ጣዕሞት

አወዛጋቢው የታሪክ ትምህርት ሞጁል

በዩንቨርሲቲዎች ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ (Ethiopian history) የተሰኘው የትምህርት መስክ መሰጠት ካቆመ ትንሽ ሰንበት ማለቱን የታዛ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ያነጋገራቸው የታሪክ መምህራን ያረጋግጣሉ። የታሪክ ማስተማሪያው ሁሉን አካታች አይደለም በሚል ሰበብ ለዓመታት የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል በማለም በቅርቡ የተዘጋጀው “የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ታሪክ ማስተማሪያ ሞጁል” በርካታ ምሁራንን በዎንታ እና በአሉታ ሲያከራክር ሰንብቷል።

ከሦስት ሺህ ዓመታት በላይ የዘለቀውን የመንግሥትነት ታሪክ ይንዳል፣ ኢትዮጵያን ከቅኝ ግዛት ጋር የሚያገናኝ ሰነድ ነው፣ የጋራ የሚባለውን ሐገራዊ ታሪክ ያሳንሳል፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን አስተዋጽኦ ደብቋል፣ አሉታዊ የታሪክ ጎኖች ላይ ትኩረት ሰጥቷል፣ ለሴሜቲክ ሕዝቦች ጥላቻ አሳይቷል፣… የሚሉ ጠንካራ ወቀሳዎች ያስተናገደው አዲሱ ሞጁል በሰባት ምዕራፎች እና አንድ መቶ ሰባት ርዕሶች ተገድቦ ስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ከሰሞኑ ተሰምቷል። ሞጁሉ በያዝነው ዓመት ህዳር ወር ላይ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአስተያየት የተላከ ሲሆን፤ የተሰጡ አስተያየቶችን  የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ለማጠናቀር ታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ በአውደ ጥናት ምክክር እንደተደረገበት በመገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል።

 በአውደ ጥናቱ ላይ እንደተገለጸው በቀደመው የሞጁሉ ረቂቅ ላይ ተስተውለዋል የተባሉት ችግሮች  ማስተካከያ የተደረገባቸው ሲሆን በልዩ ልዩ መንገዶች ከተሰበሰበው አስተያየት በመነሳት መካተት ሲገባቸው የተዘለሉ ጉዳዮችም እንዲጨመሩ ተደርጓል።

 የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዳሳወቀው በምሁራኑ ውይይት ተደርጎባቸው ከስምምነት ላይ መድረስ ያልቻሉት የሞጁሉ ክፍሎች በዚህኛው ዕትም ላይ አልተካተቱም። ተቀናሾቹ የታሪክ ሁነቶች በቀጣይ ጊዜያት በሚካሄዱ ጥናቶች እና ውይይቶች ከአንድ እልባት ላይ በሚደርሱበት ጊዜ በሁለተኛው እትም እንዲካተቱ ይደረጋል።

በምሁራኑ ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ የነበረው የታሪክ ማስተማሪያ ሞጁል ለማስተማሪያነት ዝግጁ እንደሆነ በተገለጸበት መድረክ ንግግር ያደረጉት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም

 “የታሪክ ትምህርት ከቀደመው ህዝብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ ልቦናዊ ገፅታዎቻችንን ለመረዳት የሚያስችለን ነው” ብለዋል።

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ10 ጊዜ ተከበረ። የትምህርት ሚንስቴር ከባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር እና ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ ከወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር  ‹‹የቋንቋ መብት፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እና የኢትዮጵያ አፋዊ ቋንቋዎችን ተቋማዊ ማድረግ›› በሚል መሪ ቃል በወርሃ የካቲት ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ የትምህርት ሚንስትር ዲኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ፣ በአዲስ አበባ  ዩንቨርሲቲ የቋንቋ መምህር ፕሮፌሰር ባዬ ይማም በተገኙበት ክብረ በዓል ላይ በመጥፋት ላይ ያሉቋንቋዎችን ለመታደግ በተለያዩ ምሁራን እና ተቋማት ዘንድ ስራዎች እየተሰሩ ነው መባሉን ትምህርት ሚንስቴር ባደረሰን መረጃ አመላክቷል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top