ማዕደ ስንኝ

ነጩ ፈረስ ማን ነው?

ከዓድዋ ጦር ማግስት በቆሰለ አርበኛ የተማረከ ሰው
እልፍኝ ውስጥ ሆኖ እንደዚህ ጠየቀ
“ሲወጋ፣ ሲያዋጋ፣ ሲያጠቃን የነበር
ነጩ ፈረስ የታል?”
ይኔ… ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል?
ነጩ ፈረስማ…!
ጦርነት ስትለፍፍ ድንበር ስትገፋ
መሬት ስትቆፍር ዱካ ስታሰፋ
ይቅርብህ እያለ ምክር ያቀረበው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው።
ነጩ ፈረስማ…!
አይገባውም ብለህ አልተማረም ብለህ
እንደ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣ እንግሊዝ ተመኝተህ
አፍሪቃ ምድር ላይ ግዛት ልያዝ ብለህ
ሰውነቱን ንቀህ በጥቁረቱ ስቀህ
በብረት ካቴና አስረህ ያደማኸው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው!
ነጩ ፈረስማ…!
ከኤርትራ ምድር መቀሌ አምባላጌ
ማን አለብኝ ብለህ ስትገፋ ስትወረው
አይገባውም ብለህ ውጫሌ ምድር ላይ
በቃላት ውስጥ መርዝ ለውሰህ ሰጥተኸው
እውነቱን ተርጉሞ “እምቢ!” ያለህ ሰው ነው!
ነጩ ፈረስ የታል? ነጩ ፈረስ የታል?
ይሔ ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል?
ነጩ ፈረስማ…!

ያንተን ስልጡን ሐገር የሰለጠነን ሰው የዘመነውን ጦር
የታጠቀን አረር መትረየስ ሳይፈራ መድፉን ቁብ ሳይሰጠው
እምቢ ላገር ብሎ የተዋጋህ ሰው ነው!
ነጩ ፈረስማ… ነጩ ፈረስማ…!
ተደፈርኩኝ ብሎ
ከሰሜን ደቡብ ጫፍ ምእራብ ምስራቅ ነቅሎ
የከፋ ዘመኑን የሆድ ስሞታውን
ከመደፈር በታች አቅልሎ አሳንሶ
ግማሹ በጸሎት ጨፌውን ነስንሶ
ግማሹ በወኔ ጎፈሬውን ነቅሶ
እንደ ነብር ዝቶ እንዳንበሳ አግስቶ
በምታ ነጋሪት ሁሉም ባንድ ከቶ
ዓድዋ ምድር ላይ በጦር በጎራዴ የተጋፈጠህ ሰው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው!
ነጩ ፈረስ የታል…?
ይኼ… ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል!?
ነጩ ፈረስማ…!
የጣይቱን ምክር ያባ መላን መላ
እሺ ብሎ ሰምቶ በልቡ እያብላላ
የቴጌዋን ምክር ትእዛዝ አክብሮ
የምትጠጣውን ምንጭ ከቦ ተቆጣጥሮ

ውሃ ውሃ ያሰኘህ ደንቆሮ ነው ያልከው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው!
ነጩ ፈረስማ…!
እምነት በልቡ አስሮ
አንድነት አክብሮ
ፈጣሪውን ሰምቶ ከራሱ ጋር ታርቆ
ጦር እና ጎራዴ ባጭር ባጭር ታጥቆ
ሆ… ብሎ ሲመጣ ሆ… በለህ ተኩሰህ
ሀገር ትኑር ባለ ሀገሩ ላይ ገድለህ
እሳት የሚተፋ ባሩዱ ሲያልቅብህ
በቀደመው ጥይት ቆስሎ በማረከህ
ደሙ እየፈሰሰ ውሃ ጠጣ ያለህ
አይገባውም ብለህ ንቀህ የደፈርከው
ንቀቱን ዋ…ጥ አርጎ አንተን የማረከው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው!
ነጩ ፈረስማ…
መቀሌ አምባላጌ ዶጋመድ አድርጎህ
በዓድዋ ተራሮች እፍረት አከናንቦህ
ባቆሰልከው ጀግና ድፍረት እጅ ሰጥቶህ
ማተብ ባታከብርም ማተብ እያሳየህ
እልፍኝ አስገብቶ አብልቶ ያጠጣህ
ሮምን የጣለ ዓለም ያከበረው
የጥቁር ህዝብ ኩራት መመኪያ የሆነው
ለማረከው ግብር ጥሎ ያጠገበው
የዓድዋው ጀግና የቴዎድሮስ ልጅ
የዮሐንስ ወንድም የጣይቱ ባሏ
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያልከው
የጥቁር ሕዝብ ኩራት ንጉስ ምኒልክ ነው።
ነጩ ፈረስ ማን ነው?

ቅፅ 03 ቁጥር 29 | የካቲት 2012 ዓ.ም. 5

የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ዘንድሮ
ለ124ኛ ጊዜ ይከበራል። ስለድሉና ጦርነቱ በርካታ
የታሪክ ተመራማሪዎችና የጥበብ ሰዎች ብዙ
ብለውለታል። የዓድዋ ድል ዓለም የመሰከረለት፣
ለአፍሪካ ነጻነት አብነት የሆነ፣ የኢትዮጵያውያን
ብሔራዊ ኩራት ነው። የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ
የተነገረውን ለመድገም፣ ወይም በታሪክ ጥናት
ውስጥ አዲስ ግኝትና ንባብ ለማስተዋወቅ
አይደለም። ከዓድዋ ድል ባሻገር ያሉ ቅድመ
ዓድዋ፣ በጦርነቱ ወቅትና ድህረ-ዓድዋ እስከ
ዘመናችን ድረስ ያሉ የአገራዊ አንድነት፣ የያኔው
የኢትዮጵያዊ አልሸነፍ ባይነት ስነ-ልቡናዎችን እና
ከትውልድ ወደትውልድ ሊተላለፉ የሚገባቸውን
የድል ሰንሰለት ወይም ድሮችን መመልከት ነው።

ቅድመ ዓድዋ
ስለ ቅድመ ዓድዋ ስናስብ ሦስት መሠረታዊ
ነገሮችን መመልከት ያስፈልጋል። እነሱም
አገራዊ፣ አካባቢያዊ (የአፍሪካዊያን ገጠመኝ)፣
እና ዓለማቀፋዊ (የአውሮፓውያን ትኩረት እና
ፍላጎቶች በአፍሪካ) የሚሉት ናቸው። እነዚህን
ሦስቱን ጉዳዮች መመርመር የዘመኑን መንፈስ
ለመፈተሽ ይረዳናል። የዓድዋን ድል ሙሉ
ይዘት ለመገንዘብ የሚያስችሉን ቁልፍ መረጃዎች
የሚገኙትም እነዚህ ሦስቱን የትኩረት ምሕዋሮች
ይዘን ስንመረምር ነው። እያንዳንዳቸውን በየተራ
በአጭሩ እንመልከት።
ሀ/ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ፡- ዓለም አቀፋዊ
ሁኔታ የሚለው በዋናነት በቅኝ ግዛት ተቀዳሚ
ተሳትፎ የነበራቸውን አውሮፓውያን ሁኔታ
የሚመለከት ነው። ይህም አውሮፓውያን
በአፍሪካ የነበራቸውን ተግባራዊ ተሳትፎ፣
ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ዕይታና ምኞት እንዲሁም
ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦችን የሚመለከት ነው።
በኢኮኖሚያዊ ሁናቴ አፍሪካውያን በአውሮፓውያን
በኩል እጅግ በጣም ኋላ ቀሮችና ያልሰለጠኑ
ተደርገው ተስለዋል። በዚህም የሃይማኖት
ሚሺነሪዎቻቸውን እና ሰላዮቻቸውን በመላክ
የአፍሪካውያንን ስነ-ልቡና ለመስለብ ሙከራ
ተደርጓል። ከዚህ የከፋው ደግሞ ፈላስፎቻቸው
ስለአፍሪካውያን የነበራቸው አመለካከት ነው።
እንደ ካንት እና ሄግል ያሉ ጫና ፈጣሪ ፈላስፎች
አፍሪካውያን ለዓለም ታሪክ ምንም ዓይነት
አስተዋጾ ያላደረጉ በጫካ ውስጥ የሚኖሩና
የሥልጣኔ ጮራ ያልዳሰሳቸው አድርገው
ስለዋቸዋል። በዚህም ምክንያት ቀደም ሲል በባሪያ
ንግድ፣ ኋላ ደግሞ በቅኝ ግዛት አፍሪካውያንን
መቆጣጠር ቀላል እንደሆነ አውሮፓውያን
አምነዋል። ከኢኮኖሚ አንጻር ደግሞ የአፍሪካ
ተፈጥሮ ሃብት ለአውሮፓውያን የኢንዱስትሪ
እድገት አማራጭ የሌለው ግብዓት ነበር። እነዚህ

በቀጥታ ካየነው አንዳንዶቹ ጎረቤት አገራት ከቅኝ
ገዥዎቻቸው ጋር በማበር እና በመመሳጠር፤
ሌሎቹ የቅኝ ግዛት ኃይሎች ከኢትዮጵያ
ጋር ነበራቸው ብለው በገመቱት ግንኙነት
አንድምታ ኢትዮጵያን ለመውጋት ሲሰለፉ ነበር።

ምናልባትም ማንም አፍሪካዊ ከቅኝ ግዛት እጣ-
ፈንታ ሊያመልጥ አይችልም የሚል አስተሳሰብ

የዘመኑ ገዥ መንፈስ ነበር ማለት ይቻላል።
በተዘዋዋሪ ደግሞ የያኔዋ ኢትዮጵያ
የነበራትን ድንበር በግልጽ ለማስቀመጥ
እንደ ፈተና የሆነባት፤ ቀደምት አፍሪካውያን
የየራሳቸው ጥንታዊ ድንበር አለመያዛቸው ነው።
በዚህም ኢትዮጵያ “ከኢትዮጵያ ውጭ” ካሉ ቅኝ
ግዛቶች ጋር የተዋዋለቻቸው የድንበር ውሎች
አልፎ አልፎ በቅኝ ገዥዎች መልካም ፈቃድ
ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ ተገድዳለች። በዚህም
የውጫሌው ውል፣ በሶማሌ በኩል ከእንግሊዝ
ጋር ያደረገቻቸው ውሎች፣ እንዲሁም ከፈረንሳይ
ጋር በጅቡቲ በኩል የተደረጉ ውሎች አወዛጋቢ
ነበሩ። በተለይ የውጫሌ ውልና የመረብ-ምላሽ
ጉዳይ እስከዘመናችን ድረስ አወዛጋቢ ሆኖ ብዙ
ዋጋ ያስከፈለን ነው።
የነዚህ አካባቢያዊና ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎች
ድምር ውጤት፤ ኢትዮጵያ ለምታደርገው
ከዓድዋ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top