ጣዕሞት

ተንቀሳቃሽ ቤተ መጻሕፍት

ለአስገዳጅ ስራ ካልሆነ በስተቀር ከቤት መውጣት በማይመከርበት በዚህ ሰዓት መጻሕፍትን ማንበብ አንዱ ውጤታማ የጊዜ ማሳለፊያ ነው። የንባብ ፍላጎት ቢጨምርም አንባቢያን ያሻቸውን መጻሕፍት እንደልብ ማግኘት አለመቻላው ደግሞ በተግዳሮትነት ይጠቀሳል።

ወጣቱ መጽሐፍ አቅራቢ አንዷለም ይስሀቅ ይባላል። ከኮሮና ቫይረስ ክስተት በኋላ የቀደሙ ደንበኞቹ መጽሐፍትን ይዞላቸው እንዲመጣ በስልክ ሲያዙት ፍላጎታቸውን ለማሟላት ባደረገው እንቅስቃሴ የፈላጊዎች ቁጥር በማሻቀቡ አገልግሎቱን አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኝ ማንኛውም ደዋይ እንዲዳረስ አድርጓል።

“የመኪና አገልግሎትን ከመጀመሬ በፊት በእግሬ እየተዘዋወርኩ እሸጥ ነበር። አሁን ወደ መኪና አድጓል። ደንበኞቼ በ0947488523 ደውለው የሚያዙኝን ማንኛውንም መጽሐፍ ቤታቸው ድረስ አደርሳለሁ።” ሲል ከታዛ መጽሔት ጋር በመበረው ቆይታ ያብራራው ወጣት አንዷለም በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቲያትሪካል አርት ተማሪ እንደነበረም ነግሮናል።

አንዷለም ከመጻሕፍት ንግዱ በተጓዳኝ የራሱን ስራዎች በመጽሐፍ እና በሲዲ አሳትሟል። “የተሰበሩ ሕልሞች” ለሕትመት የበቃ የግጥም ስብስብ ስራው ሲሆን “ናፍቆት የተከለው ሐውልት” የተሰኘ በድምጽ የተዘጋጀ የግጥም ሲዲም አለው። በጋዜጠኝነት እና በስነ-ጽሑፍ ዘርፍ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግም ይታወቃል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top