ጥበብ በታሪክ ገፅ

ማን ምን አለ?

ማን ምን አለ?

አፍሪካ ከቅኝ አገዛዝ ነጻ እንድትወጣ ታላቅ ተጋድሎ ካደረጉ መሪዎች መካከል የጋናው ኩዋሜ ኑክሀሩማ ከፊት ተሰላፊዎች ውስጥ አንዱ ናቸው። የደቡብ አፍሪካው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ታቦ ሙምቤኪ ደግሞ በፓን አፍሪካ ላይ ባላቸው ጠንካራ አቋም እና ከአፓርታይድ አገዛዝ በኋላ በነበረው ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ላይ ባላቸው ዋነኛ ተሳትፎ ይታወቃሉ።

 ሁለቱ መሪዎች በፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚያገናኝ ተመሳሳይ ታሪክ አላቸው። ኩዋሚ ኑክሩሀማ የአፍሪካ አንድነትን ከመሰረቱ መሪዎች መካከል ሲሆኑ፤ ታቦ ሙምቤኪ ደግሞ በአፍሪካ ኅብረት ተሳትፎ ላይ ተሳትፈዋል። ሁለቱ ታላላቅ መሪዎች ስለ ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል ዓድዋ በተለያየ ጊዜ የተናገሯቸውን በነጻ ትርጓሜ እንዲህ አሰናድተነዋል።

 “ዓድዋ ላይ በተገኘው ድል ኢትዮጵያ ለሁሉም አፍሪካውያን ብሄራዊ አንድነት እና ሕብረት ቅኝ ገዢን ለመታገል አስፈላጊ መሆናቸውን አስተምራለች።” ታቦ ሙምቤኪ

 ዛሬ እዚህ የዓድዋን 121ኛ ዓመት በማስመልከት በሚከበረው በዓል ላይ እንድገኝ ግብዣ ስላደረጉልኝ በቅድሚያ፤ ልክ ከዛሬ ሁለት ቀን በፊት በዓድዋ ተገኝቼ የማይረሳ አከባበር በማሳለፍ፤ እጅጉን የሚጠቅመንን የፓንአፍሪካ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሰራ ሲበሰር እንዳደረግኩት ሁሉ፤ አዘጋጆችን ለማመስገን እወዳለሁ።

 የእኛ በእዚህ መገኘት፤አህጉራችን በሙሉ የሚያውቀውን ከክፍለ ዘመን በፊት በ1888 ዓ.ም. የዓድዋ ጦርነት የተገኘው ድል በእርግጥም የኢትዮጵያም የአፍሪካም ድል ለመሆኑ፤ ማረጋገጫ ምስክር ለመሆን ነው።

በተጨማሪም የእኛ በዚህ መገኘት፤ በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፣ በንግሥት ጣይቱ፣ በራስ አሉላ፣ በራስ መኮንን እና ሌሎች ታላላቅ ኢትዮጵያውያን እየተመራ ታላቅ ጀብዱ ለፈፀመው አፍሪካዊ ሠራዊት፤ ያለንን ክብር በድጋሚ ለመግለፅ ነው። ወራሪውን የጣሊያን ጦር በማሸነፍ አህጉራችን ከቅኝ አገዛዝ፣ ኢምፔሪያሊዝም፣ እና ለነፃነት በሚደረግ ትግል፤ መጨረሻው ድል እንደሆነ፤ ቀድመን በተስፋ እንድናውቅ በዓድዋ ድል ዜና አብስረውናል።

 ድሉ በአህጉሩ ዙሪያ ያሉ አፍሪካውያን ለኢትዮጵያ ያላቸውን የክብር ዕይታ ትክክለኛነት ያረጋገጠ ነው። በተጨማሪም ለሺህ ዓመታት በሉዓላዊነት የኖረው ህዝብ የሚፈጥርባቸውን ተነሳሽነት በዲያስፖራው ዘንድም ልዩ ቦታ እንዲሰጠው አድርጓል።

 በዚህ ምክንያት ነው፤ ብዙ አፍሪካዊያን ኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚሉትን ስሞች እንደተመሳሳይ በመጠቀም በተለዋዋጭነት የሚጠቀሙት።

 ይህንን በተመለከተ ዛሬ፤ እዚህ አብራችሁኝ ያላችሁ አብዛኞቻችሁ እንደምታውቁት፤ በሮበርት አሌክሳንደር ያንግ የተፃፈው እና በ1829 ዓ.ም. እ.አ.አ. በኒውዮርክ የታተመው “The Ethiopian Manifesto: Issued in Defence of the Black  Man’s Rights in the Scale of Universal Freedom” በሚገባ ገልፆታል ይህ ስሜትን የሚነካ ማኒፌስቶ ለአፍሪካዊያን ባሮች ነፃ መውጣትን በአሜሪካ ለሚገኙ ጥቁሮች መብት መከበርም ስሜታዊ ቀረቤታ ያለው ነው።

 ሮበርት ያንግ “The Ethiopian Manifesto” ያለበት ምክንያት ሁለት ነበር።

አንድ፡- መላውን የአፍሪካዊያንን እና ጥቁር ህዝቦችን ‘ኢትዮጵያውያን’ ብሎ መጥቀሱ፤ ሌላው ደግሞ የአፍሪካውያንን ነፃ የመውጣት እና ፍትሕን የማግኘት ፍላጎት ከኢትዮጵያ ጋር እንዲያያዝ ማድረጉ ነበር።

 በዚህም፤ ሮበርት ያንግ The Ethiopian Manifesto” ለአፍሪካውያን እና በመላው በአሜሪካ ለሚገኝ ጥቁር ህዝብ የተላለፈውን መልእክት በተከታዩ ገለጻ ይጀምረዋል።

 “ኢትዮጵያዊያን! የተባረከ ኃይል በውስጣችን ስላለ፤ እንደሰው በውስጣችን ለእኛ ብቻ እና ስለኛ ተብሎ የተሰራ የሚያስተሳስረን ነገር አለ፤ እንደሰው ….”

ቀጠለናም፡ “ስለዚህም እኛ፤ ለአላማችን መሳካት ስንል፤ ይህንን …. የሁላችንም ትኩረት የሚያስፈልግውን ይህንን ታላቅ ማኒፌስቶ፤ ከኢትዮጵያም ይሁን ከአፍሪካ ህዝቦች ትውልድ ያለን፤ የእናንተ ደህና መሆን ለእኛ ታላቅ እና መነሳሻ ምክንያት ሆኖን የራሳችንን ድርሻ ለመወጣት የሚመራን ይሆናል።” እያለ የበለጠ እንዲህ ሲል ፃፈ፡ “ኢትዮጵያዊያን! ህሊናችሁን ለምክንያት ክፍት አድርጉ… እወቁ፤ ከዚያም አሁን ባላችሁበት እና በቆማችሁበት ሁኔታ፤ እየኖራችሁበት ባላችሁት ሃገር ውስጥ ባለ በየትኛውም መንግሥት ስር ሆናችሁ፤ እኛ ተመችቷችሁ እና እየታገላችሁ ነገር ግን የማስተዳደር መብት እንዲኖራችሁ እንፈልጋለን። እኛ እዚህ የምናወራው ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ነው…

 “ወድቀንና ተዋርደን በሚያሳዝን ሁኔታ የበታች ሆኗል የእኛ ዘር፤ እኛ ስንረከበው ደግሞ ከበታችነትም ወርዶ ባርነት ውስጥ ነው ስላለ፤ ራሱን ከጣለበት አዘቅት ልናነሳውና፤ የሰውነት መብት እንዳለው ልናሰርፅበት፤ ነው የእኛ ጽሑፎች ዋና ፍላጎት…

 “እነዚህ ጽሑፎች፤ የአስተሳሰቤን ምልከታ ለሌሎች የሚያሳዩትን፤ ከነጮች ወይም ከጥቁሮች የወሰድኩት አይደለም፤ ከወንሞቼ እና ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን እንጂ፤ እሱም ሌላ ሳይሆን ውስጤን በአንዳች ሰማያዊ ኃይል በማጠንከር በአግባቡ እንድወስን የሚረዳኝ ነው። ከዚህ እሳቤ በመነሳትም ነው መብቴን የማውቀው፤ ከእናቱ ማህፀን የወጣ ሁሉ ነፃ ሆኖ መፈጠሩን፤ ማንም የሰው አካል ስወለድ ያገኘሁትን በአምላክ ስፈጠር የተለገሰኝ ስጦታ መብቴን የሚነጥቀኝ ማነው?…

 “አይሆንም! እኔ በራሴ ሰው ነኝ፤ እናም አንደሰው እኖራለሁ፤ እንደሰውም እሞታለሁ። እኔ ነፃ ሆኜ ስወለድ በአምላኬ የተሰጠኝ ነፃነት ስላለ፤ በተመሳሳይ ሁኔታም ሁሉም ከጥቁር የሚወለድ ወንድ እና ሴትም ይሄ መብት እንዳለው ልገልፅና ላረጋግጥ እወዳለሁ።  “ሰው፤ ነጭ ሰው፣ ጥቁር ሰው ወይም ኢትዮጵያውያን፤ ለእናንተ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን እናገራለሁ።

“በደንብ አድምጡኝ። እናም ቃሎቼንም ትኩረት ስጡ። እወቁ ወደእናንተ የሚደርሱት እኚህ ቃላት ነብያዊ እውነታ ያላቸው ምክንያታዊ ድምጾች ናቸው። ጊዜው በእጃችሁ ላይ እንደሆነ በብዙ ምልክቶች ስታዩ፤ አምላክ የክፉ ሰዎችን ስራ እንደሚመለከት እወቁ፤ የመራራ አገዛዝ ለቅሶዎች፤ ከእነዚህ ደስታ-አልባ ሰዎች፤ በባርነት ቀንበር እየተጨቆኑ ሲገዙ የኖሩት፤ ወደ ቅዱስነት ከፍ ከፍ ብለዋል።

 በኒውዮርክ ከሚገኝ በባርነት ውስጥ ባለ ሰባኪ ከ188 ዓመታት በፊት የተገለፀው “The Ethiopian Manifesto” የሚለው አስተሳሰብ ነው፤ ፓን-አፍሪካኒዝም እና አፍሪካዊ ብሄርተኝነት እንዲወለድና፤ ሁሉም አፍሪካዊ በዲያስፖራ ያለውም ተባብሮ በ19ኛው እና 20ኛው ክፍለዘመን ለነፃነት እና ፀረ-ባርነት እንዲታገል ያደረጉት እና በእርግጥም ይህ የአፍሪካ ብሄርተኝነት ነው፤ በመጀመሪያ Ethiopianism (ኢትዮጵያኒዝም) ተብሎ የሚታወቀው።

  ለምሳሌ በ1906 ዓ.ም. እ.አ.አ. መጨረሻ፤ በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ስር በደቡብ አፍሪካ የናታል ክፍለግዛትዋና አስተዳዳሪ፤ የኤ.ኤን.ሲ. (African National Congress (ANC)) የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የነበረውን ጆን ዱቤ “ራሱን ኢትዮጵያዊ እያለ ስለሚጠራ ክትትል ይደረግበት” ብሏል በእርግጥ በተመሳሳይ ዓመት፤ የኤ.ኤን.ሲ. ቀዳሚ የነበረው፤ የደቡብ አፍሪካውያን ኮንግረስ (the South African Native Congress) እንዲህ ብሏል“ኢትዮጵያኒዝም የእድገት ምልክት ነው፤ የአፍሪካ ነዋሪዎች ከአውሮፓውያን ሥልጣኔ ጋር ሲገናኙ የተፈጠረ፤ ራሱን በማኅበራዊ፣ በሃይማኖታዊ እና በኢኮኖሚያዊ የሚገልጥ በሁሉም መስክ ስሜት የሚሰጥ ነው”

ይሄ የኢትዮጵያኒዝም አገላለፅ በአውሮፓውያን ከተቋቋሙ ሚሽነሪ ቤተክርስቲያኖች አፈንግጠው በመውጣት የራሳቸውን ቤተክርስቲያን ባቋቋሙ አፍሪካውያን ክርስቲያኖች ዘንድ የተለመደ ነበር። በዚህም ራሳቸውን ከሚሽነሪዎቹ በመለየት የራሳቸው ነፃ የሆነ የእምነት ተቋም ለመገንባት ቻሉ።

ይህንን በተመለከተ ከመጀመሪያዎቹ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የሃይማኖት እንቅስቃሴን ከመሩ ሰዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ሪቨራንድ ጄ.ጂ. ዣባ (Rev J.G. Xaba) ከዓድዋ  ማን ምን አለ?  የካቲት 2012 ዓ.ም. ድል ከአንድ ዓመት በኋላ በ1897 እንዳለው፡- “የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዋንኛ ዓላማ፤ ክርስትናን ማስፋፋት እና በመላው የአፍሪካ አህጉር ውስጥ የአንድነት ስሜት እንዲኖር ማድረግ ነው…”

ከዚህ ጋር ተያይዞ ደቡብ አፍሪካዊው ጳጳስ ማሉሲ ምፑምሏና (Malusi Mpumlwana) እንዲህ ብለዋል።

 “በቤተክርስቲያን የነበረው የኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ሃይማኖታዊ ብሄርተኛ እንቅስቃሴ ነው። ወደአምላክ የሚያስኬደው መንገድ በአውሮፓውያን ቅኝ አገዛዝ ስር መሆን የለበትም ይላል። ከመጽሐፍቅዱስ ውስጥም “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሄር ትዘረጋለች” የሚለውን በመጥቀስ። የኢትዮጵያ ክርስትና ታሪክ ከአውሮፓውያን ቅኝ አገዛዝ ጋር ግንኙነት አልነበረውም። በእኔ እምነት ዓድዋ ላይ የቅኝ ገዢ ወራሪዎችን በማሸነፍ ላይ ባለ ንግር መሰረቱን ያደረገ ነው።

 “በተመሳሳይ መንፈስም፤ በደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ኅብረትን የፈጠረ የመጀመሪያው እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፤ የኢትዮጵያ እንቅስቃሴ የደቡብ አፍሪካውያንን ተበታትኖ በየቦታውና በየብሄሩ ይደረግ የነበረውን የፀረ-ቅኝ-አገዛዝ ትግል ዘመን እና በተደራጀ መልኩ በኅብረት ይደረግ የነበረውን ዘመናዊ ሃገራዊ የቅኝ-አገዛዝ ትግል ዘመንን የሚያገናኝ ድልድይ ሆኖ አገልግሏል። ስለዚህ ኢትዮጵያ እንደሃገር ተባብረን ቅኝ-አገዛዝን እንድንታገል፣ ለክብራችን እሴቶች እንድንቆም፣ ሰብአዊ መብቶቻችንን ከሃገራዊ አንድነታችን ጋር አስተሳስረን እንድንታገል፤ መነሳሻ ምክንያት ሆናናለች።”

 ለዚህም ነው በሐገራቸውም ሆነ በውጭ የሚኖሩ አፍሪካዊያን ራሳቸውን ከኢትዮጵያ ጋር ያስተሳሰሩት፤ የነጻነት ጥያቄያቸውንም ያገናኙት። የዓድዋ ድል በመላው አፍሪካ ለነበረው የኢትዮጵያኒዝም መጀመር ታላቅ አበርክቶ ያጎናፀፈ አንፀባራቂ ድል ነበር።

 ይሄ መተማመንም የተረጋገጠው የኢምፔርያሊስት ኃይሎች በፌብሯሪ 26፣1885 ዓ.ም. አፍሪካን ለመቀራመት በበርሊን ኮንፈረንስ በተስማሙ በ11ኛው ዓመት በተገኘው የዓድዋ ድል ነው።

የዓድዋ ድል በዚህ ምክንያት ለሁሉም አፍሪካውያን በማያባራው የነፃነት ትግላቸው እና ፀረ-ቅኝ-አገዛዝ ምከታቸው፤ ምንም እንኳ በመጀመሪያ ቢሸነፉም፤ ፈጠነም ዘገየም ማሸነፋቸው እንደማይቀር በማረጋገጥ የበርሊኑን ስምምነት ፉርሽ ያደረገ ነው።

 ዓድዋ ላይ በተገኘው ድል ኢትዮጵያ ለሁሉም አፍሪካውያን ብሄራዊ አንድነት እና ሕብረት ቅኝ ገዢን ለመታገል አስፈላጊ መሆናቸውን አስተምራለች። በመላው ሃገሪቷ የሚገኙ ህዝቦች በመተባበር ነፃነታቸውን በማስጠበቅ የራሳቸውን ዕጣፈንታ በራሳቸው ለመወሰን ደማቸውን ሊያፈሱ እንደሚገባ በዓድዋው ጦርነት ምሳሌ ሆናለች።

በተጨማሪም ድሉ በኢምፔሪያሊስት ኃይሎች አፍሪካውያን የበታች እና ኋላቀር እንደሆኑ የሚገልፀውን ንግር ድምጥማጡን አጥፍቶታል። የሰውነት ክብር እና ከሁሉም ሃገራት ጋር እኩል መሆናቸውንም አስምሮበታል።

 እዚህ ላይ እኔ የምናገረው፤ ለመስዋዕትነት ዝግጁ ሆኖ ረጅም ርቀት የተጓዘው የኢትዮጵያ ገበሬ በውጊያው ሎጂስቲክስ በሟሟላት ጦርነቱን ስለደገፈው፣ መሳሪያ ባነገቡት ወታደሮችም ስላለው አበርክቶ፣ ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቀውን የጣሊያን  ጦር “ድል ወይም ሞት” ብለው በባዶ እግራቸው ስለተጋፈጡት ነው።

 የዓድዋ ድል በተጨማሪም ያሰመረበት፤ ጠላትን በአስተሳሰብ በመብለጥ ክህሎት እና አርበኝነት የተሞላ አመራር ያለውን ወሳን ጠቀሜታ ብቻ ሳይሆን፤ በፖለቲካው እና በዲፕሎማሲያዊ ፈተናዎች በኩል ያለውን ብቃት ጭምር ነው።

 በመጨረሻም፤ የዓድዋ ድል ለሁሉም አፍሪካውያን ያስተላለፈው መልእክት፤ ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ብለው መጥራታቸው ልክ መሆኑን ማረጋጥ ነው። ምክንያቱም ‘አውሮፓውያን አይሸነፉም’ የሚለውን የያኔው አስተሳሰብ ስህተት መሆኑን በተግባር አስመስክረዋልና። እናም የተባበረች አፍሪካና አፍሪካውያን አሸናፊዎች ናቸው!

 በተጨማሪም፤ በንግሥት ጣይቱ ከጦርነቱ በፊትና በኋላ እንዲሁም በጦርነቱ ጊዜ ባለው የሴቶች ተሳትፎ እና ድርሻ፤ ስለሴቶች ነፃነት እና የፆታ እኩልነትም የዓድዋ ድል የራሱን መልእክት አስተላልፏል።

የዓድዋ ድል ለሁሉም አፍሪካዊ አስፈላጊ ነበር። ምክንያቱም የቅኝ ገዢዎችን የበላይነት መንፈስ የናደና ያደከመ፤ እንዲሁም በጭቆና ውስጥ የነበሩትን አፍሪካውያን በራስ መተማመናቸውን በመመለስ መንፈሳዊ ጥንካሬን ያላበሰ ታሪክ በመሆኑ ነው።

የጆሃንስበርግ ጋዜጣ የሆነው ዘ ስታር (The Star) በማርች5 1896 ዓ.ም. እትሙ፤ ከዓድዋው ድል ከጥቂት ቀናት በኋላ መሆኑ ነው፤ እንዲህ ፅፏል።

 “ታላቅ እና አውዳሚ የሆነው ሽንፈት… የሚያመላክተው አውሮፓውያን ባለፉት ዓመታት በነባሩ ህዝብ የደረሰባቸውን ታላቅ ምከታ ነው… በአፍሪካ ባሉ ሌሎች ነጭ ህዝቦች ይሄ በፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም… ይሄ ታላቅ ሽንፈት ምናልባትም ሥልጣኔ ወደ አፍሪካ እንዳይገባ ጊዜያዊ መሰናክል መሆኑ አያጠራጥርም”

በተመሳሳይ ቀን፤ የደቡብ አፍሪካው ኬፕ አርጉስ ጋዜጣ (Cape Argus newspaper) ዋና አዘጋጅ እንዲህ አለ።

 “ጣሊያን በአቢሲኒያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ በማይጥም አጨራረስም ቢሆን ልታቆም ይገባል… ምኒልክ በየትኛውም ዓይነት መንገድ ሊሰበር ይገባል… አሁን ባጋጠማት ችግር ለጣሊያን ሐዘኔታችንን እንገልፃለን።”

 ሁለቱም ጋዜጦች የሚወክሉት በቅኝ-አገዛዝ ስር በነበረችው ደቡብ አፍሪካ ይኖሩ የነበሩ የነጭ ሰፋሪዎችን አመለካከት ነው።

እንደሚጠበቀው ከላይ የጠቀስኳቸውን ጽሑፎች፤ የተጨቆኑት ጥቁሮች የሚያነቡት የዓድዋ ድል “የሚያመላክተው አውሮፓውያን ባለፉት ዓመታት በነባሩ ህዝብ የደረሰባቸውን ታላቅ ምከታ ነው…” የሚለውን እና “ምኒልክ መቼም ቢሆን እንደማይሸነፍ” ብለው ነው።

ከደቡብ አፍሪካ ጋዜጦች ጋር ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያለው የታይምስ ኦፍ ለንደን (The Times of London) ጋዜጣ አምደኛ ከፓሪስ እንደሚከተለው ጽፏል።

 “ማንም እዚህ ያለ… አይመኘውም፤ የሰለጠነው ህዝብ ተዋርዶ አቢሲኒያዎች እንዲሳካላቸው፤ ነገር ግን የተለየ ሃሳብ እና ዓላማ መያዝም ይቻላል፤ በጀግና ግን ጨካኝና ኋላቀር ጦር ፊት ለፊት ተዋግተው በተሸነፉት ላይ ክፉውን ማሰብ ግን ልክ አይደለም”

 ያም ሆኖ ግን የዛው ጋዜጣ አዘጋጅ፤ የተሻለ ምክንያተዊ እና ሚዛናዊ ጽሑፉ

“በምኒልክ አማካኝነት የደረሰው የጣሊያን ሽንፈት በታሪክ ውስጥ ለዘላለም የማይረሳ ነው። ድሉ እስካሁን ድረስ እንዳልሰለጠኑ አድርገን የምንመለከታቸውን አፍሪካውያን ስሜት የሚያነሳሳ ነው… የምኒልክ ድል የመላው አፍሪካ ድል ነው። ይህን መሰል ገለፃ ወደፊት ጠንካራ ማስረጃ ይሆናል። በነፋስ አክናፎች በረሃውን አቋርጦ ከጫፍ እስከጫፍ ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ይወራል። ወደፊትም ቢሆን፤ አፍሪካ አውሮፓን ማሸነፏ በመታወቁ፤ ራሳቸውን የመከላከል ስሜት በአፍሪካውያን ዘንድ በመፍጠር የሚሊዮኖች አፍሪካውያን አስተሳሰብን የሚያሳድግ ነው። በጣሊያናውያን ሽንፈት መደሰቱ ምቾት አይሰጥም። ይሄ ሽንፈት የእኛም የሌሎችም ነው… የቅኝ ገዢዋ የዛሬዋ አውሮፓ ሽንፈት ነው። የነገዋ አውሮፓ ሽንፈትም ጭምር ነው።”

 በማርች 4 1896 ዓ.ም. ትምህርቱ፤ የተከበረ ፈረንሳዊ የታሪክ ምሁር እንዲህ አለ።

“የጣሊያኖች በምኒልክ መሸነፍ በአዕምሯችው ላትረሱ ልታስቀምጡት የሚገባ ታሪካዊ ክስተት ነው። ይህ የአፍሪካ መነቃቃት ነው፤ እስካሁን ኋላቀር ብለን እየጠራናቸው በአውሮፓውያን ተዋርደው የተገዙት የአፍሪካውያን ሃገራት ከእንቅልፍ መነቃቃት ምልክት ነው። መርሳት የሌለብን ነገር፤ ዛሬ ኋላቀር እያልን የምንጠራቸው ሃገሮች ባሉበት ቦታ በጥንት ጊዜ ታላላቅ ስልጣኔዎች የነበሩባቸው ቦታዎች መሆናቸው ነው፤ በተለይም ኢትዮጵያ በጥንቱ ጊዜ በታላቅ ሥልጣኔዋ እና በሃብቷ የምትታወቅ ሃገር ነበረች።”

 እነዚህ የተለያዩ አመለካከቶች በአውሮፓ ጋዜጦች ላይ በሚሰራጩበት ጊዜ፤ በጣሊያን ውስጥ ደግሞ የዓድዋን ሽንፈት ተከትሎ የመጣ አስፈላጊ እንቅስቃሴ ነበረ። ይህ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በኢምፔርያሊስቶች የሚደረገውን የአፍሪካ ወረራ የሚቃወም ነበር።

 ከእነዚህም ጥቂቶቹ በ1910 በታተመ መፅሃፍ ላይ ተገልፀው ነበር። ይሄ 11ኛው ቅፅ “Memoirs of (Baroness) Bertha Von Suttner: The Records of an Eventful Life.”የተባለ በበርታ ቮን ሱተነር የተፃፈ መጽሐፍ ነው፡፡

 እሷ በዚህ መፅሐፍ ከዘገበቻቸው ውስጥ፡ “በጣሊያን ውስጥ ህዝቡ የጦርነቶችን መቀጠል በመቃወም ሰልፍ ያደርግ ነበር። ሰልፉን ይጠሩ የነበሩት ግን ሪፐበረሊካን እና ሶሻሊስቶች ስለነበሩ በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ጫና ይደረግባቸው ነበር። በፌብሯሪ 29 ትልቅ የእራት ግብዣ በአፍሪካ የሚደረገውን ጦርነት በመቃወም የተደረገ ሲሆን፤ በግዛት አስተዳደሩ ግን ሊከለከል ችሏል። እናም በቀጣዩ ቀን አስከፊው የዓድዋ ሽንፈት ዜና ተሰማ። ስምንት ሺህ ሰዎች እንደሞቱ፣ የቀሩት እንደተማረኩ፣ ሁለት ጄነራሎች መገደላቸው… ባጭሩ እጅግ በጣም አስደንጋጭ ያልተለመደ ሐዘን በጣሊያን ውስጥ፤ በመላው አውሮፓም ከፍ ያለ ሐዘኔታ ለጣሊያን ነበረ…

 “እንቅስቃሴው (በአፍሪካ የሚደረገው የተቃውሞ እንቅስቃሴ) ወደብዙ ቦታዎች መዳረስ ጀመረ። በሮም፣ በቱሪን፣ በሚላን፣ በቦሎኛ፣ እና በፓውዳ ሴቶች እየተደራጁ ስለሰላም የሚሰብክ ሰነድ ላይ ፊርማ እያስፈረሙ ለፓርላማ አስገቡ። ብዙ ሺህ ሰዎች የፈረሙባቸው ነበሩ ሰነዶቹ።”

 “ስለዚህ ሴቶቹ ንቁ ነበሩ። ህዝቡን የወከሉት ሴቶች ኃይል የተሞሉ ነበሩ። ባሎቻቸውን እና  38 ቅፅ 03 ቁጥር 29 | የካቲት 2012 ዓ.ም.  ቅፅ 03 ቁጥር 29 | የካቲት 2012 ዓ.ም. 39  ልጆቻቸውን ወደ አውደ-ውጊያ ሊወስዱ የተዘጋጁ መኪኖችን መንገድ በመዝጋት፤ ባቡሮችን ደግሞ ሐዲዳቸው ላይ በመተኛት ሊያስቆሟቸው ችለዋል።”

“በተመሳሳይም በጦር ካምፖች ውስጥ፤ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደአፍሪካ በመስደድ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ነበር። ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ወታደሮችም ከጦር ካምፖቹ እየወጡ ወደየሃገራቸው ይመለሱ ነበር።”

 “በመላው ሃገሪቱ የነበረው ውዝግብ፣ ጦርነት እና ሰላም በሚባሉ ሁለት ፅንፎች ላይ የነበረ ግብግብ ነው…

 “ንጉሱ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ክሪስፒን ለማቆየት ፍላጎት ነበረው፤ ነገር ግን በመላው ሃገሪቱ የነበረው ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ክርስፒን አሸነፈው።

“አዲስ ሚኒስቴር ተሾመ። ሩዲኒ… አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነ

 “የክሪስፒ ማስታወሻዎችና ስለጦርነቱ የሚያወሩ ጋዜጦች ስለቸሰላም በሚያወሩ ሃሳቦች ላይ ያፈጠጠ ተቃውሞ ነበራቸው። ‘ዓድዋን እንበቀል’፣ ‘ጦርነት እስከመጨረሻ ድረስ!’ እና ወዲያውኑ ከዓድዋው ሽንፈት በኋላ ቢሆኑ ተሰሚነትን ያገኙ የነበሩ ሃሳቦች ነበሩ “ሆኖም በበለጠ ጩኸት እና በፍጥነት ልክ ያልሆነው ጦርነት እንዳይቀጥል የሚቃወሙ ድምፆች እየተበራከቱ መጡ። እንቅስቃሴዎቹ እና ተቃውሞዎቹ የተደራጁ ነበሩ፤ በዛም ምክንያት ስኬታማ ነበሩ። ቲዎዶሮ ሞኔታ እንደነገረኝ ሁሉም ነገር በዚህ አቅጣጫ እንዲሄድ ፍላጎቶች ነበሩ። ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሩዲኒ ትልቅ ድል ነበረ፤ ጦርነቱ እንዲቀጥል አይፈልግም ነበርና “የጣሊያኖች በአፍሪካ ውስጥ መሸነፍ ያሳምመኛል። ነገር ግን በአጠቃላይ ጥሩ ትምህርት ነበር። እኔ ከክሪስፒ ቀጥሎ መሪ ብሆን ኖሮ ያለምንም ማመንታት “ጣሊያን ትልቅ ጥቃት በመፈፀሟ የሚገባትን ቅጣት አግኝታለች። ጥቃቱን የበለጠ አናበላሸው፤ ሌሎች ከዚህ የሚበልጡ የሚሰሩ ስራዎች አሉን። ጣሊያንም ከዚህ በኋላ ለሰላም ጠንክራ ትሰራለች” እል ነበር።”

 በዚህ ምክንያት የዓድዋው ድል ሌላኛውን መልእክት አስተላለፈ “ከተራው የኢምፔሪያሊስት ሃገራት ህዝብ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ መያዝ እንደሚችሉና አብረው መስራት እንደሚችሉ፤ ፀባቸው ፖሊሲና ፕሮግራም ከሚያወጡት ከኢምፔሪያሊስት ሃገራት ኤሊቶች ጋር እንደሆነ” በዚህ ግንዛቤ መሰረት ነበር፤ የዓድዋ ድል ከ1896 ቀጥሎ ባሉ ጥቂት አስርት ዓመታት  ላይ በአውሮፓ ውስጥ ፀረ-ቅኝ-አገዛዝ እና ፀረ- አፓርታይድ እንቅስቃሴዎች እንዲበራከቱ  ምክንያት በመሆኑ ጠቃሚ የሆነው። በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ፀረ-አፓርታይድ እና የቬትናምን ጦርነት የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎች የተበራከቱት፤ ኢትዮጵያ በዓድዋ ላይ አሸንፋ ለመላው ዓለም ምሳሌ ለመሆን በመቻሏ ነው።

ለሁሉም አፍሪካውን ባለው ታሪካዊ ቦታ ምክንያት፤ እና በተለይም በዓድዋው ድል የተነሳ፤ ኢትዮጵያ ወደመጀመሪያው በ1900 ዓ.ም. እ.አ.አ. ወደተካሄደው የፓንአፍሪካን ኮንፈረንስ ግብዣ ተደረገላት። በዝግጅቱ ታዋቂ ፓንአፍሪካኒስቶች ነበሩ። W.E.B. du Bois (ዱ ቦይ) አስገራሚ ንግግር አደረገ፤ የ20ኛው ክፍለዘመን ችግር ከቆዳ ቀለም ጋር የተያያዘ ችግር እንደሆነም ተናገረ።

 ሁላችንም እንደምናውቀው ምኒልክ ራሱን  በአፍሪካዊ ወክሎ በስብሰባው ተካፍሏል፤ ነገር ግን ከአፍሪካ ዲያስፖራ ነበር የተወከለው፤ ከሄይቲ የመጣው ቤኒቶ ሲለቬን ነበር ኢትዮጵያን ወክሎ በኮንፈረንሱ የተሳተፈው።

 ቤኒቶ ሲልቬን ከምኒልክ የመወከል ክብር ያገኘበት ምክንያት በዓለማችን ለመጀመሪያዋ በጥቁሮች በ1804 ለተመሰረተው ሪፐብሊክ ክብር ለመስጠት ነው። የአፍሪካ ተወላጅ የሆኑ የሃይቲ ነዋሪዎች ከስፔኖች፣ እንግሊዞች፣ እና ፈረንሳዮች ጋር ተዋግተው ድል ለማድረግ ስለቻሉ ነበር ሪፐብሊኩን ለመመስረት የቻሉት።

 በዚህም እሳቤ ነበር በዓለም ዙሪያ ባሉ አፍሪካውያን ዘንድ ኢትዮጵያ በያዘችው ቦታ ምክንያት፤ ከዓድዋው ጦርነት በኋላ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለአፍሪካ ነፃነት የሚታገሉትን ታጋዮች በመወከል የፓን አፍሪካ ኅብረት የክብር ፕሬዝዳንት የሚለውን ትልቅ ሹመት የተሰጣቸው።

 ከሁለት ቀናት በፊት የተከበረውን የዓድዋ ድል በማስመልከት፤ ዛሬ እዚህ የተሰበሰብነው በኢትዮጵያውያን እና በአፍሪካውያን ታላቅ ዲስፕሊን የታነፀ ሠራዊት በወራሪ የአውሮፓ ኃይሎች ላይ ያገኘውን ድል ለማስታወስ ነው።

 አብዛኛዎቹ የእኛ የአፍሪካ የተከበሩ መሪዎቻችን፤ በዓድዋ ላይ ለተዋጉት ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ክብር ደጋግሞ በማውራት፤ አፍሪካዊ የአብዮት መንፈሳቸው እነሱ ለነፃነት እንዲታገሉ እንዴት እንዳነሳሳቸው ያስረዳሉ።

 ይህን በተመለከተ ምርጡ የአፍሪካ አርበኛ የጋናው ክዋሜ ንኩሩማ፤ ያኔ በለንደን እንግሊዝ ተቀምጦ እያለ፤ በ1936 የተፈፀመውን የጣሊያን ወረራ በኢትዮጵያ ላይ በተመለከተ እንዲህ ብሏል፡

“ያኔ በዛ ሰዓት ሁሉም የለንደን ነዋሪ በእኔ ላይ ጦርነት ያወጀ ያህል ነበር የተሰማኝ። ለቀጣይ ጥቂት ደቂቃዎች በእያንዳንዱ ሰው ፊት ላይ አተኩሬ ከማየት ውጪ ምንም አላደረግኩም። እነዚህ ሰዎች ስለቅኝ-አገዛዝ አስከፊነት ይረዱ ይሆን ስል አሰብኩ። ይህንን ዓይነት ሲስተም ሲወገድ የራሴን ድርሻ የምወጣበት ያ ቀን እንዲመጣ ጸሎት አደረግኩ። ብሔርተኝነቴ ወደፊት ገፋፋኝ፤ የምመኘውን ለማሳካት ገሃናምም ቢሆን ለመሄድ ፈቃደኛ ነበርኩ።”  

ከብዙ ጊዜ በኋላ፤ ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ብሏል

 “ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በሚወርርበት ጊዜ አስራ ሰባት ዓመቴ ነበር። ያ ወረራ ልቤን ወረራውን ብቻ ሳይሆን ፋሺዝምንም በጠቅላላ እንድጠላ ያደረገኝ ነበር።… ኢትዮጵያ በሃሳቤ ውስጥ ሁሌም ልዩ ቦታ ያላት ናት። ወደ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ መጓዝ ተደምሮ ከሚሰጠኝ ደስታ ይልቅ፤ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ እደሰታለሁ። ኢትዮጵያን ስጎበኝ አፍሪካዊ ለመሆኔ ምክንያት የሆነኝን የጥንት ማንነቴን ያየሁ ያህል ይሰማኛል። ንጉሠ ነገሥቱን ኃይለሥላሴን ማግኘት በራሱ፤ ከታሪክ ጋር እጅ እንደመጨባበጥ ያለ ስሜት ይሰጣል።”

Former South African President Nelson Mandela smiles for photographers after a meeting with actor Tim Robbins at Mandela’s home in Johannesburg September 22, 2005. Robbins is currently in South Africa filming. REUTERS/Mike Hutchings – RTRP1WF

አሁን ሁላችንም አፍሪካውያን በጋራ ራሳችንን ጥያቄ የምንጠይቅበት ሰዓት ላይ ነን።እንደምን ባለ ጉዳይ ላይ ነው በስምምነት እጅ ተጨባብጠን በመስማማት የዓድዋ ድል ከዛሬ 121 ዓመታት ከተራመደበት እርምጃ በላይ በመራመድ ለውጥ ልናመጣ የምንችለው?

በዚህ እሳቤ እኔም እንደማምነው ሁላችንም በአፍሪካ ኅብረት የተስማማንበት፤ ሁለት ስትራቴጂያዊ ስራዎች ከፊታችን አሉ። የአፍሪካዊያንን አንድነት ማረጋገጥ እና የአፍሪካን  ህዳሴ ህልም ማሳካት እንደማስበው አሁን ባለንበት ጊዜ ይመስለኛል ከዓድዋ ድል ልንማራቸው በምንችላቸው ነጥቦች ላይ ያለንን ሃሳብ ማንፀባረቅ የምንችለው። በሁሉም ኢትዮጵያውያን ትብብር የዓድዋው ድል እንደሰመረው ሁሉ፤ አንዱ ልንማረው የሚገባን ብሄራዊ አንድነት ኖሮን፣ በተራማጅ ራዕዮች ስትራቴጂያዊ ዓላማዎቻችንን ለማሳካት መሰረታዊ ሁነቶችን መፍጠር እንዳለብን ነው። በዚህ እውነታም እነዚህ ስትራቴጂያዊ ግቦች ከአህጉራችን ጋር በአጠቃላይ የተጎዳኙ ሊሆኑ ይገባል። ይሄ ማለት በእርግጠኝነት፤ ሁላችንም ሃገሮቻችንን አስተባብረን እነዚህ ስትራቴጂያዊ ግቦች እንዲሳኩ በጋራ መስራት አለብን።

የዚህ ሁሉ ትርጉም ሁላችንም በጋራ ሆነን በመስራት በዓድዋ ለተገኘው ድል ያለንን ክብር በውጤት እንግለፅ፤ የሁላችንም ሃገሮች እያንዳንዳቸውና አህጉራችንም በሙሉ በአንድነት ስትራቴጂያዊ ግቦቹን ለማሳካት እንስራ።

 ሁለተኛው ከዓድዋ ድል የምንማረው ትምህርት፤ ልናሳካቸው ለምንፈልገው ስትራቴጂያዊ ግቦች የተሟላና በቂ ዝግጅት በማድረግ በስርዓት ወደምንፈልገው ስኬት መጓዝ እንዳለብን ነው። እኔ እርግጠኛ ነኝ እዚህ ያላችሁት በዓድዋው ድል ጊዜ የነበሩ የፖለቲካ፣ ሎጂስቲክ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ዝግጅቶች ድሉ እንዲሳካ ያደረጉትን አስተዋፅኦ እንደምታውቁ።

ሦስተኛው ትምህርት ከዓድዋ የምንማረው ብዬ የማስበው እኔ፤ በትግል ስለሆነ ስትራቴጂያዊ ግቦቻችንን የምናሳካው፤ ስለዚህ እኛም እንቅፋት ሲያጋጥመን ለመታገልና ተገቢውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆን እንዳለብን ነው።

 በዚህ እሳቤ አሁንም በድጋሚ፤ መቶ ሺህ የሚሆን ጠንካራ ሠራዊት በብዙ ወራት ለመገንባት በኢትዮጵያ ገበሬዎች የተከፈለውን መስዋእትነት ላስታውሳችሁ። ይህም ዘመናዊ ትጥቅ የታጠቀውን የአውሮፓ ጦር ለመዋጋትና ራሳቸውን መስዋእት ለማድረግ ወደጦርነቱ የገቡትን ወታደሮችንም ይጨምራል።

 እርግጠኛ ሆኜ አራተኛው ከዓድዋ ድል የምንማረው ትምህርት፤ አህጉሪቷ እና ሃገራችን የሚፈልጉትን በመርህ፣ በቆራጥነት እና የእኔነት በሚሰማው አመራር ሰፊውን የአፍሪካ ህዝብ ማስተባበር እንዳለብን ነው።

 ይህንን በተመለከተ ምንም ጥርጥር የለኝም ምን ያህል በንጉሥ ዳግማዊ ምኒልክ የሚመራው ጦር፤ በጀግንነት እና በቆራጥነት በሚመሩት የጦር ሰዎች እንደተመራ፤ ንግሥት ጣይቱ እና ሌሎችም፤ ስኬታማ የሆነ ትግል በማድረግ ጣሊያንን በማሸነፍ የሃገራቸውንም ነፃነት አስጠብቀዋል።

ላለፈው ግማሽ ሰዓት እዚህ ላላችሁት ለተከበራችሁ እንግዶች ንግግር የማድረግ ዕድል ነበረኝ። እዚህ ላሉ ኢትዮጵያውያን እህቶቼ እና ወንድሞቼ ኢትዮጵያ ላበረከተችው ታላቅ አስተዋፅኦ ክብር መስጠት እንዳለብን አውቃለሁ። ለብዙ ክፍለዘመናት፤ አፍሪካ ምን ማሳካት እንደምትችል ታሪኳ የሚያነሳሳ ነውና።

 በእነዚህ ክፍለዘመናት ኢትዮጵያ ሉአላዊትየአፍሪካ ሃገር በመሆን ከሌሎች በመለየት፤ ከአሜሪካ፣ ከጣሊያን፣ ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ እና ከራሺያ ጋር ህጋዊ ዲፐሎማሲያዊ ግንኙነት መስርታለች። እንደ አንድ ነፃ አፍሪካዊት ሃገር ነፃነቷን ለማስጠበቅ በዓላም የሚታወቅ ተጋድሎ አድርጋለች። ከዓድዋ ድል በፊት በነበሩት ጦርነቶችም ይህንን አስመስክራለች፤ በንጉሥ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ስር፤ እና በንጉሥ ዮሃንስ 4ኛ ስር ለምሳሌ ከእንግሊዝ፣ ግብፅ እና ጣሊያን ጋር።

 አስቀድሜ እንዳልኩት፤ ኢትዮጵያ አፍሪካውያን ያልሙት የነበረውን ለማሳካት በመቻሏ ምክንያት፤ አፍሪካውያን እና በዲያስፖራው ያሉትም ጭምር ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ እያሉ ሲጠሩ በኩራት ነበር። በትግል የነበራቸው የጋራ ፍላጎትም ኢትዮጵያኒዝም ተብሎ ተጠራ። 

ሁላችንም እንደምናውቀው፤ በፀረ-ቅኝ- አገዛዝ ሃሳባቸው ምክንያት የተሰባሰቡት  የ19ኛው ክፍለዘመን ቤተክርስቲያኖች ራሳቸውን ኢትዮጵያውያን እያሉ ይጠራሉ። ምንም እንኳ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር በክፍለዘመናት የሚለያይ ታሪክ የነበራቸው ቢሆንም፤ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ከ68ቱ መጻሕፍት ያውቁ ነበር

– በእሱም ምክንያት በእየሩሳሌም ቤተመቅደስ ስር ነገስታት ስጦታዎችን አመጡ

– ልዑላን ከግብፅ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያም እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች ለማለት የምፈልገው፤ እስካሁን ከኢትዮጵያ ጋር አያይዤ ያልኩትና፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጠቀስኳቸው ጥቅሶች፤ በዛሬዎቹ ኢትዮጵያውያን ላይ የተለየ የኃላፊነት ጫና እንደሚያሳድሩ ነው። ይህም እናንተ የእኔ ኢትዮጵያዊ እና አፍሪካዊ እህቶቼ እና ወንድሞቼ፤ የተለየና የተከበረ ኃላፊነት አለባችሁ። በታሪካችሁ ያለውን ታላቅነት እና ጨዋነት የአሁኑ ድርጊታችሁ እንዲገልፀው፤ እውነተኛ የአፍሪካ ተወካዮች የአፍሪካ አህጉር እና በዲያስፖራ ያሉት አፍሪካውያን ምኞት ከግብ የምታደርሱ እናንተ ናችሁና፤

ለማጠናቀቅ ያህል፤ አስረግጬ መናገር የምፈልገው አህጉሪቱ በጠቅላላና ኢትዮጵያ የዓድዋ ድልን ያለማቋረጥ በማክበር፤ ሁሉንም ተራማጅ ስትራቴጂያዊ ግቦቻችን እንድናሳካ ተነሳሽነት በመፍጠር፤ በራስ መተማመናችንም እንዲገነባ፤

በተመሳሳይ ለመናገር የምፈልገው እነዚህ ስትራቴጂያዊ ግቦቻችንን ለማሳካት፤ በቅድሚያ ስንነሳ ወደትንንሽ እና ሊያዙ፣ ሊጨበጡ ወደሚችሉ ስራዎች እንቀይራቸው። ሁለተኛ ከዓድዋ ድል በተማርነው መሰረት እነዚህን ስራዎች ለማሳካት በወኔ ተግተን እንስራ።

 በዚህም ታሪካዊ ከ121 ዓመታት በፊት የነበረ የዓድዋ ድል፤ በተግባር በመቀጠል እንደ ጅምሩ የተነሳሽነት መንፈሳችን ምንጭ በመሆን፤ የአፍሪካን ህዝቦች ለሙሉ ነፃነት እንዲያበቃን ይሁን። እናም የአፍሪካ ህዳሴም ይሳካል!

 አመሰግናለሁ!!

(ታቦ ምቤኪ የዓድዋ ድልን 121ኛ መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በየካቲት 26፣ 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ንግግር)

“ለድሉ ዋነኛ ተጠቃሽ የሀገሪቱ ሕዝቦች መካከል የነበረው እንደ ብረት የጠነከረ አንድነት ነው።” ኩዋሚ ኑኩሩሀማ

ወርሀ መጋቢት 1896 የዓለም ሕዝቦችን ቀልብ የገዛ ኩነት የተስተናገደበት፣ ለኢትዮጵያ ልዩ ታሪካዊ ወቅት ነው። ኢትዮጵያውያን ባህር አቋርጦ የመጣውን ፋሽስት ጣልያን በአስደናቂ ሁኔታ አሳፍረው መልሰውታል።

የታሪክ ሊቁ ዶናልድ ሌቪን እንዲህ ብሏል  “የጥቁር አፍሪካዊቷ ሀገር ኢትዮጵያ ገድል፤ አውሮጳውያን በአፍሪቃ ላይ በነበራቸው ገናና ታሪክ ውስጥ እንደ ጉልላት የሚቆጠር ነው።የዓድዋ ድልን ስናስብ ኢትዮጵያውያን የእናት ሀገራቸውን ነፃነት ለማስጠበቅ የከፈሉት ታላቅ መስዋዕትነት ይታሰበናል።

ዓድዋ ለነገ መልካምነት በአንድ ዓላማ የተሰለፉበት የትግል አውዳቸው መሆኑን ያሉኑ ትውልድመረዳት ይኖርበታል። አፍሪቃ የራሷን ታሪክ መጻፍ ብሎም ማጎልበት ከሻተች የዓድዋን መርህ የመከተል ግዴታ ይኖርባታል። ድሉ የፀረ ቀኝ ግዛት ትግል ቀንዲል በመሆን ለተጨቆኑ እና ተስፋ ላጡ ወገኖችሁሉ አነቃቂ መንፈስን ዘርቷል። ዘውዴ ገብረሥላሴ የአድዋን ታላቅነት የዘከሩት በዚሁ መልክ ነው፤ “ይህ ድል በአውሮጳውያን ሰማይ ላይ የጭንቀት ድባብን ሲያነግሥ፣ በአንፃሩ በአፍሪቃ እና በእስያ በቅኝ ገዢዎች ሥር ለሚማቅቁት ሕዝቦች የተስፋ ውጋጋን ፈንጥቋል።”

 ታዋቂው የታሪክ ሊቅ እና የፓን አፍሪቃኒዝም አቀንቃኝ ደብሊው ኢቢ ዱባይስ፣ ስለ ዓድዋ ይህንን ሐሳብ ሰንዝሯል፤ “በቀኝ ግዛት ሥር ያሉ ሌሎች የአፍሪቃ ሀገሮች ዓድዋን እንደ ሞዴል በመውሰድ ለነጻነታቸው ብርቱ ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ነጻነትን ለድርድር እንደማይቀርብ በተግባር ማሳየት አለባቸው።

 የዓድዋ ድልበባርነት ውስጥ ለሚማቅቁ የአፍሪቃውያን ሕዝቦች በወኔ ስንቅነት ከማገልገሉ በተጨማሪ የፓን-አፍሪቃ እንቅስቃሴ እንዲጎለብት፣ የአፍሪቃ ኅብረት እንዲመሠረት የነበረው አስተዋፅኦ የላቀ ነው።

 ቅኝ ግዛት የሰው ልጅን ክብር ወደ እንስሳ ዝቅ የሚያደርገውርግ ስርአት ነው። ቅኝ ግዛት ነጭ አውፓውያንን የበላይጥቁር ሕዝቦች የበታች ማድረግን የወጠነ የሴራ ስርአት ነው። መሰሪው ተልእኮ ዓድዋን ተከትለው በተቀጣጠሉ አመጾች ተበጥሷል። ድብቅ ተልእኳቸውን አንግበው የአፍሪካን ምድር የረገጡት አውሮፓውያንአፍሪካን ማሰልጠን እና ማልማት የሚል ፕሮፖጋንዳቸውን ተገን አድርገዋል።

የቀኝ ገዢዎቹ ጉባኤ በጀርመን በርሊን በ1884-85 መካሄዱ ይታወቃል። ውሳኔው ኃያላኑ ሳይጋጩ አፍሪቃን መቀራመትእንዲቻላቸው ያቀደ ነው። አፍሪቃዊያን ሀገራቸውን ከቅኝ ገዢዎች ቀምበር ለማላቀቅ፣ ነጻነታቸውን ለማስመለስ፣… ውድ ሕይወታቸወን አልሰሰቱም። አልጄራዊያን ለ17 ዓመታት የፈረንሳይ ቅኝ ገዢዎችን በብርቱ ታግለዋል። እስልምናን ለአርበኝነታቸው እንደ ትግል ስልት ተጠቅመውበታል።ይሁን እንጂ፤ የሰለጠነ መሳሪያን እስከ አፍንጫው የታጠቀንየነጭ ወራሪ ኃይልን መመከት የሚያስችል ኃይል አላጎለበቱም።

የሱዳን ተዋጊዎች በአሞዱርማን የእንግሊዝን ቅኝ አገዛዝ ለመጣልታግለዋል። ለዚህም በ1898 ሱዳናዊያን የ11000 ተዋጊዎችን ሕይወት ገበሩ። በተቃራኒው ወራሪ ወገን የሞተው ግን 49 ወታደር ብቻ ነበር። በጄነራል ኪችነር የሚመራው የእንግሊዝ ኃይልዘመናዊውን አውቶማቲክ መሳሪያ በመታጠቁ ብዙ መስዋእትነት አስከፍሏል። እንደ ሳሞራ ቱሬ ገለጻ ወደ 30000 የሚጠጉ ፈረሰኛ ወታደሮችየፈረንሳይ ቅኝ ገዢዎችን ለ16 ዓመታት ተፋልመዋል። ይህ ወራሪዎች የእግር እሳት ለአፍሪቃዊያን ደግሞ ኩራት የነበረው የነጻነት ፋኖ በ1900 በጋቦን ተይዞ እዛው በግዞት ላይ እንዳለ ሊሞት ችሏል።

ሌሎች የነጻነት ተጋድሎዎችን በተመለከተ  የንድቤሉ ሕዝብ በዝምቧቤ፣ በ1896 በጋና የአንሳቲ ሕዝብ፣ በ1900 የናሚቢያ ተፋላሚዎች፣ በ1904 የማጂ ተፋላሚዎች፣ በታንዛኒያ በ 1905-07 የነበሩት የፀረ ቅኝ ገዢዎች ትግል የሚጠቀሱ ናቸው።

 የ20ኛው ክፍለ ዘመን የፀረ ቅኝ ግዛት ከሚጠቀሱት መካከል የኬንያዊያን የነጻነተ እንቅስቃሴ፣ ከ1961-74 የነበሩት የጸረ ቅኝ ገዢዎች ትግል የሚጠቀሱ ናቸው።

 የ20ኛው ክፍል ዘመን የፀረ ቅኝ ግዛት ከሚጠቀሱት መካከል የኬንያዊያን የነጻነት እንቅስቃሴ፣ ከ1961-74 በዙምቧቤ እና በሞዛምቢክ የተካሄደው ጦርነት፣ እንዲሁም በአንጎላ፣ በጊኒቢሳዎ፣ በከንቨርዲ የነበሩት ንቅናቄዎች፣ በጉልህ የሚጠቀሱ ናቸው።

 ነገር ግን ኢትዮጵያ የቀኝ ገዢ ኃይሎችን ተዋግ ተው ያሸነፉ ብቸኛ ሕዝቦች ናቸው። ኢትዮጵያ ባልተለመደ መልኩ ከወራሪው ኃይል ጋር ግንባር ለግንባር ገጥመው በማሸነፍ ነጻነታቸውን እውን ማድረግ ችለዋል።ለድሉዋነኛ ተጠቃሽ በሀገሪቱ ሕዝቦች መካከል የነበረው እንደ ብረት የጠነከረ አንድነት ነው።

ቨርጂንያሊጆኮብስ ዓድዋን ለአፍሪቃ የሚያበረክተው ፋይዳ በሦስት ዘርፍ ከፍሎ አስቀምጦታል፤ “ኢትዮጵያ በቅድሚያ ቅኝ ገዢዎችን በምን መልኩ መታገል እንደሚቻል ትምህርት ሰጥታ አልፋለች፤ ሌላው እንደ ተራራ በገዘፈ የራስ መተማመን መንፈስ በወራሪ የነጭ ኃይል ፊት ታግላ የጣለች አፍሪቃዊያን ሕዝቦች ኩራት ነች፣ በመጨረሻም ኢትዮጵያ በአፍሪቃዊያን ዘንድ ዝንተ ዓለም የምትወሳ የነጻነት ቀንዲል እንደሆነች ትኖራለች።”

አብዛኛዎቹ የአፍሪቃ ሀገራት ነጻነታቸውን ባገኙ ማግስት አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ በተለያየ ቅርፅ ለሰንደቃቸው መለዮ አድርገው ወስደውታል። ከአፍሪቃ ውጪ ባሉ ዓለማት የካረቢያን የዘር ግንድ ባላቸው በብሩክሊን፣ በኒውዮርክ፣ በቶሮንቶ፣ በካናዳ፣ በለንደን፣ በሚያሚ በፍሎሪዳ፣ በዲትሮይት፣ በሚቺጋን፣ በፓርት ኦፍ ስፔን፣ በትሪኒዳድ እና ቶባጎ ይህ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ከፍ ተደርጎ ይውለበለባል።

 ወደ ሠላሳ የሚጠጉ የአፍሪቃ እና ካረቢያን ሀገራት ሦስቱን የኢትዮጵያ ቀለማት ለመለያቸው ለመጠቀም የበቁት በአገጣሚ ሳይሆን ኢትዮጵያን የነጻነታቸው ተምሳሌት አድርገው በመውሰዳቸው ነው።

 የጊኒተቀዳሚ መሪ አህመድ ሴኮቱሬ “ኢትዮጵያውያን ታላቅ አፍሪቃውያን ናቸው፤ ነጻነታቸውን በጀግንነት ታግለው አስጠብቀዋል፤ ለሌሎች አፍሪቃዊያንም መንገዱን አመላክተዋል። አፓርታይድን የመለሰየከፋ የጭቆና ስርአት የታገሉት ባለ ታሪክ ኔልሴን ማንዴላ ኢትዮጵያ የአፍሪቃ ኩራት መሆኗን መስክረዋል። ዓድዋ ትውልዶች ያወረሰው ታላቅ ኩራትን ነው። ኢትዮጵያውያን የዘመኑን ሥልጡን የውሮጳ ወራሪ ኃይልዓድዋ ላይ ማሸነፍ የቻሉት በቂ ዝግጅት እና የጠነከረ አንድነት ስለነበራቸው ነው።

ታላቁ ዓድዋ የአፍሪቃዊያንን ቅኝ ገዢዎች ወሽመጥ በጥሷል። በርካካታ ሕዝቦች ለነፃነታቸው እንዲታገሉ አነሳስቷል።አፍሪቃውያን በዚህ ዘመን በነጻነት እና በሰላም ለመኖራቸው ዋስትና ነው። ይህም ዓድዋ በጊዜ ማእቀፍ እንዳይወሰን ያደርገዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top