ታሪክ እና ባሕል

ኢትዮጵያውያን በ2019

በቅርቡ በምናጠናቅቀው የፈረንጆቹ ዓመት ኢትዮጵያውያን በዓለም መድረክ ላይ ደምቀው የታዩበት ነው ማለት ይቻላል፡፡

 • ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የኖቤል ሽልማት
 • ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የአፍሪካዊያን ሴቶች ቁጥር ግን እጅግ አነስተኛ በሆነበት በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሲካተቱ ከ2018 በኋላ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ፕሬዝደንቷ ባሳለፍነው ዓመት ዝርዝር ውስጥ የ97ኛ ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን በተጠናቀቀው ዓመት አራት ደረጃ አሻሽለው 93ኛ ሆነዋል፡
 • ለማኅበረሰባቸው እና ለሴቶች ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ሲል ከ100 ሐገሮች ከተውጣጡ ተወዳዳሪዎች ጋር አነጻጽሮ “የ2019 ሲ.ኤን.ኤን. የዓመቱ ጀግና” ሲል ቀዳሚውን ደረጃ በመስጠት እውቅና እና ሽልማት ለፍሬወይኑ መብራህቱ ሰጥጧታል፡፡
 • ዶክተር አረጋዊ ግርማይ ‹የሰሜን ካሮላይና ግዛት የዓመቱ ምርጥ የቤተሰብ ሐኪም› ተብለው በ2019 ዓ.ም. እ.አ.አ. ተሸልመዋል፡፡
 • በ2019 ዓ.ም እ.አ.አ. በተካሄደው “World Athletics Award“ ጀግናዋ የኢትዮጵያ አትሌት ደራርቱ ቱሉ “Woman of The Year“ ወይም “የዓመቱ ምርጥ ሴት” የሚለውን ሽልማት ተሸልማለች፡፡
 • ለመጀመሪያ ጊዜ  ‹የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ክብር እና ማስታወሻ ሽልማት› ስነስርዓት በአትላንታ ተካሂዷል፡፡ ሽልማቱም የተካሄደው በ36ኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን (ESFNA – Ethiopian sport federation in north america) ባዘጋጀው ፌስቲቫል ላይ ነው፡፡ የሽልማት ስነስርዓቱም የተካሄደው ከኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር (Ethiopian Free Press Journalists Association) ጋር በመተባበር ነው፡፡

በሽልማት ስነስርዓቱም በየዘርፋቸው ለመሸለም የበቁት የሚከተሉት ኢትዮጵያውያን ናቸው፡-

 1. በሙዚቃ – ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
 2. በግጥም – በእውቀቱ ስዩም
 3. በአሳታሚዎች – ኤሊያስ ወንድሙ (ፀሃይ አሳታሚዎች መስራች)
 4. በቲያትር – ዓለምፀሃይ ወዳጆ
 5. በሚዲያ – ሄኖክ አለማየሁ
 6. የአብረሃም በላይነህ ‹እቴ አባይ› የተሰኘው ጥዑም ዜማ፤ በአፍሪካ ደረጃ በተካሄደው የ6ኛው አፍሪማ የሙዚቃ ሽልማት ላይም ‹ምርጥ አፍሪካዊ የባህል ዘፋኝ› (Best African Traditional Artist) በሚል ዘርፍ በማሸነፍ የራሱንና የሃገሩን ስም በአፍሪካ ደረጃ እንዲጠራ አድርጓል፡፡
 7. በ2019 ዓ.ም. እ.አ.አ. ላይ በተካሄደው  miss progress international 2019 የቁንጅና ውድድር ላይ፤ ኢትዮጵያን ወክላ በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው ወይዘሪት ቕሳነት ሞላ “ምርጥ የባህል አለባበስ” (best national costume) በሚለው ዘርፍ አንደኛ ወጥታ ተሸልማለች፡፡ ቕሳነት በውድድሩ ላይ የለበሰችው የአርሲ-ኦሮሞ ባህላዊ የሴቶች አለባበስን የነበረ ሲሆን፤ ይህም ባህላዊ አለባበስ ከመላው ዓለም ከመጡ ቆነጃጅት ተሸላ እንድትሸለም አስችሏታል፡፡  
 8. በ2019 ዓ.ም. እ.አ.አ. የኢትዮጵያውያን ብሎም የአፍሪካውያን ኩራት የሆነው ‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ› እና ዋና ኃላፊው አቶ ተወልደ ገብረማርያም የተለያዩ ሽልማትን በመቀበል የደመቁበት ዓመት ነበር፡፡
 9. March 25, 2019 ላይ በተካሄደው ‹የአፍሪካ የዓመቱ ሻምፒዮን› (African Champion of the year) በተሰኘው ሽልማት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ተከታታይ ዓመት ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ይህም በአፍሪካ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዋነኛው እና ምርጥ የስራ አፈፃፀም የሚታይበት ተቋም ለመሆኑ ዋነኛ ማስረጃ ነው፡፡
 10. CAPA Global Aviation  በሚያካሂደው  ዓመታዊው  የተቋማት ኃላፊዎች ሽልማት ላይ፤ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ‹የዓመቱ ምርት የአየር መንገድ ኃላፊ› ተብለው ሊሸለሙ በቅተዋል፡፡
 11. Feb 09, 2019 ላይ በተደረገው የ Most Influential People of African Descent (MIPAD) ሽልማት ስነስርዓት ላይ፤ አቶ ተወልደ ገብረማርያም  ‹ምርጥ አፍሪካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ› በሚል ዘርፍ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል፡፡
 12. ዓለም
 13. አቀፍ የአየር መንገዶች ህብረት የሆነው Skytrax በ2019, June 19 ላይ በፓሪስ ከተማ ባካሄደው የሽልማት ስነስርዓት  ‹የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ› በመባል ለ3ኛ ተከታታይ ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
 14. ባለቅኔና ፀሃፊ-ተውኔት ለምን ሲሳይ እና የዞን 9 ብሎገር ሆኖ በመፃፍ የሚታወቀው በፍቃዱ ኃይሉ ‹international writer of courage› ወይም በአማርኛው ‹አለማቀፍ ደፋር ፀሃፊ› ብለን ልንጠራው በምንችለው የሽልማት ስነስርዓት ላይ የ2019 Pen Pinter Prize ን በጋራ ሊያሸንፉ  ችለዋል፡፡
 15. የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የ2019 የስፕሪንግ ኢምፔሪያል ሽልማትን፣ ከጃፓን መንግስት ኖቬምበር 3 ላይ ወስደዋል፡፡
 16. “የኢትዮ-ጃዝ አባት” ተብለው የሚጠሩት ሙላቱ አስታጥቄ ባሰለፍነው ዓመት ነበር፤ ለኪነጥበብ ባበረከቱት አስተዋፅኦ Order of Arts and Letters የተሰኘ ሽልማትን ከፈረንሳይ መንግስት ለመቀበል የቻሉት፡፡
Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top