ከቀንዱም ከሸሆናውም

ፓርላማው እና የንግሥቲቷ ስውር እጅ

ፓርላማው እና የንግሥቲቷ ስውር እጅ

እንግሊዝ ጥቂት የማይባሉ “ደደብ ህጎችን (እንደ አንዳንዶች አስተያየት) ሳትሽር ዛሬም ድረስ እንዲሰሩ በመፍቀድ ትታወቃለች። ለአብነት ያህል በስኮትላንድ አንድ ሰው በር አንኳኩቶ መጸዳጃ ቤት መጠቀም እፈልጋለሁ ካለ የቤቱ ባለቤት የግድ ጥያቄውን ማስተናገድ ይኖርበታል። አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ልጇን በፈለገችበት ቦታ ሌላው ቀርቶ በፖሊስ ኮፍያ ላይ መገላገል እንድትችል ህጉ ይደግፋታል። በሌላ በኩል “በምክር ቤት ውስጥ መሞት ህገ ወጥ ተግባር ነው” ይላል ይኸው ወጣ ያለ ሕግ።

የአስቂኝና የአስደንጋጭ ህጎች ባለቤት የሆነው የእንግሊዝ ፓርላማ በዓለም ታሪክ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ ነው። ከ13ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ሥራ ላይ ነበር። ታዲያ ጥንት በዘውዳዊ ሥርዓት ፍላጎት ረቀው የወጡ ህጎች እና አሠራሮች ዛሬም ድረስ የአከራካሪነትና የአስገራሚነት ካባቸውን ደርበው እንደተሠየሙ ናቸው።

 ብዙዎች ዛሬ ዛሬ የዘውዳዊው ሥርዓት (ንግስቲቷ) የክብር እንጂ የፖለቲካ ተፅእኖ ፈጣሪነት ሚና የለውም ብለው ያስባሉ። የቀሩት ደግሞ በዚህ አይስማሙም። እንግሊዝ ዛሬ ፍፁም በሆነ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ተወካዮቿንና በውክልና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ብትመርጥም የንግሥቲቷ ተፅዕኖ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተናነሰ ነው። ለዚህ ማሳያ የሚጠቀሱ አብነቶች አሉ። ከዘመኑ ጋር የማይሄዱ፣ ዘውዳዊ ሥርዓቱን የሚያሳብጡ በአጠቃላይ እንቅፋት ፈጣሪ ህጎችንና አሰራሮችን ማሻሻል ወይም መለወጥ አልተቻለም። ይህም ያለ ንግሥቲቷ ይሁንታ የፖለቲካ ታላቅነት አለኝ የሚለው ፓርቲ መራመድ አለመቻሉ ነው። እነዚህ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት ስለ ፓርላማው ወጣ ያለ አሠራር ጥቂት ልበል።

 ፓርላማው ዘ-ሃውስ ኦፍ ኮመን እና ዘ-ሃውስ ኦፍ ሎርድስ ተብሎ የተከፈለ ነው። የሃውስ ኦፍ ኮመን አባላት (650) በህዝብ ምርጫ ነው የሚመረጡት። አብላጫ ቁጥር ያለው ፓርቲ የሀገሪቷን መንግሥት ይመሰርታል። የምክር ቤቱ አባላት ህጎችን በማውጣት እና ትላልቅ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና በመከራከር ይታወቃሉ። የሃውስ ኦፍ ሎርድስ (760) አባላት ያለ ምርጫ ነው ቦታቸው ላይ የሚሰየሙት።

 የሁለቱም ፓርላማዎች መቀመጫዎች ቀለም የተለያየ ነው። የተወካዮች ምክር ቤት አረንጓዴ ሲሆን የጌታዎቹ (House of Lords) ቀይ ነው። ቀይ ቀለም የንጉሳዊ ቀለም ነው ተብሎ ይታሰባል። አዲስ አፈ ጉባኤ ሲመረጥ በራሱ ጊዜ አይደለም ወደ ወንበሩ የሚያመራው። በፓርላማው አባላት በግድ እየተጎተተ እንጂ። ይህ የቆየ ባህላዊ ሥርዓት ሲሆን አፈ ጉባኤው ፓርላማውን ከንጉሳዊው ቤተሰብ የማገናኘት ድልድይ አካል ተደርጎ ይወስዳል። በፓርላማ ስብሰባ ወቅት አባላት አንድን ተናጋሪ ለተቃውሞ ወይም ለድጋፍ ባልተለመደ ድምፆች እያጉረመረሙ እና እየጮሁ ሊያቋርጡት ይችላሉ። ይህም ፓርላማው ንቁ እና ተፎካካሪ ከባቢ አየር ውስጥ መሆኑን ለማሳያ የሚጠቀሙበት በመሆኑ በተቻለ መጠን በትዕግስት ይያዛል። በጥያቄ እና መልስ ስብሰባ ወቅት የፓርላማው አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የተቃዋሚው መሪ ከተናገረ በኋላ ቁጭ ብድግ ሲሉ መመልከት የተለመደ ነው። ለተናጋሪዎቹ ክብር ለመስጠት ማለትም በሀገራችን ቋንቋ “ኖር ብለናል!” ለማለት ይመስላል። ግን አይደለም። ይህን የሚያደርጉት የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ ትኩረት ለመሳብ ነው። በሚነገረው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ መናገር የምፈልገው ወይም መጠየቅ የምፈልገው አለ እንደማለት።

ይህ ማለት ግን የአፈ ጉባኤው ጽሕፈት ቤት ቀድሞ ማን መናገር እንደሚፈልግ አያውቅም ማለት አይደለም። አባላቱ በአንድ ጉዳይ ላይ ድምፅ ወደ መስጠት ሲገቡ የሚጠቀሙባቸው የይሁንታ እና አሉታ ቃላቶችም እንደ ምክር ቤታቸው ቀለማት የተለያዩ ናቸው። የምክር ቤቱ አባላት ውጤቱን ሲገልፁ “አይ” እና “ኖ” ሲሉ የጌታዎቹ ምክር ቤት “ኮንቴንት” እና “ኮንቴንት ያልሆነ” ነው የሚሉት። የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር 650 ቢሆንም የወንበር ቁጥር ግን 427 ብቻ ነው። ስለዚህ ትላልቅ ስብሰባዎች ሲኖሩ የተቀሩት ቆመው ለማዳመጥ ይገደዳሉ። ማንኛውም የምክር ቤት አባላት መቀመጫ ማግኘት ከፈለገ ከጠዋቱ 2 ሰዓት መጥቶ የ“ፀሎቷን ካርድ” መያዝ አለበት።

 አሁን ደግሞ በአንድ በኩል የንግሥቲቷን ከፍተኛ ሥልጣንና ተቀባይነት በሌላ በኩል ትልቅ ነፃነት ያለው ፓርላማ ትልቅ አቅም ያጣባቸውን አንዳንድ ጉዳዮች እየመዘዝን እንመልከት።

 ፓርላማው እና የንግሥቲቷ ስውር እጅ ዓለማየሁ ገበየሁ 34 ታዛ መጽሔት | ቅፅ 03 ቁጥር 25 | መስከረም-ጥቅምት 2012 ዓ.ም. እንደሚታወቀው በብዙ ሀገሮች ተሿሚዎች ቃል የሚገቡት የመረጣቸውን ህዝብ ለማገልገልና ለመንግሥታዊ ግዴታ ነው። ተመራጭ የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት ግን ለየት ያለ ቃለ መሃላ ካልፈፀሙ ደመወዝ አይከፈላቸውም። ወንበሩ ላይ ተሰይመው መከራከር አይችሉም። 500 ፓውንድ ይቀጣሉ። ሌላው ቀርቶ መቀመጫቸው ላይ ባዶ ተብሎ ሊጻፍበት ይችላል። እና ቅዱስ ቃል የታተመበትን መጽሐፍ አጥብቆ በመሳም “እኔ እገሌ /እገሊት ሁሉን ቻይ በሆነው በፈጣሪ ስም ንግሥት ኤልሳቤጥንና ወራሾቻቸውን በታማኝነት በህጉ መሰረት ለማገልገል ቃል እገባለሁ፤ “ፈጣሪም ይርዳኝ” ማለት ግዳቸው ይሆናል።

 በአንድ ወቅት ታዲያ 22 የሚደርሱ የምክር ቤት አባላት ለዚህ የቆየ ህግ አንገዛም፣ የኛ ተጠሪነት ለመረጠን ህዝብ ስለሆነ ቃለ መሃላችንንም ለህዝባችን እናደርጋለን በማለት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር። የሊበራል ዲሞክራቱ አባል እና የተቃውሞው ቡድን ተወካይ ኖርማን ቤከር ግንኙነት ለሌላው አካል ቃለ መሃላ ማድረግ ትርጉም የለሽ ተግባር በማለት ነበር የተቃወመው። “ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ ላልሆነች ንግሥት አንምልም” ያሉ እንደነበሩ ሁሉ በመሃላ ወቅት ጣታቸውን የመስቀል ምልክት በመስራት ተቃውሟቸውን የገለፁ ነበሩ። ዞሮ ዞሮ ይህ ተቃውሞ “ህገ-መንግሥታዊ ውንብድና ነው” በሚሉ አንዳንድ አባላት ተፅዕኖ ጉዳዩ ተጠናክሮ እንዳይቀጥልና እንዲጨናገፍ ተደርጓል።

 ሌላው ያልተለመደ የሚመስለው ተግባር በሁለቱም ምክር ቤቶች ወደ መደበኛው ስብሰባ ከመገባቱ በፊት አባላቱ ፀሎት የማድረስ ግዴታ ያለባቸው መሆኑ ነው። ሚስጥሩ ባይታወቅም ፀሎቱ የሚደረገው ወደ ግድግዳው በመዞር ነው። የተወካዮች ምክርቤት ፀሎት ፈጣሪ በመንፈስ ለንግሥቲቱና ለመንግስታቸው ክብር እንዲያጎናፅፍ እንዲሁም አባላቱ ፍፁም በሆነ ኃላፊነት እንዲሰሩ የሚጠይቅ ነው።

የፓርላማው አባላት ፀሎቱ እንዲታገድ ፔቲሽን አስጀምረው ነበር። የአባላቱ የለውጥ ጥያቄ ምን ነበር? እነሱ እንደሚሉት ሃይማኖታዊ ሥርዓት የግለሰቦች ምርጫ እንጂ የሀገር ወይም የህግ አውጪው ፍላጎት አይደለም። የፓርላማ አባላት ነፃ በሆኑበት ጊዜ በግላቸው ፀሎታቸውን ሊያደርሱ ይችላሉ እንጂ ፀሎትን ተቋማዊ ማድረግ አግባብ አይደለም የሚል ነው። ይሁን እንጂ በስድስት ወራት ውስጥ የተገኘው የስምምነት ፊርማ 28 ሺህ አካባቢ በመሆኑ ጉዳዩ ተቋርጧል። ሃሳቡ ትክክል ቢመስልም ለምን የብዙኃኑን ፓርላማ አባላት ድጋፍ ማግኘት ተሳነው የሚለው ነጥብ ምላሽ ይፈልጋል።

የሁለተኛው ምክር ቤት (The House of Lords) አባላት አሰያየምም ሌላው አከራካሪ ጉዳይ ነበር። እነዚህ የምክር ቤት አባላት ዲሞክራት በሆነችው እንግሊዝ ያለ ህዝብ ምርጫ በስየማ ብቻ ነው ሥልጣን የሚይዙት። ለዚህም ነው አንዳንድ የለውጥ ንቅናቄ አራማጆች ሕገ- ወጥ አሰራሩን በመቃወም ህጉ እንዲቀየር እየጎተጎቱ የሚገኙት። አብዛኛዎቹ አባላት የሚሰየሙት በሀገሪቱ ውስጥ ባሉት ትላልቅ ፓርቲዎች ነው። አንዴ ከተሾሙ ከፈለጉ እስከ ህይወት ፍፃሜያቸው ቁጭ ሊሉ ይችላሉ። ደግሞ ብወዛም ሆነ የስየማ ሹመት የሚባል ነገር የለም። ለአብነት ያህል የ2018ትን መረጃ ስናይ 32 ከመቶ ከኮንሰርቫቲቭ፣ 24 ከመቶ ከሌበር፣ 12 ከመቶ ከሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ተሰይመዋል። 3 ከመቶ የሚደርሱት ጳጳሳት ሲሆኑ 4 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከማንም ጋር ተባባሪ ያልሆኑት ናቸው።

 በቅርቡ እነዚህን ተወካዮች በተመለከተ የሃውስ ኦፍ ሎርድስ ምክር ቤት አስቸኳይ ለውጥ ያስፈልገዋል የሚል ትችት አንብቤ ነበር። አንዳንድ ሰዎች “የምችዎቹ ክበብ አባላት” በማለት ነው የሚያሽሟጥጧቸው። በእርግጥ ጥያቄ እና መልስ ስብሰባ ወቅት የፓርላማው አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የተቃዋሚው መሪ ከ ተ ና ገ ረ በ ኋ ላ ቁጭ ብድግ ሲሉ መመልከት የተለመደ ነው። ለተናጋሪዎቹ ክብር ለመስጠት ማለትም በሀገራችን ቋንቋ “ኖር ብለናል!” ለማለት ይመስላል። ግን አይደለም። ይህን የሚያደርጉት የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ ትኩረት ለመሳብ ነው። አባላቱ መደበኛ ደመወዝ የላቸውም። ነገር ግን አንድ ቀን ስብሰባ ላይ ከተገኙ 305 ፓውንድ ይቆረጥላቸዋል። ይህ ገንዘብ ከታክስ ነፃ ስለሆነ የማይሸራረፍ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን የመጓጓዣ እና የሬስቶራንት ፋሲሊቲን በማስመልከት 150 ፓውንድ ይጨመርላቸዋል። ስብሰባ የሚያበዙ ከሆነ ከዋናዎቹ የምክር ቤት አባላት በላይ ነው ተጠቃሚ የሚሆኑት። ለዚህም ነው ብዙዎች ህዝብ በቀጥታ ኃላፊነት ያልሰጣቸው ሰዎች የህዝቡን ኪስ እያራቆቱ ነው በማለት የሚተቿቸው። በዚያ ላይ በቁጥር ደረጃ ከዋናው ምክር ቤት በላይ ናቸው። ሆኖም ይህንም ጉዳይ ፓርላማው መቀየር አልቻለም።

እነዚህ ጥቂት አብነቶች ምክር ቤቱ ከጊዜው ጋር የማይሄዱ የተለዩ ህጎቹን ለመቀየር አቅም የማጣቱን ሁኔታ ያሳያሉ። በሌላ በኩል ንግሥታዊ ሕጎች ዛሬም ድረስ የቅርብ ያህል እየተጠበቁ ይመስላል። በተለይ ንግሥቲቷን የሚመለከቱ ህጎችን ስንመለከት የጠቅላይነት ሚናቸው ጎልቶ ይታያል። ለምሳሌ ውሻዎ ከንግስቲቱ ውሻ ጋር ያለ ንግስቲቱ ይሁንታ ፍቅር መስራት ቢጀምር ታላቅ ቅጣት ይቀበላሉ። በሀገሪቱ የሚገኙ አሳ ነባሪዎችና ስተርጂን የተባሉ የአሳ ዓይነቶች በሙሉ የንግሥቲቱ ንብረት ናቸው። በፖስታ ላይ ቴምብርን ገልብጦ መለጠፍ እንደ ሀገር ከዳተኛ ያስቆጥራል። ንግሥቲቷ የዋዛ አይደሉም። ፓርላማው ደግሞ የዋዛ ሳይሆን የፈዛዛ ነው የሚያስብል አብነት በህዝቡ ይጠቀስበታል። በፓርላማው ማየት የተሳናቸውን ከሚመራ ውሻ በስተቀር እንስሳትን ይዞ መግባት በፍፁም የተከለከለ ነው። ነገር ግን በርካታ አይጦች ማንንም ሳያስፈቅዱ በፓርላማው ውሎ እና አዳር ማድረግ ከጀመሩ ዘመናት ተቆጥረዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top