ማዕደ ስንኝ

አባይ አለቀሰ!

የሚፈነጥቀው – የገደል ዳር ጢሱ

ሳቅ ነው ስል ከርሜ ለቅሶ ነበር ለሱ

በዘመናት ብሶት ስሜቱ ሲነካ

እምባ እያፈሰሰ ወንዝ ያለቅሳል ለካ

ዶፍ ጭሆት አሰማ ድንገት ደፈረሰ

ምን መርዶ ሰምቶ ነው አባይ አለቀሰለ

አንጋፋው ወንዛችን ምነው አመረረ

እናትን መረዳት – በሱ አልተጀመረ፤

አባይ በልክ እዘን – ራስህን አጽናና

ገና ብዙ ቀሪ አለብህ ፈተና፤

ተደፍተን እናልቅስ!

በቀዬህ የሚያልፈው … ያንተ – የሚመስልህ ያትልቁ ጅረት

ሆኖ ተገኘልህ – የጎረቤት ወረት፣

አገር ተሰባስቦ – ካላገኘ መላ

ወንዜ የምትለው ሊሆን ነው የሌላ፤

ወትሮም ይታወቃል – ህዝብ ክንዱ ሲዝል

                      በባዕድ ይጠቃል

ይቅርና የጁን ያፉን ይነጠቃል፤

መይሳው ቴዎድሮስ – ዮሃንስ መተማ፤

ምን ይል ነበር ዛሬ ይሄን ጉድ ቢሰማ

በጠራራ ፀሐይ በጅህ ያለን ዕንቁ ወንዝ ስታስቀማ

የፈርኦን ግዛት – ውሃ አነሳኝ ብሎ …

    ጦር እንዳይቀሰቅስ

ድፍን ያበሻ ሰው – አባይ ዳርቻ ላይ

    ሂድ ተደፍተህ አልቅስ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top