ጣዕሞት

የአስደናቂው ኢትዮጵያዊ ታሪክ

በትውልድ ሃገሩ ኢትዮጵያ የክብሩንና የገናናነቱን ያህል አምብዛም ስለማይታወቀው ‘ማሊክ አምበር’ የሚተርክ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ። ኢትዮጵያዊው የሕንድ ንጉስ ከምን ተነስቶ የት ደረሰ? እንዴት ባለ መንገድ ከባርነት ወደ ንግሥና ተሸጋገረ? የሚሉትን እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚያነሳሳው መጽሐፉ በOmar H.Ali ተጽፎ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በ2016 የታተመ ነው።

መጽሐፉ የማሊክን ዱካ ተከትሎ የጥንታዊውን ዓለም ብዙ ቦታዎች ያስጎበኘናል፤ የህንድን ታሪክ ያስቃኘናል።

ጥቁሮች፣ አፍሪካውያን፣ ኢትዮጽያውያን ወገኖቻችን ከዛሬ 480 ዓመታት በፊት ሰለባ የነበሩበት የባርያ ንግድ ምን ይመስል ነበር?

በምእራባዊ ሕንድ የነበሩት ሱልጣናዊ ግዛቶች ውስጥ ኢትዮጵያውያን በዘመኑ ያበረከቷቸው አስተዋፅዖች ምን ይመስላሉ?

ማሊክ አምባር ከቀንበር እስከ መንበር በተራዘመ ህይወቱ የፖለቲካ ሴራንና የታላላቅ ዐፄዎችን ሰራዊት ወረራ እና ጥቃት እንዴት መከተው?

የሚሉ እና ሌሎችንም አስገራሚና አስተማሪ የሕይወት ጉዞዎቹን ከሐረርጌ፣ ኢትዮጵያ እስከ አህመድናጋር፣ ሕንድ ያስቃኛል።

ማሊክ አምበር በህንድ ስመ ገናና ነው። ማሊክ ጀግና ብቻ አይደለም፤ ሲበዛ ብልህ ነው። ታጅ መሃልን የሰራው የሕንድ ንጉሥ ሻህ ጅሃን አያት አክባር ሳይቀር ተንበርክኮለታል። በ1550 ዎቹ ከሐረርጌ በባርነት ተወስዶ በደቡብ ሕንድ አዛዥ፣ ናዛዥ፣ አንጋሽ መሆን ችሏል። አዳዲስ የሕንድ ከተሞችን መስርቷል። የማይቀረውን ሞት የቀመሰው ኃያልነቱ ሳይከዳው ነው።  

ተርጓሚ ኪዳኔ መካሻ የመጀመሪያ የትርጉም ሥራውን አስመክልቶ ለቀረበለት ጥያቄ

“አስደናቂውን ታሪክ ሳነበው ወደድኩት። ይበልጥ ሳውቀው እና ሲስበኝ ለመተርጎም ተነሳሳሁ” ሲል መልሷል።  

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top