ታሪክ እና ባሕል

በኢትዮጵያ የቱሪዝም ልማት ዘርፍ የመንግስት ተግባራት (ከ1950 – 1983

ባለፈው ዕትም ‹‹ስለ ቱሪዝም አንዳንድ ነጥቦች›› በሚል ርዕስ ጥቅል ሃሳቦችን በደምሳሳው ለማቅረብ ሞክሬያለሁ። በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ለማግኘት በቻልኳቸው ሰነዶች ላይ በመመርኮዝ በዘውዳዊውና በወታደራዊው መንግስታት የልማት ዕቅዶች ውስጥ የቱሪዝም ዘርፍ የልማት ትልም ምን ምን ላይ ያተኮረ እንደነበር ለማመልከት እሞክራለሁ። ጽሑፉ ከነፃነት መመለስ በኋላ ከነበሩት ዓመታት ይጀምራል።

 ከጣሊያን ወረራ በኋላ በነበረው የንጉስ ኃይለ ሥላሴ ዘመንና ኋላም በወታደራዊው መንግስት ዘመን በመንግስት የአምስት ወይንም የዓመት ዕቅድ ውስጥ የቱሪዝም ልማት የተለየ ስፍራ ይሰጠው ነበር። የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የመጀመሪያው የአምስት ዓመት የልማት ፕላን የተዘጋጀው በ1954 ዓ.ም ነበር። በዚያው ዓመት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ተቋቋመ። የድርጅቱ ተጠሪነትም ለማስታወቂያና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነበር። ከዚህ በኋላ በተከታታይ ሁለት የአምስት ዓመት የልማት ፕላኖች ተዘጋጅተው ተግባራዊ ሆነዋል። ሁለተኛው ፕላን ከ1955 እስከ 1959፣ ሦስተኛው ደግሞ ከ1960 እስከ 1965 ለነበሩት ዓመታት የተዘጋጀ ነበር።

የቱሪዝም ዘርፍ ልማት 1955-1959

በአጼ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛው የአምስት ዓመት የልማት ፕላን ውስጥ የቱሪዝም ዘርፍ የተጠቀሰው ‹‹ማስተናገድና ቱሪዝም›› ተብሎ ነበር። ‹‹ማስተናገድ›› የሚያመለክተው ከአነስተኛ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች ግንባታና አገልግሎት ጋር የተያያዘውን ተግባር ነበር። በዚህ የልማት ዘመን ሆቴሎች የሚስፋፉት ከፍ ባሉት ከተሞችና ቱሪስቶች በሚሄዱባቸው ስፍራዎች እንደነበር፣ ሆቴሎችን ለማስፋፋት የሚያስችል ብዙ የሀገር ውስጥ የግል ካፒታል ባለመኖሩ መንግስት በመስኩ መሳተፍ ባለፈው ዕትም ‹‹ስለ ቱሪዝም አንዳንድ ነጥቦች›› በሚል ርዕስ ጥቅል ሃሳቦችን በደምሳሳው ለማቅረብ ሞክሬያለሁ። በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ለማግኘት በቻልኳቸው ሰነዶች ላይ በመመርኮዝ በዘውዳዊውና በወታደራዊው መንግስታት የልማት ዕቅዶች ውስጥ የቱሪዝም ዘርፍ የልማት ትልም ምን ምን ላይ ያተኮረ እንደነበር ለማመልከት እሞክራለሁ። ጽሑፉ ከነፃነት መመለስ በኋላ ከነበሩት ዓመታት ይጀምራል። ከጣሊያን ወረራ በኋላ በነበረው የንጉስ ኃይለ ሥላሴ ዘመንና ኋላም በወታደራዊው መንግስት ዘመን በመንግስት የአምስት ወይንም የዓመት ዕቅድ ውስጥ የቱሪዝም ልማት የተለየ ስፍራ ይሰጠው ነበር። የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የመጀመሪያው የአምስት ዓመት የልማት ፕላን የተዘጋጀው በ1954 ዓ.ም ነበር። በዚያው ዓመት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ተቋቋመ። የድርጅቱ ተጠሪነትም ለማስታወቂያና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነበር። ከዚህ በኋላ በተከታታይ ሁለት የአምስት ዓመት የልማት ፕላኖች ተዘጋጅተው ተግባራዊ ሆነዋል። ሁለተኛው ፕላን ከ1955 እስከ 1959፣ ሦስተኛው ደግሞ ከ1960 እስከ 1965 ለነበሩት ዓመታት የተዘጋጀ ነበር።

የቱሪዝም ዘርፍ ልማት ከ1955-1959 በአጼ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛው የአምስት ዓመት የልማት ፕላን ውስጥ የቱሪዝም ዘርፍ የተጠቀሰው ‹‹ማስተናገድና ቱሪዝም›› ተብሎ ነበር። ‹‹ማስተናገድ›› የሚያመለክተው ከአነስተኛ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች ግንባታና አገልግሎት ጋር የተያያዘውን ተግባር ነበር። በዚህ የልማት ዘመን ሆቴሎች የሚስፋፉት ከፍ ባሉት ከተሞችና ቱሪስቶች በሚሄዱባቸው ስፍራዎች እንደነበር፣ ሆቴሎችን ለማስፋፋት የሚያስችል ብዙ የሀገር ውስጥ የግል ካፒታል ባለመኖሩ መንግስት በመስኩ መሳተፍ እንደሚገባው ተመልክቷል። በአዲስ አበባና በአሰብ ወደብ አካባቢ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ተጠቅሷል። በዚህ ረገድ ከ600 እስከ 800 አልጋዎች ያሏቸው ከሦስት እስከ አምስት የሚደርሱ ሆቴሎችን በመገንባት በሀገሪቱ የሚገኙ የሆቴል አልጋዎችን ቁጥር 20 በመቶ ከፍ ለማድረግ ታቅዶ ነበር። የፕላን ዘመኑ ሲያበቃ በተጠናቀረው ሪፖርት መሰረት ስራቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁትን ባለ ብዙ ክፍል ሆቴሎች ሳይጨምር 1590 አልጋዎች ያሏቸው በርካታ ሆቴሎች ተሰርተው ስራ ጀምረው ነበር።

 ከዚህ በተጨማሪ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ሆቴሎችንና የትራንስፖርት አውታሮችን በሚገባ አደራጅቶ በርከት ያሉ ጐብኚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ ስለ ሀገሪቱ መግለጫ የሚሰጡ የቱሪስት ቢሮዎችን በውጭ ሀገሮች ማቋቋም አንዱና ዋናው ተግባር ነበር።

በሁለተኛው የአምስት ዓመት የልማት ፕላን ዘመን በድምሩ 118,690 የሚሆኑ ቱሪስቶች ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ፣ ከአፍሪካና ከሌሎች ሀገሮች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ኢትዮጵያን የጐበኙ ሲሆን የእያንዳንዱ ቱሪስት አማካይ የቆይታ ጊዜ አራት ቀናት፣ እለታዊ ወጪ ደግሞ ብር 66 እንደነበር ተገምቷል። ከ1956 እስከ 1958 ዓ.ም በነበሩት ሦስት ዓመታት የቱሪስት ቁጥር ዓመታዊ እድገት እንደ ቅደም ተከተሉ 3 በመቶ፣ 28 በመቶና 33 በመቶ ነበር።

የቱሪዝም ልማት ከ1960-1965

 ሦስተኛው የአምስት ዓመት የልማት ፕላን ሲዘጋጅ መንግስት በሁለተኛው የአምስት ዓመት የልማት ፕላን በቱሪዝም ጉዳይ ብዙም ያልተቸገረበት እንደነበር በትችት መልክ ተቀምጧል። ይህን መነሻ በማድረግ በፕላን ዘመኑ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍ ያለ ጥቅም ሊያስገኝ የሚችል ‹‹ኢንዱስትሪ›› እንደሆነ በውል ተጠቅሶ የፕላኑ ዋና ስራ በየክፍሉ የሚደረገውን ድካም ማቀናጀትና የሚያስፈልገውን መመሪያ (ፖሊሲ) በየመልኩ ማቅረብ እንደሆነ ተጠቁሟል።

 በፕላን ሰነዱ ውስጥ ‹‹አንድ የተባበረና የተዋሃደ የቱሪዝም እድገት ፕሮግራም መኖር እንዳለበት፣›› ይህም የሆቴሎችንና የመገናኛ ችግሮችን ብቻ ሳይሆን መንግስት በቱሪዝም ኢንዱስትሪ መስክ ሊይዝ የሚገባውን አቋም፣ የግል ባለሃብቶች ተሳትፎና ድርሻ እስከምን ድረስ እንደሆነ፣ በተጨማሪም ‹‹ለልማቱ ስራ የሚፈለገውን የካፒታል ቅደም ተከተልና የታሰቡትን ድርጅቶች›› የሚያመለክት መመሪያ መዘጋጀት እንዳለበት ተጠቅሷል። ይልቁንም በ1961 ዓ.ም የሚጀመር አንድ ሰፊ ጥናት በውል ላልተጠቀሰ አጥኚ አካል መሰጠቱን፣ የጥናቱም ዓላማ ‹‹መንግስት የቱሪዝምን መስፋፋት የሚያፋጥንበትን ዘዴ ለመሻትና ተፈላጊውንም ጥቅም በተሟላ አኳኋን እንዲያገኝ ለማስቻል›› እንደሆነ ተጠቁሞ ነበር።

በሦስተኛው የአምስት ዓመት የልማት ዘመን የመንግስት ዋና ዋና ሃላፊነቶች ተብለው የተለዩት የሚከተሉት ስድስት ተግባራት ነበሩ፡-

1. ከዋናው የቱሪዝም ፕላን ጋር በተጣጣመ መልኩ ለግል ባለሃብቶች ተሳትፎ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት፣

 2. አስፈላጊ የሆኑ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለመገንባት ከግል ባለሃብቶች በቂ ካፒታል በማይኖር ጊዜ ለዚሁ ስራ የሚውል መዋዕለ ነዋይ በቀጥታ ማውጣት፣

3. የግል ባለሃብቶች የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለመገንባት እንዲችሉ የመገናኛና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮችን አስቀድሞ ማሟላት፣

 4. ቅድሚያ ትኩረት በተሰጣቸው የመስህብ ስፍራዎች አካባቢ ባለሃብቶች ተስማሚ ሆቴሎችን እንዲገነቡ ማበረታታት፤ አሊያም ለዚሁ ስራ መንግስት ቅድሚያ መውሰድ ካለበት የንግድ ውድድር ባለበት ሁኔታ እንዲሆን፣

5. በቱሪዝም ዘርፍ ልማት መንግስት የሚያወጣው ደንብና መመሪያ ለጠቅላላ ልማት አመቺ መሆን ስላለበት በየደረጃው የሚዘረጉት የመገናኛና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደረጃቸውን የጠበቁና የጐብኚዎችን ምቾት የማይቀንሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣

 6. ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታ የሚያስፈልግ ብድር ከመንግስት ባንኮች እንዲገኝ ልዩ አስተያየት ማድረግ፣ ከገቢ አንፃር በልማት ዘመኑ መጀመሪያ ዓመት ላይ ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ብር 9.5 ሚሊዮን እንደሚሆንና በልማት ዘመኑ መገባደጃ ይህ ገቢ ወደ ብር 35 ሚሊዮን እንደሚደርስ ተገምቶ ነበር።

 የቱሪስቱ አማካይ የቆይታ ጊዜ በሁለት ቀናት እንዲጨምር በማድረግ ገቢውን 50 በመቶ ከፍ ማድረግ እንደሚቻልም ታሳቢ ተደርጐ ነበር።

በእነኚህ አምስት ዓመታት ውስጥ በቅደም ተከተል እንዲለሙ ትኩረት ተሰጥቷቸው የነበሩት ስፍራዎች የሚከተሉት ነበሩ፡-

 1. በአዲስ አበባ የሚገኙ ስፍራዎች (ለምሳሌ አዋሽ ፓርክ፣ የስምጥ ሸለቆ ሃይቆች፣ ወዘተ። በተጨማሪም በአዲስ አበባና በባህር ዳር መካከል አባይ ወንዝ አጠገብ አንድ ቱሪስት-መጥን ሆቴል ለማቋቋም ታስቦ ነበር)

 2. የጋምቤላ አካባቢ (በተለይ ለአደን)

3. ድሬዳዋና ሐረር

 4. አስመራና የቀይ ባህር አካባቢ

 5. ታሪካዊው የጉዞ መስመር (ባህር ዳር፣ ጐንደር፣ ላሊበላና አክሱም)

6. ብሄራዊ ፓርኮችን በህግ ማቋቋም፣ የዱር አራዊት ጥብቅ ክልሎችን መወሰን፣ የዱር እንስሳትን በተመለከተ ጥናትና ምርምር እንዲካሄድ ማበረታታት

 በልማት ዘመኑ ለመስኩ የሚያስፈልገው ጠቅላላ የልማት ወጪ (ከመንግስትና ከባለሃብቶች የሚጠበቀውን ካፒታል አጠቃሎ) ብር 27 ሚሊዮን ነበር። የበጀት ድልድሉ የሚከተለውን ይመስላል፡-

1. የሒልተን ሆቴል ግንባታን ሳይጨምር ለአዳዲስ ሆቴሎች ግንባታና ነባሮችን ለማሻሻል ብር 20 ሚሊዮን፣

 2. ለተሽከርካሪ ግዥ፣ ለህንፃዎች ግንባታ፣ ለመንገዶች ስራና ጥገና ብር 2.03 ሚሊዮን፣

3. ለቱሪዝም ጥናትና ለሰራተኞች ስልጠና ብር 2.07 ሚሊዮን፣

4. ለኤክስፖ መንደሮች ማቋቋሚያ፣ ለላንቲካና ለዕደ ጥበብ ውጤቶች ብር 1.4 ሚሊዮን፣ 5. ለፓርኮችና ለአራዊት ጥብቅ ክልሎች ልማት ብር 1.5 ሚሊዮን 6. ቱሪዝም በወታደራዊው መንግስት ዘመን (ከ1967-1983)

 ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1970 ዓ.ም ድረስ የነበሩት አምስት ዓመታት ምስቅልቅል የበዛባቸው የአብዮት ዓመታት በመሆናቸው ስለ ሀገር ኢኮኖሚ በአጠቃላይ፤ ስለ ቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚ በተለይ ምን ተተልሞ እንደነበር የሚያስረዱ ሰነዶችን በቀላሉ ማግኘት (ለዚያውም ካሉ) አይቻልም። ይሁን እንጂ ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ የኀብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት (ኀኢጊወመ) ‹‹የብሄራዊ አብዮታዊ የምርትና የባህል ዕድገት ዘመቻ›› በተሰኘ ተቋም-መሰል ንቅናቄ አማካይነት ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕቅድ እየተዘጋጀ ተግባራዊ ሲሆን ቆየ። በኋላም ይህ አካሄድ በአስር ዓመት መሪ ዕቅድ ተተክቶ ትልሙን ስትራቴጂያዊ ለማድረግ ተሞክሯል። የኀ.ኢ.ጊ.ወ.መ የመጀመሪያው የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ ከ1977 እስከ 1986 ዓ.ም ድረስ የነበሩትን አስር ዓመታት ያካተተ ነበር። ከ1970 እስከ 1976 ዓ.ም ድረስ በነበሩት ዓመታት ተከታታይ ዓመታዊ ዕቅዶች የነበሩ ይመስላል። ለምሳሌ በብሄራዊ አብዮታዊ የምርትና የባህል ዕድገት ዘመቻ ሁለተኛ ዓመት ዕቅድ ውስጥ የቱሪዝም ዘርፍ ‹‹ቱሪዝምና ሆቴል›› በሚል ስያሜ ተለይቶ የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት ታስቦ ነበር።

 1. የሀገሪቱ የቱሪዝም እንቅስቃሴ መልሶ እንዲያንሰራራ የሚያስችል የቱሪዝም ፖሊሲ ማውጣት፣

 2. በሀገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች ስለሚገኙት መንግስታዊና የግል ሆቴሎች ጠቅላላ አቅምና የአገልግሎት ደረጃ አጠቃላይ ግምገማ ማከናወን፣

3. የመንግስታዊ ሆቴሎችን ትርፍ ማሳደግ ወይንም የኪሳራቸውን መጠን መቀነስ፣ እነኚህን ዓላማዎች ለማስፈጸም ተነድፈው የነበሩት ሁለት ስልቶች ነበሩ። አንደኛው ስልት ስለመንግስትና የግል ሆቴሎች አቋም፣ እንዲሁም ስለሌሎች ደጋፊ አገልግሎቶች አጠቃላይ ጥናት ለማካሄድ በዕርዳታ ወይንም በክፍያ መልክ የውጭ ሀገር ባለሙያዎችን መቅጠር ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የመንግስት ሆቴሎችን የትርፍና ኪሳራ አቋም ለማሻሻል ያለመ ነበር። በተለይ ሁለተኛውን ትልም እውን ለማድረግ የተወሰዱ ሦስት እርምጃዎች ነበሩ። እነርሱም የወጪ ቁጠባ ኘሮግራም ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፣ የቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ብክነት ለመቀነስ የምዝገባ፣ የቁጥጥርና የእንክብካቤ ስርዓት መዘርጋትና አነስተኛ የመንግስት ሆቴሎችን አቋም በመመርመር የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ፤ የሚዘጉትንና የሚስፋፉትን ለይቶ ለመንግስት የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ ነበሩ።

የ1972ቱ ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ያስገኘው ውጤት ምን እንደነበር ባይገለጽም በዚህ ዓመት ከተከናወኑት አበይት መዋቅራዊ ለውጦች ዋነኛው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን መቋቋሙ ነበር። በተከታዩ የ1973 ዓ.ም ዕቅድ የቱሪዝም ዘርፍ ዓላማዎች በአራት ዋና ዋና ተግባራት ላይ እንዲያተኩሩ ታልሞ ነበር። ዓላማዎቹም፡-

 1. የመስህብ ሃብቶችን ለውጭ ሀገር ጐብኚዎች በማስተዋወቅ የውጭ ምንዛሬ ገቢን ከፍ ማድረግ፣

 2. የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማበረታታትና ማስፋፋት፣

3. የመንግስት ሆቴሎችንና የቱሪዝም ድርጅቶችን ማጠናከርና ትርፋማ ማድረግ፣ አክሳሪዎቹ ከኪሳራ የሚወጡበትን መንገድ መፈለግ፣

 4. በዘርፉ የተሰማሩ የግል ባለሃብቶች እንቅስቃሴ ስርዓት እንዲይዝ ማድረግ ነበሩ።

ከመዋቅር ማሻሻል አንፃር በግልና በአክሲዮን መልክ ተቋቁመው የነበሩ ሆቴሎችን፣ ምግብ ቤቶችንና መዝናኛ ስፍራዎችን በመውረስ የኢትዮጵያ ሆቴሎችና መዝናኛ ስፍራዎች ማስፋፊያ ኮርፖሬሽን ተቋቋመ። የብሄራዊ አስጎብኚ ድርጅትም የተቋቋመው በዚሁ ጊዜ ነበር።

በአራተኛውና በአምስተኛው ዓመት የምርትና የባህል ልማት ዓመታዊ ዕቅዶች ውስጥ የቃላት ለውጥ ካልሆነ በስተቀር የቱሪዝም ዘርፍ ልማትን በተመለከተ ከ1973ቱ ዓመታዊ ዕቅድ የተለወጠ ነገር አልነበረም። በዕቅድ ሰነዱ ውስጥ እንደተጠቀሰው የቱሪስት ቁጥር መቀነስን በተመለከተ ‹‹ለአብዮቱ እንክብካቤ ሲባል በቱሪስቶች አመጣጥ ጉዳይ ላይ ጊዜያዊ ገደብ በመደረጉ የተጠበቀውን ያህል [ቱሪስት ለመሳብ] አልተቻለም ነበር።›› ሆኖም በ1973 በጀት ዓመት ውስጥ ቱሪዝም ለኢኮኖሚው ግንባታ አስተዋጽዖ እንዲያደርግ የሚያስችለው የቱሪዝም ፖሊሲ ወጥቶ ተግባራዊ በመሆን ላይ እንደነበር በዕቅድ ሰነዱ ውስጥ ተጠቅሷል።

 በሌላ በኩል በታሪካዊ ስፍራዎች አካባቢ በመሰራት ላይ ከነበሩት ሆቴሎች መካከል የዘርዓይ ደረስ ሆቴል ማሻሻያ (በአሰብ)፣ የአዲስ አበባ ፍልውሃ ሻወር፣ የሶደሬ ሆቴል ማስፋፊያ፣ የነቀምቴ ኢትዮጵያ ሆቴል ማስፋፊያና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል (በባሌ ጎባ) ለበርካታ ዓመታት ባለመጠናቀቃቸው በየዓመታዊ ዕቅዱ ሲጠቀሱ የነበሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ነበሩ።

 የቱሪዝም ልማት በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ (ከ1977-1986)

 በመስከረም 1977 ዓ.ም ይፋ በሆነው የወታደራዊው መንግስት የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ ውስጥ ‹‹እስከ አብዮቱ ፍንዳታ ድረስ›› የቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚ ትኩረት ያልተሰጠውና በዕቅድ የማይመራ ስለነበር ከመስኩ የተገኘው ጥቅም አነስተኛ እንደነበር ተመልክቷል። ነገር ግን ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረትና የተገኘው ውጤት የሚፈለገውን ያህል አይሁን እንጂ አነሰም በዛ በንጉሱ መንግስት ዓመታዊ ዕቅድ ውስጥ የቱሪዝም ልማት የተካተተ እንደነበር ከፍ ሲል ለማሳየት ተሞክሯል።

 የአስር ዓመቱ መሪ ዕቅድ የቱሪዝም ዘርፍ ችግሮችን በመዘርዘር ይጀምርና የዕቅዱን ዓላማዎች፣ ስልቶችና እርምጃዎች፣ እንዲሁም በዕቅድ ዘመኑ ይኖራሉ ተብለው የሚገመቱትን ቱሪስቶች ቁጥርና ይገኛል ተብሎ የሚታሰውን ገቢ ለማመላከት ሞክሯል። በመሪ እቅዱ መሰረት የቱሪዝም ዘርፍ ችግሮች የሚከተሉት ነበሩ፡-

 1. የመሰረተ ልማት አውታሮች በአግባቡ አለመሟላትና የመስህብ ስፍራዎች በእንክብካቤ አለመያዝ፣

 2. የመስህብ ሃብቶች (የዱር አራዊትን ጨምሮ) አስተዳደር በልዩ ልዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ስር የተበታተነ በመሆኑ ልማታቸውን ለማቀናጀትና ለማስተባበር አዳጋች መሆኑ፣

 3. የሆቴሎች ደረጃ ዝቅተኛነትና የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት፣

 4. የቪዛ አሰጣጥ ስርዓት፣ በመግቢያና መውጫ በሮች የሚደረገው ፍተሻ፣ በሀገር ውስጥ የቱሪስት እንቅስቃሴን በሚመለከት ያለው መመሪያ ጐብኚዎች በብዛት እንዲመጡ የማያበረታታ መሆኑ፣

 በአስር ዓመቱ መሪ ዕቅድ ውስጥ በተለዩት ችግሮች ላይ ያነጣጠሩ ሦስት ዓላማዎች ተነድፈው ነበር። እነርሱም፡-

1. የመስህብ ሃብቶችን በውጭ ሀገር ማስተዋወቅ፣ በሀገሮች መካከል የንግድ፣ የምርምርና የቱሪዝም ግንኙነቶችን በመፍጠር ለኢኮኖሚ ልማት የሚረዳ የውጭ ምንዛሬ መጠንን ማዳበር፣

2. የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲለመድ በማድረግ ብሄረሰቦች እርስ በርስ እንዲተዋወቁ በመካከላቸውም መፈቃቀር እንዲሰፍን ማድረግ፣ ‹‹ሠርቶ አደሩ የእረፍት ጊዜውን ፍሬአማ በሆነ የጉብኝት ፕሮግራም እንዲያሳልፍ›› ጥረት ማድረግ፣

 3. በከተሞች የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲስፋፉ ማድረግ ነበሩ።

ዓላማዎቹን ለማስፈጸም ተነድፈው የነበሩ ስልቶች፡-

1. ፊልሞችን፣ ስላይዶችን፣ ፌስቲቫሎችን፣ ኤግዚቢሽኖችንና የመሳሰሉትን የተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም ሰፊ የማስተዋወቅ ስራ በውጭ ሀገራት ማካሄድ፣

2. ከተለያዩ የቱሪስት ወኪሎች ጋር በመቀራረብ ጐብኚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ መሳብ፣

 3. የውጭ ምንዛሬን ለማሰባሰብ የአገልግሎት ተቋማትን ደረጃና ቁጥር ማሳደግ፣ የዕደ ጥበብ ውጤቶችን ጥራትና የስጦታ ዕቃዎችን ማጐልበት፣

 4. የቪዛ፣ የባንክና የጉምሩክ ስርዓቶችን ማሻሻልና የሀገር ውስጥ መዘዋወሪያ ደንቦችን ማስተካከል፣

 5. የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን፣ የስብሰባ ማዕከላትንና የማጓጓዣ መሳሪያዎችን ማሟላትና ማስፋፋት፣

6. የመስህብ ሃብቶችን ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ለማደራጀት በሚደረገው መንግስታዊ፣ ህዝባዊና ዓለም አቀፋዊ ጥረት አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ፣

 የቱሪስት መስህብ ሃብቶችን በተለያዩ የማስታወቂያ ዘዴዎች በማስተዋወቅና በመመዝገብ፤ ‹‹የሀገርህን እወቅ›› ክበባትን በመንግስት፣ በህዝባዊ ድርጅቶች፣ በሙያ ማህበራትና በትምህርት ቤቶች በማቋቋም፤ እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ቱሪስቶች አመቺ የሚሆኑ የአገልግሎትና የመገናኛ ተቋማትን በማደራጀት፣ ዋጋዎቻቸውን በመቆጣጠርና በማሻሻል የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማዳበር ታልሞ በተቻለ አቅም እንቅስቃሴ ተደርጐ ነበር። ስርዓቱ የሶሻሊዝም ነበርና ቁጥጥር የእርምጃው ዋና አካል ነበር። በዚህ መሰረት ለምሳሌ፣ የሆቴል አገልግሎትን ለማስፋፋት ‹‹የመንግስትና የህዝባዊ ድርጅቶች ማረፊያ ስፍራዎች›› የሚባሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን  በማቋቋም፣ ‹‹መንግስት በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ግለሰቦች›› ሆቴሎችን እንዲያቋቁሙ በመደገፍ የአገልግሎት ዋጋዎቻቸውን ሁኔታ መቆጣጠር እንደ ዋና ዋና እርምጃዎች ተወስደዋል።

 የቱሪስቶችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ የተጣሉ ግቦች

 በ1975 ዓ.ም የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ቁጥር 64,000 እንደነበርና ከዚሁም ውስጥ 18,000 ለዕረፍት፣ 9,000 ለስራ፣ 5,000 ለስብሰባ፣ ቀሪዎቹ 32,000 ደግሞ ለሌሎች ጉዳዮች የመጡ እንደነበሩ የተጠናቀሩት መረጃዎች ያሳያሉ። በ1976 ዓ.ም የውጭ ቱሪስቶች ቁጥር ወደ 71,000 እንደሚደርስ በመገመት በዕቅዱ መገባደጃ ዓመት ላይ ወደ 200,000 እንደሚያድግ ተተንብዮም ነበር።

 ሰንጠረዥ 1.

የውጭ ሀገር ጐብኚዎች ብዛት በሚመጡበት ምክንያት (በ1975፣ 1976 እና 1986)

ስም የሚመጡበት ምክንያት ጠቅላላ
ለዕረፍት ለስራ ለስብሰባ ለሌላ
1975 15,000 9,000 5,000 32,000 64,000
1976 22,000 11,000 6,000 32,000 71,000
1986 100,000 30,000 16,000 54,000 200,000

መረጃው እንደሚያሳየው በ1986 ዓ.ም ከአጠቃላይ ጐብኚዎች ውስጥ አብዛኞቹ ለዕረፍት ወይንም ለመዝናናት የመጡ ሲሆን ለስራ የመጡት 15 በመቶ፣ ለስብሰባ የመጡት 8 በመቶ፣ ለተለያዩ ጉዳዮች የመጡት ደግሞ 27 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የያዙ ነበሩ። በገቢ ረገድ በ1976 ዓ.ም ከውጭ ሀገር ጐብኚዎች ይገኛል ተብሎ የተገመተው ብር 35.5 ሚሊዮን ሲሆን በመሪ ዕቅዱ ዘመን ይህንኑ በ17.13 በመቶ ከፍ በማድረግ በ1986 ዓ.ም ብር 207.2 ሚሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ ነበር።

 ሰንጠረዥ 2. የቱሪስቶች ብዛት በአማካይ የቀን ወጪ፣ የቆይታ ጊዜ፣

የሚሰበሰብ ገቢና ጠቅላላ ገቢ በሚሊዮን ብር (በ1975፣ 1976 እና 1986)

 በ1976 ዓ.ም ወደ ሀገር ውስጥ የገቡት ቱሪስቶች ቁጥር

ዓ.ም የቱሪስቶች ብዛት አማካይ የቀን ወጪ በነፍስ ወከፍ (ብር) አማካይ የቆይታ ጊዜ የሚሰበሰብ ገቢ በነፍስ ወከፍ ጠቅላላ ገቢ በሚሊዮን
1975 64,000 96 4 364 24.6
1976 71,000 100 5 500 35.5
1986 200,000 146 7 1036 207.2

ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብዙ ልዩነት አይታይበትም። አማካይ የቀን ወጪ፣ የቆይታ ጊዜም ሆነ የነፍስ ወከፍ ገቢው በተመሳሳይ የሚታይ ነው። እስከ 1986 ዓ.ም ድረስ ይመጣሉ የተባሉ ጐብኚዎችና ይገኛል ተብሎ የታቀደው ገቢ 1983 ላይ በተካሄደው የመንግስት ለውጥ ተስተጓጉሏል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top