስድስት ያህል የግጥም እና ወጥ ስራዎችን ለህትመት ያበቃ ሲሆን። ሌሎች የትርጉም ሥራዎችም ለንባብ ካደረሳቸው መካከል ናቸው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top