ጥበብ በታሪክ ገፅ

አልፍሬድ በርንሃርድ ኖቤል ማን ነው?

ስዉዲናዊ የንግድ ሰዉ  ኬሚስት ኢንጅነር እና ተለያዩ ግኝቶች ፈጣሪ ነዉ። እ.ኤ.አ ከጥቅምት 21፣ 1833 እስከ ታህሳስ 10፣ 1896 ድረስ ኖሯል። ለቤተሰቡ ሦስተኛ ልጅ ነው። የኢኒጂነሪንግ መሰረታዊ ንድፈ ሃሳቦችን ስቶክሆልም በሚገኘዉ የሮያል ኢንስቲቲዉሽን ኦፍ ቴክኖሎጂ አባል ከነበረዉ አባቱ የወረሰዉ በለጋ እድሜዉ እንደነበር ይነገርለታል። 

ከኢንጅነር አባቱ ኢማኑኤል ኖቤል ከእናቱ ካሎራይና ኖቤል የተወለደዉ አልፍሬድ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖርበት ከተማ እ.ኤ.አ በ1837 ወደ ሴንት ፒተርስበርግ አቀና። ሥራ አልሳካ ያለው አባቱ ኢማኑኤል አየሩንም ከተማውንም ልቀይር በሚል ማረፊያውን ፒተርስበርግ ከተማ አደረገ። በርንሃርድ ኖቤል ከቤተሰቡ ጋር በሚኖርባት አዲስ ከተማው የተለያዩ መሳሪያዎችን ከእንጨትና ከብረት በማምረት የልጅነት ጊዜዉን አሳልፏል።

በኬሚስትሪ እና በቋንቋ ጥሩ ብቃት የነበረው ታዳጊ ኖቤል በ1842 በግል ጥናት መስጫዎች ትምህርቱን ተከታትሏል። ይህ የቤተሰቦቹ ውሳኔ ለብቃቱ የነበረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል። እንግሊዘኛ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ እና የራሺያ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ መናገር ሲችል እድሜው ብዙም አልገፋም ነበር።

ኖቤል ከ1841 እ.ኤ.አ እስከ 1842 ለ18 ወራት ብቻ ወደ ተማረበት በስቶክሆልም ወደሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተወስዷል። በመደበኛ ትምህርት ላይ ለ18 ወራት ብቻ የቆየ ሲሆን በወጣትነቱ ኒኮላይ ዜኒን ከተባለ ኬሚስት ጋር የጥናት ጊዜውን ያሳልፍ ነበር። በመቀጠልም እ.አ.አ በ1850 ወደ ፓሪስ በማቅናት በዚያ ለቀጣይ ስራዎቹ መሰረት የጣለለትን ስልጠና ወስዷል።


ኖቤል 355 በሚሆኑ ግኝቶቹ የፈጠራ ባቤትነት መብት ተሰጥቶታል፡፡ ከፈጠራዎቹ ሁሉ ‘ዳይናማይት’ ወይም ደማሚት የሚባው ሰው ሰራሽ የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር በጣም ታዋቂው ነው። ይህ ንጥረ ነገር በአልፍሬድ ኖቤል ስም ኖቢሊየን በመባል ይታወቃል። ኖቤል እንደ ብረት እና ብረት ነክ ቁሳቁሶችን አምራችነቱ በመሳሪያ ማምረቻ ድርጅት ውስጥ ‘ዳይናማይት’ እና ‘ቦፈር’ የተባለ የጦር መሳሪያ በዋናነት ያመርት ነበር።

ባመረተው መሳሪያ ምክንያት የሞቱ ጨቅላ ህፃናትን ሞት ዜና ካነበበ በኋላ በስራው ደስተኛ ሆኖ መቀጠል ቢያቅተውም የጋዜጠኞች የስህተት ዜና ግን ህይወቱን ቀይሮታል።

እ.አ.አ. በ1888 የአልፍሬድ ኖቤል ወንድም የሆነው ሉድቨንግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ካንስ በሞተ ማግስት የሀገሪቱ ጋዜጦች ያስነበቡት ዘገባ ‘‘የሞት ነጋዴው ሞተ’’ የሚል ርዕስ ነበረው። በሕይወት ያለው ኖቤል ሞቱ እንዴት ሊዘገብ እንደሚችል በሕይወት ሆኖ ዐየ፡፡ ሟቹ አልፍሬድ እንደሆነ ያመኑት ጋዜጠኞች የሰሩት ስህተት ልጅና ሚስት የሌለዉን ይህንን ሰዉ ከህልፈቱ በኋላ ዓለም እና ህዝቦቿ በምን ዐይነት መልኩ ሊያስታወሱት እንደሚችሉ እንዲያስብ አስገደደው፡፡ በዚህም መነሻነት እ.ኤ.አ በ1895 ፓሪስ በሚገኘዉ የሲዊዲሽ ኖርዊክ ክለብ በየዓመቱ ሃገራት እና ህዝቦቿን ሳይለይ የሚሸልመዉን የኖቤል ሽልማትን ለመመስረት የሚያስችለዉን የመጨረሻ ፊርማና ቃለመሃላዉን አኑሯል።

ኖቤል ለዚህ ሽልማት ከነበረዉ የሃብት ተቀማጭ 94 በመቶ ማለትም 31,225,000 የሲዉዲሽ ክሮኖር ለሽልማት ድርጅቱ ምስረታ እንዲዉል አድርጓል። ሽልማቶቹም በአምስት የተለያዩ ዘርፎች የተመደቡ ሲሆን በፊዚክስ ዘርፍ፣ በኬሚስትሪ ዘርፍ፣ በህክምና ሳይንስ እና ሳይኮሎጂ ዘርፍ፣ በስነፅሁፍ ዘርፍ እና በዓለም አቀፍ አለመግባባት ዙሪያ የተኩስ አቁም ስምምነትን በተዋጊዎች መካከል በመፍጠር ለሰላም የበኩላቸውን ላደረጉ ሰዎች የሚሰጥ የሰላም ሽልማት 5ኛ ዘርፍ ነው።

የኖቤል ሽልማት ድርጅት ከተቋቋመ በኋላ በኖቤል ስም የተሰየሙ በርካታ ድርጅቶች ተመስርተው እስከዛሬም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ከነዚህም መካል ‘አካዝ ኖቤል’ መቀመጫውን በአምስተርም ያደረገ የቀለም ማምረቻ ፋብሪካ እና ‘ዳይናማይት ኖቤል’ በጀርመን የሚገኝ የኬሚካል እና የጦር ማምረቻ ድርጅት ይገኝበታል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top