ከቀንዱም ከሸሆናውም

ግቢ፣ እልፍኝ እና ሰቀላ

ግቢ፣ እልፍኝ እና ሰቀላ

ቱሉ ፊንፊኔ ላይ የምንሊክ ቤ ተ መ ን ግ ሥ ት ከተመሠረተ በኋላ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ “ግቢ” ተብሎ ይታወቅ ነበር። ሥርወ ቃሉ “መግባት” ፣ “ገባ” ከሚለው የአማርኛ ቃል የመጣ ነው” ይላል ኢንሳይክሎፒዲያ ኢቶፒካ።

ትክክለኛው ንጉሣዊያን ግቢ ወይም ቤተ-መንግሥት ሁለት ህንፃዎችን ይይዛል። እልፍኝና አዳራሽን። እልፍኝ የንጉሡ መኖሪያ ሲሆን፤ አዳራሽ ደግሞ የእንግዶች ማስተናገጃ ነው። እልፍኝ የሚለው ቃል በንጉሣዊያን ቤተ-ሰቦች ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ይታወቃል።

ወደኋላ ስንሄድ ወደ አፄ እያሱ IIኛ እንደርሳለን። አፄ ባካፋ በ1730 (እ.አ.አ) ሲሞቱ አስክሬናቸው ከእልፍኝ ወጥቶ ወደ ቤተ-ክርስቲያን መወሰዱ ተዘክሯል። ገብረሥላሴ ስለ አፄ ምንሊክ በፃፉት ዜና መዋዕል የአንኮበር፣ የእንጦጦና የአዲስ አበባ እልፍኞች ተጠቅሶዋል። ዳግማዊ ምንሊክ እልፍኝ ግቢ በቅርፁ የተነሳ እንቁላል ቤት ተብሎ ይታወቃል። የንጉሠ-ነገሥቱ እልፍኝ አስፈላጊ ሥፍራ እንደተሰጠው ተደርጎ ለማሳያነት የሚቀርበው በተለየ ስም የሚጠሩት የማዕረግ ዓይነቶች ናቸው። እልፍኝ አሽከር፣ እልፍኝ አስከልካይ (chamberlain) ሲባሉ፣ ቤተ-ክርስቲያናትም ለእልፍኙ ቅርብ ሆነው ሲገኙ ከእልፍኝ ጋር የተያያዘ ስያሜን ይይዛሉ። በጎንደር የሚገኘው እልፍኝ ጊዮርጊስ እና የአዲስ አበባ እልፍኝ (ጊቢ ገብርኤል ተጠቃሾች ናቸው።

 አዳራሽ ደግሞ ክብረ-በዓላትን ለማክበር እና ግብር ለመጣል ያገለግላል። የቀዳማዊ አፄ ዮውሐንስ ዜና መዋዕል ይህን ቃል ተጠቅመውበታል። አዳራሽ ከአገነባቡ ቅርፅ የተነሳው “አዳራሽ- ሰቀላ” ወይም አራት ማዕዘን አዳራሽ ተብሎ ይሰየማል። ሰቀላ ቃሉ ከመስቀል ጋር የተያያዘ ሲሆን አራት ማዕዘን ድንኳንን ያመለክታል። ሰቀላ አልባሬዝ በ16ኛው ክፍለ-ዘመን እንደጠቀሰው ረዥም አራት ማዕዘን ቤትን ያመለክታል። በአፄ ሰርፀድንግል ዜና መዋዕልም ከ100 ዓመታት በኋላ በአልሜዳ ጽሑፍ ውስጥ ሰቀላ ተጠቅሷል። አልመዳ እንደጻፈው “የኢትዮጵያውያን ቤቶች ክቦች ናቸው። ረዘም ያሉት ደግሞ ‘ሰቀላ’ ተብለው ይታወቃሉ” ብሏል። ይህ ቃል በኋላም በ18ኛው ክፍለ-ዘመን በጎንደርም ጥቅም ላይ ውሏል። በአፄ ባካፋ ዘመን ወርቅ ሰቀላ (በወርቅ የተለበጠ ሰቀላ) ወይም መልካም መዓዛ ያለው ቤተ-መንግሥት እንደማለት።

 በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ትላልቅ ባለ አራት ማዕዘን ሰቀላዎች በኢትዮጵያ ተስፋፍተው እንደነበር ይታወቃ። በትግራይ በንጉሥ ሳህለሥላሴ ዘመን ደግሞ በአንኮበር ሰቀላዎች መስፋፋታቸው ይታወቃል። በርናትዝ እንደገለፀው “ንጉሡ (ሳህለሥላሴ) አልጋው ላይ ጋደም ብሎና አጃቢዎች ተቀምጠው፣ ሮሪሳ ዳዲ ወታደሮቹ በጉራዴ እና ጋሻቸው ይዘው በተጠንቀቅ ቆመው፣ አዝማሪዎች እና እስክስታ ወራጆች ያዝናኑታል” ሲልጽፏል። የዳግማዊ ምንሊክም ሁኔታ ከዚህ እንዳልተለየ በማሳጃ (Massaja) ማስታወሻ ሰፍሯል።

 ከእልፍኝ እና ከአዳራሽ በተጨማሪ ሌሎች ክፍሎች በግቢው ይገኛሉ። ማዕድ ቤት፣ ፈረስ ቤት (stables)፣ ሥራ ቤቶች፣ የባለ እጆች ወዘተ… ቤቶች ይገኛሉ። ከዚህ ሁሉ ደግሞ ሰገነት የተለየ ሥፍራ ሲሆን ህዝቡ ፍትህን ለማግኝት የሚያመለክትበት ሥፍራ ሲሆን ቋሚ ተመልካች ዘብም በዚያው ሥፍራ ይቆምበታል። በተመሳሳይ መልኩ በደብረ- ማርቆስ እንደነበር ፓንክረስት ጽፎታል። በግቢ ውስጥ ብዙ አሽከሮች፣ ሠራተኞች፣ ባለእጆች ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ ባለሥልጣናት ብላታ ጌታዎች፣ በጅሮንድችና አጋፋሪዎች፣ ባልደረባዎች እና አሳላፊዎች ናቸው።

የቱሉ – ፊንፊኔው ግቢ (ቤተ-መንግሥት) በ1889 እ.አ.አ. የተገነባ ሲሆን በ1892 እ.አ.አ. ተቃጠለ። ወዲያው ግን በአስቸኳይ እንዲገነባ ተደረገ። የቤተ-መንግሥቱ ወለል በማራብ ምልከታ ሁለት ኪሎ ሜትር በአንድ ኪሎ ሜትር ስፋት ሲኖረው 7,000 የቤተ- መንግሥት ሠራተኞች አሉት። ከነዚህ ውስጥ 2000 የሚሆኑት የንጉሡ የግል አገልጋዮችና አጃቢዎች ናቸው።

 የቤተ-መንግሥቱ የውሃ አቅርቦት በሲዊዛዊው ኢልግ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን የኤሌክትሪክ መስመር የተዘረጋው ደግሞ በጀርመን የዲፕሎማቲክ ሚሲዮን በ1905 (እ.አ.አ.) ነበር። የግቢው ትልቅነት በአራት እና በአምስት ዙር 20,000 ጎብኚዎችን ለማስተናገድ ይችል እንደነበር የተለያዩ ጸሐፍት ፓንክረስትን ጨምሮ ጽፈዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top