ታሪክ እና ባሕል

አንጀሊና በኢትዮጵያ

የራሷን 3 ልጆች እንዲሁም ከኢትዮጵያ፣ ከካምቦዲያ እና ቬትናም የተቀበለቻቸውን 3 ልጆችን ጨምሮ 6 ልጆችን የምታሳድገው ታዋቂዋ የሆሊውድ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያየች።

አንጀሊና በልማት፣ በሴቶች እና በስደተኞች ጉዳይ ላይ ከፕሬዝዳንቷ ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርጋለች።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅም “የአንጀሊና ጆሊ ጉብኝት ኢትዮጵያ በአስገራሚ የለውጥ ጎዳና ላይ ባለችበትና የሴቶችን ጉዳይ ጨምሮ በሁሉም መስኮች አዲስ ምዕራፍ እየተከፈተ ባለበት ወቅት የተደረገ በመሆኑ ጉብኝቱ ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ስለ አፍሪካ ያለውን ዐተያይና አስተሳሰብ ለመለወጥ የማይናቅ አስተዋፅኦ አለው” ብለዋል።

በሰብአዊ ስራዎቿ የምትታወቀው አንጀሊና በበኩሏ “ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት በህፃናት እና ሴቶች ዙሪያ እንዲሁም ጤና ላይ መስራት የሚቻልባቸውን ዕድሎች ለማየት ነው” ብላለች።

ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን የ14 ዓመት ታዳጊ ዘሃራን ጨምሮ ልጆቿ አብረዋት መጥተዋል።

በ10 ዓመታት ውስጥ ብቻ ለስደተኞች ከ47 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያበረከተችው አንጀሊና ህጻናትን በጉዲፈቻ ከማሳደግ በተጨማሪ በተፈጥሯዊ እና በጦርነት አደጋዎች የተጎዱ ከ20 በላይ ሐገራት በመዘዋወር እርዳታ በማድረግ ትታወቃለች። ከነዚህም ውስጥ ኮንጎ፣ ሶሪያ፣ ሊባኖስ፣ ኢራቅ፣… ተጠቃሾች ናቸው።

የዘዊኬንድ ልገሳ

ፎርብስ መጽሔት ይፋ ባደረገው የ2016 ከፍተኛ ተከፋይ 100 የዓለማችን ዝነኞች ዝርዝር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ካካተታቸው 15 ዝነኞች ከካከል አንዱ የነበረው ተወዳጁ አቤል ተስፋዬ (The Weekend) በኤች.አይ.ቪ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት መርጃ እንዲውል 100 ሺ ዶላር መለገሱ ተሰምቷል።

መቀመጫውን ቆሮንቶ ካናዳ ውስጥ ባደረገ ‘ፒፕል ቱ ፒፕል ካናዳ’ በተሰኘ በጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝነት እርዳታውን መለገሱን ከዜናው ጋር ተያይዞ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከኢትዮጵያዊያን ወላጆች የተገኘው አቤል ተስፋዬ እንደ ፎርብስ መጽሔት ዘገባ ከሆነ የወቅቱ የተጣራ ዓመታዊ ገቢው 55 ሚልዮን ዶላር ነበር።  

በ2019 ዓ.ም. ከፍተኛ ገቢ ያስገቡ ዝነኞች

እንደፎርብስ መጽሔት ገለፃ ከሆነ ባሰለፍነው 2019 ዓ.ም. ከፍተኛ ገቢ ያገኙ ዝነኞች የሚከተሉት ናቸው፡-

 1. ቴይለር ስዊፍት – 185 ሚሊዮን ዶላር – ሙዚቀኛ
 2. ካይሊ ጄነር – 170 ሚሊዮን ዶላር – ፋሽን ሞዴል እና ሶሻል ሚዲያ
 3. ካንዬ ዌስት – 150 ሚሊዮን ዶላር – ሙዚቀኛ
 4. ሊዮኔል ሜሲ – 127 ሚሊዮን ዶላር – እግርኳስ ተጫዋች
 5. ኤድ ሺራን – 110 ሚሊዮን ዶላር – ሙዚቀኛ
 6. ክርስቲያኖ ሮናልዶ – 109 ሚሊዮን ዶላር – እግር ኳስ ተጫዋች
 7. ኔይማር – 105 ሚሊዮን ዶላር – እግር ኳስ ተጫዋች
 8. ዘ ኢግልስ – 100 ሚሊዮን ዶላር – የሙዚቃ ባንድ
 9. ዶክተር ፊል ማክግሮው – 95 ሚሊዮን ዶላር – የሚዲያ ሰው
 10.  ካኔሎ አልቫሬዝ – 94 ሚሊዮን ዶላር – ቦክሰኛ
 11.  ሮጀር ፌደረር – 93.4 ሚሊዮን ዶላር – የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች
 12.  ሃዋርድ ስተርን – 93 ሚሊዮን ዶላር – የሚዲያ ሰው
 13.  ጄ.ኬ. ሮውሊንግ – 92 ሚሊዮን ዶላር – ደራሲ
 14.  ረስል ዊልሰን – 89.5 ሚሊዮን ዶላር – የአሜሪካ እግር ኳስ ተከላካይ
 15.  ድዌይን ጆንሰን – 89.4 ሚሊዮን ዶላር – የፊልም ተዋናይ
 16.  አሮን ሮጀርስ – 89.3 ሚሊዮን ዶላር – የአሜሪካ እግር ኳስ ተከላካይ
 17.  ሌብሮን ጄምስ – 89 ሚሊዮን ዶላር – ቅርጫት ኳስ ተጫዋች
 18.  ረሽ ሊምቦው – 87 ሚሊዮን ዶላር – የሚዲያ ሰው
 19.  ኤልተን ጆን – 84 ሚሊዮን ዶላር – ሙዚቀኛ
 20.  ጄይ ዚ – 81 ሚሊዮን ዶላር – ሙዚቀኛ

20 ቢዮንሴ ኖውልስ – 81 ሚሊዮን ዶላር – ሙዚቀኛ

በ2019 ዓ.ም. ከፍተኛ ገቢ ያስገቡ 20 ፊልሞች

Box Office Mojo እንደዘገበው

20. Godzilla: King of the Monsters
በአሜሪካ: $110,500,138
በዓለምአቀፍ: $275,400,000
በአጠቃላይ: $385,900,138

19. Alita: Battle Angel
በአሜሪካ: $85,710,210
በዓለምአቀፍ: $319,142,333
በአጠቃላይ: $404,852,543

18. The Captain
በአሜሪካ: $706,572
በዓለምአቀፍ: $406,515,719
በአጠቃላይ: $407,222,291

17. My People, My Country
በአሜሪካ: $2,356,683
በዓለምአቀፍ: $420,476,733
በአጠቃላይ: $422,833,416

16. The Secret Life of Pets 2
በአሜሪካ: $158,257,265
በዓለምአቀፍ: $271,176,898
በአጠቃላይ: $429,434,163

15. Pokémon Detective Pikachu
በአሜሪካ: $144,105,346
በዓለምአቀፍ: $287,600,000
በአጠቃላይ: $431,705,346

14. It Chapter Two
በአሜሪካ: $211,587,886
በዓለምአቀፍ: $258,700,000
በአጠቃላይ: $470,287,886

13. Maleficent: Mistress of Evil (still in cinemas)
በአሜሪካ: $111,549,934
በዓለምአቀፍ: $369,015,571
በአጠቃላይ: $480,565,505

12. How to Train Your Dragon: The Hidden World
በአሜሪካ: $160,799,505
በዓለምአቀፍ: $359,097,143
በአጠቃላይ: $519,896,648

11. The Wandering Earth
በአሜሪካ: $5,875,487
በዓለምአቀፍ: $693,885,286
በአጠቃላይ: $699,760,773

10. Ne Zha
በአሜሪካ: $3,695,533
በዓለምአቀፍ: $696,852,221
በአጠቃላይ: $700,547,754

9. Frozen 2 (still in cinemas)
በአሜሪካ: $288,845,131
በዓለምአቀፍ: $453,215,336
በአጠቃላይ: $742,060,467

8. Fast & Furious Presents: Hobbs & Shaw
በአሜሪካ: $173,810,100
በዓለምአቀፍ: $585,100,000
በአጠቃላይ: $758,910,100

7. Joker (still in cinemas)
በአሜሪካ: $330,523,625
በዓለምአቀፍ: $718,400,000
በአጠቃላይ: $1,048,923,625

6. Aladdin
በአሜሪካ: $355,559,216
በዓለምአቀፍ: $695,134,737
በአጠቃላይ: $1,050,693,953

5. Toy Story 4
በአሜሪካ: $434,035,540
በዓለምአቀፍ: $639,356,585
በአጠቃላይ: $1,073,392,125

4. Captain Marvel
በአሜሪካ: $426,829,839
በዓለምአቀፍ: $701,444,955
በአጠቃላይ: $1,128,274,794

3. Spider-Man: Far From Home
በአሜሪካ: $390,532,085
በዓለምአቀፍ: $741,395,911
በአጠቃላይ: $1,131,927,996

2. The Lion King
በአሜሪካ: $543,634,365
በዓለምአቀፍ: $1,112,675,054
በአጠቃላይ: $1,656,309,419

1. Avengers: Endgame
በአሜሪካ: $858,373,000
በዓለምአቀፍ: $1,939,427,564
በአጠቃላይ: $2,797,800,564

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top