ከቀንዱም ከሸሆናውም

በኮሮና ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ዝነኞች

ጃፓናዊ ኮመዲያን

ኬን ሺሙራ

የጃፓኑ እውቅ ኮሜዲያን ኬን ሺሙራ በማርች 29 ነበር፤ በተወለደ በ70 ዓመቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቱ ያለፈችው።

የጃዝ-ፈንክ ንጉስ

ማኑ ዲባንጎ

የአፍሪካ ጃዝ-ፈንክ ዝነኛው የሳክስፎን ተጫዋች በማርች 24 ነበር፤ በተወለደ በ86 ዓመቱ ህይወቱ ያለፈው። ማኑ ዲባንጎ በካሜሮን የተወለደ ሲሆን፤ 15 ዓመት ሲሆነው ወደ ፓሪስ አቅንቷል። ከዝነኛ ስራዎቹ መካከል በ1972 የለቀቀው ‹ሶል ማኮሳ› የተሰኘ ዘፈን ያለው ሲሆን፤ ይህም ዘፈኑ በማይክል ጃክሰን ዜማዎች ላይ ሳምፕል ለመሰራት በቅቷል።

ትራምፔት ተጨዋች

ሮኒ

የጃዝ ትራምፔት ተጫዋች የሆነው ሮኒ፤ ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተወለደ በ59 ዓመቱ ህይወቱን አጥቷል። በቅዱስ ዮሴፍ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ህክምናውን ሲከታተል የቆየው ሮኒ፤ በማርች 31 ነበር እየታከመበት ባለ አልጋ ላይ እንዳለ ህይወቱ ሊያልፍ የቻለው።

የተዋንያን የአነጋገር ዘዬ አሰልጣኝ

አንድሪው ጃክ

በኮሮና ህይወቱ ያለፈው አንድሪው ጃክ፤ ተዋናዮችን የአነጋገር ዘዬ በማስተማርና እና በማስጠናት ይታወቃል። አንድሪው በዚህ ሞያው ብዙ ታዋቂ ፊልሞች ላይ የተሳተፈ ሲሆን፤ ከተሳተፈባቸው ስራዎች በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል፡- ስታር ዋርስ፣ ሎርድ ኦፍ ዘ ሪንግ፣ ጋርዲያንስ ኦፍ ዘጋላክሲ፣ ካፒቴን አሜሪካ፣ አቬንጀርስ ወ.ዘ.ተ… ይገኙበታል። በ76 ዓመቱ ያረፈው አንድሪው የሁሎት ልጆች አባት ነበር።

የካንትሪ ሙዚቃ አቀንቃኝ

ጆ ዲፊ

የ90ዎቹ ተወዳጅ የካንትሪ ሙዚቃ አቀንቃኝ ጆ ዲፊ፤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በ61 ዓመቱ አርፏል። ከመሞቱ ከሁለት ቀናት በፊት እየተደረገለት ስላለው ህክምና እና ከበሽታው እንደሚድን ያለውን ተስፋ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፅፎ ነበር።

የእግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንት

ፓፓ ዲዩፍ

የ68 ዓመቱ የቀድሞው የማርሴ ኦሎምፒክስ እግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንት ፓፓ ዲዩፍ፤ በኮሮና ህመም ምክንያት ሁለተኛ ዜግነት ባገኘባት ሴኔጋል በማርች 31፤ ህይወቱ አልፏል።

የሶማልያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር

ሐሰን ሑሴን

የሃገረ ሶማሊያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር ኑር ሐሰን ሑሴን፤ በአፕሪል አንድ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ እያለ፤ በኮሮና በሽታ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

የቡርኪናፋሶ ምክትል ፕሬዝዳንት

ወ/ሮ ሮዝ ማሪ ኮምፓውሬ

ህይወቷ እስካለፈበት ዕለት ድረስ የቡርኪና ፋሶ ፓርላማ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን ስታገለግል የነበረችው ወ/ሮ ሮዝ ማሪ ኮምፓውሬ፤ በኮሮና ህመም ምክንያት ህይወቷ ማለፉን የሃገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ Union for Progress and Change (UPC) አስታውቋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top