ጣዕሞት

በቅድመ አክሱም የነበረች ከተማ ተገኘች

ከአክሱም በ50 ኪሎሜትር በስተ ምስራቅ አቅጣጫ ርቃ ከየሃ አቅራቢያ መዝብር በሚባለው ጣቢያ ልዩ ስሙ ቤተ-ሰማዕቲ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ላይ ከ80 ዓ.ዓ. እስከ 825 ዓ.ም. የነበረች የከተማ ቅሪት መገኘቷ ተዘግቧል፡፡

ኒው ሳይንቲስት የተባለው መጽሔት በድኅረ-ገፁ እንዳሰፈረው ከአክሱምና ሮም ዘመነ-መንግሥታት በፊት የአፍሪካ ቀንድን ጨምሮ እስከ ደቡባዊ ዓረብ ያስተዳድር የነበረ ጠንካራ አስተዳደር እንደነበር ጠቅሷል፡፡ ጥናቱ እንደሚያመላክተውም የአክሱም ሥልጣኔ እንዴት እንዳደገ ማንም አያውቅም፡፡ ይሁን እንጂ ከዘመነ-አክሱም ሥልጣኔ በፊት በቦታው ማንነታቸው ያልታወቀ ህዝቦች ይኖሩ እንደነበር ገልጿል፡፡

ከዘመነ-አክሱም ሥልጣኔ በፊት ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሃገራት የራሳቸው ጥንታዊ አፃፃፍ እና የኪነ-ህንፃ ጥበብ የነበራቸው፣ በአሁኗ ሰሜን ኢትዮጵያ ይሐ በሚባለው ቦታ ላይ እንደነበር ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በአርኪኦሎጂ ቁፋሮ አጥኚዎቹ የተገኘችው ጥንታዊት ከተማ የአክሱም ሥልጣኔ አካል ናትም ተብሏል፡፡ በዚህ ቦታ ላይ ከተገኙት የፈራረሱ ህንፃዎች መሃል ቤተ-ጸሎቶች እና መኖሪያ ቤቶች ይገኙበታል፡፡ ከብረት፣ ከመዳብ እና ነሐስ ተቀላቅሎ የተሰራ በወርቅ የተለበጠ የበሬ ጭንቅላት ቅርፅ ያለበት የእጅ ቀለበት፣ የወይን መያዣ ብርጭቆ እና በዕንቁ ያጌጠ ብርጭቆም ተገኝቷል፡፡

በግዕዝ ቋንቋ መዝብር ማለት ፍርስራሽ (ኦና) ማለት ነው፡፡ ይህ ጥንታዊ ቦታም ልክ እንደ ስሙ መዝብር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ከኖህ እና ቤተሰቦቹ በስተቀር ሁሉም አህዛብ በጥፋት ውሃ እንደ ጠፉ ይጠቀሳል፡፡ ኖህም፡ ካም፣ ያፌት እና ሴም የሚባሉ ልጆች እንደወለደ፣ ካም የተባለው የኖህ ልጅ ሲሞት የተቀበረበት ቦታ መዝብር እንደሆነ፣.. እና ሌሎችም ማስረጃዎች ጠቅሷል፡፡ የአርኪኦሎጂ ተመራማሪዎችም መዝብር የሚባለው ቦታ በየሐ አቅራቢያ እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ደግሞ ሌሎች የአርኪኦሎጂ ተመራማሪዎች “መዝብር”

የዘዊኬንድ ልገሳ

ፎርብስ መጽሔት ይፋ ባደረገው የ2016 ከፍተኛ ተከፋይ 100 የዓለማችን ዝነኞች ዝርዝር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ካካተታቸው 15 ዝነኞች ከካከል አንዱ የነበረው ተወዳጁ አቤል ተስፋዬ (The Weekend) በኤች.አይ.ቪ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት መርጃ እንዲውል 100 ሺ ዶላር መለገሱ ተሰምቷል፡፡

መቀመጫውን ቆሮንቶ ካናዳ ውስጥ ባደረገ ፒፕል ቱ ፒፕል ካናዳ በተሰኘ በጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝነት እርዳታውን መለገሱን ከዜናው ጋር ተያይዞ የወጡ መደጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከኢትዮጵያዊያን ወላጆች የተገኘው አቤል ተስፋዬ እንደ ፎርብስ መጽሔት ዘገባ ከሆነ የወቅቱ የተጣራ ዓመታዊ ገቢው 55 ሚልዮን ዶላር ነበር፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top