ታሪክ እና ባሕል

የመስቀል አበባ

የመስቀል አበባ

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሞስኮብ፣ ግብፅ፣ ካናዳ፣… ለአንድ አገር… ወደሚሰጠው ወደ… የባህል ሳይንስ… የቡልጋሪያ ሕዝብ… ድረስ ከቆየች በኋላ ወደ አገርዋ ትመለሳለች። …ከኢትዮጵያ የምትወጣ ይሆናል። ከመሄዷ በፊት በጥንቃቄ… በኤክስሬይ ታይታ የተሟላ ጤንነት እንዳላት ተረጋግጧል። ለዚህም ጉዞዋም ከተዘጋጀት በኋላ ለህይወትም ከ፬፻፳፭ ሺ ብር በሚበልጥ ሂሳብ ዋስትና (ኢንሹራንስ) ተሰጥቶታል። ፈጣሪዋ የሆነው አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ግን ከሁለትና ከሶስት ሚሊዮን ብር ይልቅ የመስቀል አበባ ፍጡሩን ይፈቅዳል።

 የአፈወርቅ የመስቀል አበባ ከሌሎች ስዕሎቹ እጅግ አጭር ጊዜ የፈጀች ናት። ሦስት ወር ብቻ ነው የፈጀብኝ ይላል ስመ ጥሩ ሰዓሊዋ። ሌሎች ብዙ ዓመት የበለጠ የፈጁ ሥዕሎች አሉት። ይሁንና ይህች ሥዕል ከብዙዎቹ የአፈወርቅ ድንቅ ሥራዎች መካከል ከፍተኛ ሥፍራ የተሰጣት መስላለች። በዚህ የተነሳ ብዙ ርቀት ተጉዛለች። በብዙ አገሮች ፊልም ተነሥታ ለህዝብ ታይታለች።

የመስቀል አበባ ስለ ኢትዮጵያ የኪነጥበባት ባህል ለመመራመር የሚፈልጉ የኢትዮጵያ የሥዕል ጥበብ ለማድነቅ የሚመኙ ሰዎች ሊያይዋት የሚፈቅዱት ግሩም ዓይነት “ፍጡር” ናት። በሁለት አግዳሚ መስመር ላይ ቀለም የፈሰሰበት ሸራ አይደለችም። ዘመናዊት የኢትዮጵያዊት ምሳሌ ናት። ልክ አፈወርቅ “እናት ኢትዮጵያ” ብሎ እንደሰየማት ሥዕል ማለታችን ነው።

የመስቀል አበባን አፈወርቅ ከሳላት በኋላ ለአንድ የውጭ አገር ሰው ሸጧት ነበር። በኋላ ቆጨውና ከግማሽ በላይ ገንዘብ ጨምሮ መልሶ ገዛት። ከኢትዮጵያ መውጣት የማይገባት የኢትዮጵያዊነት ምሳሌ ልትሆን ትችላለች የሚለው እምነት በአፈወርቅ የጎለመሰው እያደር ነበር። ዛሬ የመስቀል አበባ ዋጋ ከወትሮው እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ አይካድም። እንደሞናሊዛ ሁሉ ዋጋዋ ዛሬ በአርቲስቱ ግምት ከአኀዝ ውጭ ነው። አፈወርቅ ሊሸጣት አይፈልግም። ለእሱ ትልቅ ሶፊያ ትርጉም ትሰጠዋለች። የሕይወት፤ የውበት፤ የኢትዮጵያዊነት፤ የባህል፣ የአለባበስ የሥነ ምግባር ጥራት ምሳሌው ናት። የመስቀል አበባ።

 መነን መፅሔት፤… ፩ ቀን ፲፱፻፰፫ ዓ.ም

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top