ማዕደ ስንኝ

ኑሮ እና ጣእም

ሙያዬን ታውቃለህ፤ ማጀቴን ታያለህ፤

“እንጀራሽ እንክርዳድ፤ ገበታሽ ጣዕም-አልባ!”

ለምን ትለኛለህ?

በል ዝም-ብለህ ብላ!!

ቸርቻሪ መንግሥታት፤

ሰነፍ ገበሬዎች፤

በዝባዥ ነጋዴዎች፤ በበዙበት ዓለም፤

ጠንካራ ጥርስ እንጂ ቀማሽ ምላስ የለም!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top