የታዛ ድምፆች

ከፌስ ቡክ

በመኳረፍ መተላለፍ

 ባልና ሚስቱ ተኳርፋው አይነጋገሩም አሉ:: ቤቱ እንደ መቃብር በጸጥታ ተውጦ ከርሟል:: አንድ ቀን ባል ሌሊት አሥር ሰዓት የሚነሣበት ጉዳይ ገጠመው:: ከተኛ መነሣት የሚከብደው ቢጤ ነበርና የመቀስቀሻውን ሰዓት ሊሞላ ሲስበው ተበላሽቷል:: አዘነም፤ ተናደደም:: ምን ያድርግ:: ባለቤቱ ገና ከሥራ አልገባችም:: ‹የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይመርጡ› ነውና:: በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ላይ ቀስቅሽኝ› ብሎ ጽፎ በራስጌው ባለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠና ተኛ::

 ሚስቱ ስትመጣ አየችውና ስቃ ተኛች:: ልክ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ነቃችና በዚያው በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ሆኗልና ተነሣ› ብላ ጽፋለት ተኛች:: እርሱ ዕንቅልፉን ለጥጦ ለጥጦ ሲነሣ ነግቷል:: ተናደደ፤ ግን እንዳይናገራት ለካስ ተኳርፈዋል:: እዚያው ወረቀት ላይ ‹በጣም ታሳዥኛለሽ› ብሎ ጻፈላት::

 /የዳንኤል ክብረት “ፓርኪንግ” በሚል ርእስ በብሎኩ ከጻፈው የተቀነበጨበ

የማሞ እውነት

ማሞ የእትየ ይመናሹ ጎረቤት ልጅ ነው፤ አንዳንዴ እትየ ይመናሹ ቤት ይመጣና ከልጆቻቸው ጋር ተደባልቆ ይቀመጣል፤ ሌሎች ሲያወሩ፤ማሞ ዝም ይላል፤እትየ ይመናሹ፤የማሞ ጭው ያለ ዝምታ ያስገርማቸዋል፤ እንዴት ያለ ጭምት ልጅ ነው! እያሉ ያደንቁታል፤ አልፎ አልፎ ግን ያሳዝናቸዋል፤

 አንድ ቀን “ልጅየ ለምን አትጫወትም?” “አየ! እናቴ እንዳትጫወትህ አፍህ ባለጌ ነው ፤ሰው ታስቀይማለህ፡” ብላኛለች ይላል ማሞ፤

 እትየ ይመናሹ ይሄን የመሰለ ልጅ ታፍኖ መኖሩ አሳዝኑዋቸው “ እናትህን አትስማት፤ አፍህ ማር ነው፤ ተጫወት፤ ‘በለው ጎተጎቱት፤

 “እንግዲህ ተጫወት ካላችሁኝ አለና ማሞ የጨዋታ ጭብጥ ፍለጋ፤ዙርያ ገባውን ተመለከተ፤ ከፊትለፊቱ ትልቅ ራስ ያለው የትየ ይመናሹ ልጅ ቁጭ ብሉዋል፤

 “እንግዲህ ተጫወት ካላችሁኝ… የሄ አናታም ልጅ እንዴት ሆኖ ተብልትዎ ወጣ?” “እውነትም አፍህ ባለጌ ነው” አሉ እትየ ይመናሹ እሳት ጎርሰው ፤

 “ተናግሬ ነበር!” አለና ማሞ ወደ ዝምታው ተመለሰ፤

 /በእውቀቱ ስዩም “እንደማመጥ” በሚል ርእስ ከጻፈው መልእክት የጠቀነጨበ

ቻርጅ እና ቻርጀር

በሞባይል ስልክ ስርቆት ተጠርጥሮ ክስ የቀረበበት አንድ ግለሰብ በቀጠሮው ቀን ፍርድ ቤት ሲቀርብ ዳኛው ‹‹ቻርጁ ደርሶሃል?›› ሲሉ ይጠይቁታል፡፡ ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ የዳኛውን ጥያቄ በወጉ ያልተረዳው ተከሳሽ “የምን ቻርጀር?” እኔ የወሰድኩት ሞባይል ብቻ ነው” በማለት ፈጣን ቃሉን ሰጥቷል፡፡

ሆዴ ድመቱ አለ?”

ሰውየው የሚስቱን ድመት በጣም ይጠላ ነበር….አንድ ቀን ሚስቱ ሳታየው ድመቱን አውጥቶ ለመጣል ይወስናል በጠዋት ተነስቶም ድመቱን 20 ኪሎሜትር ያህል ራቅ አድርጎ ይጥልና በደስታ ይመለሳል እቤቱ ሲደርስ ግን ድመቱ ሶፋ ላይ ተኝቶ ያገኘዋል.. በነጋታው ጠዋት ይነሳና ድመቱን 40 ኪሎሜትር ራቅ አድርጎ ጥሎት ተመለሰ እቤት ሲደርስ ድመቱ እንደ ትላንቱ ሶፋ ላይ ተኝቶ ያገኘዋል በየቀኑ ራቅ ራቅ ወዳለ ቦታ እየጣለው ያመጣል ድመቱ ግን ሁሌም ቀድሞት እቤት እንደገባ ነው:: በመጨረሻም በጣም ይመረውና ድመቱ አያውቀውም ብሎ ወደሚያስብበት ሩቅ ቦታ ሊጥለው ይወስናል ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ከተጓዘ በኃላ ወደ ቀኝ ታጠፈ ከዛ ወደ ግራ ከዛወንዙን ተሻግሮ ወደ ቀኝ ድጋሜ ወደ ግራ አሁንም ጥቂት ተጉዞ ወደ ቀኝ እንዲ እንዲ እያለ የሆነ ቦታ ሲደርስ አሁን ተገላገልኩ ብሎ ድመቱን ይለቀዋል….ከሰአታት በኃላ ሰውየው ሚስቱጋ ደውሎ፤

 “ሆዴ ድመቱ አለ እንዴ?”

 ሚስት ” አዎ ምነው….?

 “እስቲ አንዴ አቅርቢልኝ መንገድ ጠፍቶብኛል”

የባል ኑዛዜ

ባል ጣዕረ-ሞት ይዞት እያጣጣረ ሳለ ሚስቱን ያስጠራና “እንግዲህ እኔ መሞቴ ነው፤ አንቺ ግን ያለ ባል መቅረት የለብሽም፤ እንዲያውም ያንን ኩራባቸውን አግቢ” ይላታል። በዚህ አባባል የተናደደችው ሚስት “አንተን ይማርልኝ እንጂ እኔ አሁን ስለ ባል አላስብም! ደግሞ ባገባስ እንዴት ያንተን ዋነኛ ጠላት ኩራባቸውን አግቢ ትለኛለህ?” ስትል ትጠይቀዋለች። በዚህ ጊዜ ጣር የያዘው ባል እያቃሰተ መለስ ብሎ “አንቺ ደሞ አይገባሽም እንዴ? ጠላቴ መሆኑንማ መች አጣሁት? ልክ እንደ እኔ አንገብግበሽ እንድትገድይልኝ ነው እንጂ! አላት ይባላል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top