ጣዕሞት

“ፀጥተኛው መንገድ” ተከፈተ

 “ፀጥተኛው መንገድ” ተከፈተ

የሰአሊ ልጅቅዱስ በዛወቅ ስብስቦች ባሳለፍነው ወር መጨረሻ በጋለሪ ቶሞካ ለዕይታ ቀርበዋል፡፡ እስከ ታሕሳስ 19፣ 2012 ዓ.ም. ድረስ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የሚቆየው የስዕል አውደ ርዕይ ‹‹ፀጥተኛው መንገድ›› የሚል ርእስ ተሰጥቶታል፡፡

ጥቅምት 21፣ 2012 ዓ.ም. ምሽት 12፡00 ላይ የስነ-ጥበብ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለዕይታ የበቁት ስእሎች 40 የቀለም ቅብ ሥራዎች ናቸው፡፡

በስርአት የተጠኑ፣ ተደጋጋሚ ሙከራዎች በማድረግ በልምድ የዳበሩ፣ እንደሆኑ የተነገረላቸው የሰአሊው ስራዎች በቀጥታ፣ በጥምዝ እና ዝረግ መስመሮች አሳሳል እና የአቀባብ ዘዴዎችን በመጠቀም የተሰሩ ናቸው፡፡ የተተረማመሱ እና በሽክርክሪት የሚንሳፈፍ ቅርጸ ዝብ (Collar abstract images) ስለመሆናቸው በባለሙያዎች ተብራርቷል፡፡ ከአዲስ አበባችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር አዛምደን ካመሳጠርናቸው የሰፋ ትርጓሜ እንደሚኖራቸውም ተወስቷል፡፡

በአቢሲንያ የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት፣ በእንጦጦ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ፣ በኢንላይትመንት አርት አካዳሚ፣… ትምህርቱን የተከታተለው ልጅቅዱስ በዛወርቅ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ ያለምንም ድጋፍ እና ተጽእኖ ተሰጥኦውን እንዳዳበረ የሚናገረው ወጣቱ ሰአሊ በአሁን ሰአት የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የስነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ነው፡፡

ከዚህ በፊት ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመሆን የጋራ ኤግዚቢሽኖች ያሳየ ሲሆን በግሉ አውደ-ርዕይ ሲያዘጋጅ ግን ይሕ የመጀመሪያው መሆኑ ታውቋል፡፡

ተመሳሳይ የስእል አውደ ርዕዮች በጋለሪያ ቶሞካ ለዕይታ ሲቀርቡ ይሕ ለ30ኛ ጊዜ መሆኑን በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ከነበረው ስነ-ስርአት ለመረዳት ችለናል፡፡ 

፪፭ ወርቃማ ዓመታት

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ ካስቀመጡ የሙዚቃ ባንዶች ውስጥ አንዱ የሆነው ኤክስፕረስ ባንድ በያዝነው ወር ሃያ አምስት ዓመት ሞልቶታል፡፡ ህዳር ፪፩ የተመሰረተው ኤክስፕረስ ባንድ ለሩብ ክፍለ ዘመን እንደተወደደ ዘልቋል፡፡ በሙያቸው አንቱታን ያተረፉት ሙዚቀኞች ፈለቀ ኃይሉ፣ ክብረት ዘኪዮስ፣ ደረጄ ተፈራ እና ኤሊያስ በቀለ መስራቾቹ ናቸው፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ባንዱን ከለቀቀው ኤልያስ በቀለ እና በቅርብ ዓመታት በሞት ከተለየው ደረጄ ተፈራ በስተቀር ባንዱ አሁንም ከነ ሙሉ ክብሩ ዘልቋል፡፡

ኤክስፕረስ ባንድ ዝነኛ እና ተወዳጅ የሆኑ ድምጻዊያንን ለመድረክ አብቅቷል፡፡ ተሰጥኦአቸውን ለማውጣት መንገድ ላጡ ጀማሪያን በር ከፍቷል፡፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ ትእግስት በቀለ፣ አብዱ ኪያር፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሸዋንዳኝ ኃይሉ፣ ጆኒ ራጋ፣… ከባንዱ ጋር ከጀመሩ እና አብረው ከሰሩ መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top