ማዕደ ስንኝ

ደረጃ የሌለው መሰላል

ይሄ ያገሬሰው እኮ፣ መሰላል አወጣጥ ያውቃል
አንዱን እርከን ረግጦ ሲያልፍ፣ ነቅሎ ጉያው ይከታል
ደሞ ቀጣዩን ይረግጣል…
ነቅሎ ጉያው ይከታል…
እንዲህ እንዲያ እያለ ዘልቆ፣ ከዝና በላይ ይወጣል፤
ከጥቅምም በላይ ይሰፍራል…
እንደኮራ እንደተዝናና፣ ቃል ሳይናዘዝ ይሞታል
በቀብሩም ስርአት ላይ
‹‹ደግ፤ ለሰው አሳቢ
ለተቸገረ ደራሽሽ…››
የሚል የህይወት ታሪክ ወግ፣ ይፋ ይነበብለታል።
ከቀን በኋላም ገኖ፣ ሀውልቱ ገዝፎ ይታያል።
ያም የደረጃ እርከን-እንጨት፣ መቃብር አጥሩ ይሆናል!!
እንግዲህ ተከታይ ትውልድ፡-
በአንጋፋው አበሻ መንገድ
ደረጃ በሌለው መሰላል፣ በጥበብ ፍለጋ ተሰደድ!!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top