ቀዳሚ ቃል

ቀዳሚ ቃል

በትላንትና ውስጥ መጥፎ ነገሮች ብቻ የሉም። ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ በሆኑበት ምቹ አጋጣሚዎች የሞሉትም
አይደለም። ቅልቅል ነው። ሕይወት፡- ከተድላውም ከሀዘኑም፤ ከበጎውም ከመጥፎውም፤ ከቀናውም ከጥመቱም
ያበጀችው ነው። ከትላንት የታሪክ ሰበዛችን ስንመዝ ዛሬአችንን የሚያሳምሩ፣ አሁናችንን የሚያጠናክሩ የምንላቸውን
ብንመርጥ እናተርፋለን። አትራፊዎቹ ግን እኛ ብቻ አንሆንም። ከሁላችንም ጥቃቅን ሙከራዎች ድምር ሐገር ታተርፋለች።
ባለፈ ማንነቱ የማይጋጭ፣ በዛሬ መገዱ የማይቃረን፣ የነገ ብሩህ መዳረሻውን የተለመ ትውልድ የሚኖራት ሐገር አብዝታ
ታተርፋለች።
በዚህ ረገድ ያለውን ክፍተት ለመሙላት በመጣር ላይ የምትገኘው ታዛ መጽሔታችን በቁጥር 32 ዕትሟ ትላንትን ከዛሬ
ጋር የሚያስተሳስሩ ቁምነገሮችን አካታለች። 20 ዓመታት ከማይበልጡት የሐገራችን የኪነጥበብ ጎጆ ሰይጣን ቤት ጀምሮ
በጣሊያን ወረራ ወቅት እስከነበሩ ተጻራሪ ገጽታዎች ድረስ በጥቂት በጥቂቱ ተዳሰውባታል።
በወግ፣ በስነ-ግጥሞች፣ በአጭር ልብወለድ፣ በመጽሐፍ ዳሰሳ፣ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን አንስተናል። ሰለ ወቅታዊዎቹ የኮሮና
ወረርሽኝ እንዲሁም በፖለቲከኞቻችን እና በፖለቲካ ፓርቲዎቻችን እየተስተዋለ ስለሚገኘው ጉዳይ ከታሪክ እና ከባህል
አንጻር የሚኖረውን መልክ የሚያሳይ የውይይት ማጫሪያ ሐሳቦች ሰንዝረናል። የተዘነጉትን ባለ ታሪኮች የሚያስታውሱት
እና ቋሚ ተከታታዮቻችን የምትጠብቁት የፍልስፍና ሐሳቦች በገጻቸው ተሰናድተዋል።
የኮሮና ወረርሽኝን የምንከላከልበትን የጥንቃቄ መንገዶች ሳንዘነጋ፣ ሐገራችን ከገባችበት ቅርቃር የምትወጣበትን
የውይይት እና ለሕግ የመገዛት መርህ ሳንጥስ፣ መልካም መልካሙን ሁሉ የምንሰማበት እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣ።
መልካም ንባብ!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top