ማዕደ ስንኝ

የዕለት እንቅልፋችንን ንሳን

በራሳችን ምድር፣ በራሳችን አፈር፣
በራሳችን እርሻ፣ በራሳችን ሞፈር፣
…ግን በሌሎች ቀምበር…
በራሳችን አሐዝ፣ በራሳችን ፊደል፣
በራሳችን እውነት፣ የራሳችን በደል፣
ለራስ መንገር ሲሳን፣ ወግ በሌሎች ልሳን…!!
በራሳችን አንገት፣ በራሳችን ራስ
በራሳችን ፍራሽ፣ በራሳችን ትራስ
በራሳችን ምሽት፣ በራሳችን ሌሊት
በራሳችን አዚም፣ እልምምምምምም…
የኛ ባልሆነ ህልም!
በራሳችን እግዜር፣ በራሳችን እምነት፣
በራሳችን እንባ፣ በራሳችን ጸሎት፣
አሁን እንዲህ ማለት…
አባታችን ሆይ…
“ቆመን የሌሎችን፣ ቀንበር ከመሸከም፣
በሽተኛ ሲሉን፣ ታመን ከመታከም፣
“ድናችኋል” ሲሉን፣ ሳይድን ከማገገም፣
የማናምንበትን፣ ቀን ቀን ከማላዘን፣
ለማይፈታ ህልም፣ ሌሊት ከመባዘን፣
አውራጣት አስይዘን፣ በጣር ከመለፍለፍ፣
ቅዠት ከማንከርፈፍ፣
እንቅልፍ ንሳንና፣ ሌሊት እንኳ እንረፍ!!”

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top