ከፌስ ቡክ

ከፌስ ቡክ የማህበራዊ ሚድያ ተፅዕኖ

አባት: ” ኧረ ተው ልጄ፤ ፌስቡክ አጠቃቀምህ ልክ ይኑረው!”

ልጅ: ” አባየ “ኮሜንትህን” ተቀብያለሁ። ግን ሁሌም “ኦንላይን” መሆኔ ምን ችግር አለው?”

አባት: “ችግር አለው እንጅ! ፌስቡክ ላይ ከማዘውተርህ የተነሳ ባህል ወጋችን ዘነጋሀው እኮ።”

ልጅ: “አትሳሳት አባየ ስለ ባህል ወጋችን ጠንቅቄ አውቃለሁ።”

አባት: ” እስኪ እንደው በሞቴ በባህላችን መሰረት በአውዳመት ጊዜ የበግ አተራረድ ስርአታችን ምን እንደሚመስል

ከመጀመሪያው ጀምሮ ንገረኝ?”

ልጅ: “መጀመሪያ ገበያ ወጥተህ በግ “ሰርች” ታደርጋለህ።”

አባት: ” በግ ትፈልጋለህ ማለትህ ነው? እሽ ከዛስ?”

ልጅ: ” ከዛ በጉን ቤት ታመጣና መሬት ላይ “ዳውን ሎድ” ታደርገዋለህ።”

አባት: ” መሬት ላይ ትጥለዋለህ ማለትህ ነው? እሽ ከዛስ?”

ልጅ: ” ከዛማ አንገቱን “ሾርትከት” ካደረክ በኋላ ቆዳውን “ሪሙቭ” ታደርገዋለህ።”

አባት: “ወቸ ጉድ! ከባረከው በኋላ ቆዳውን ትገፋለህ ማለትህ ነው? ሆሆ! ከዛስ?”

ልጅ: “ከዛ በኋላ ሆዱን “ኦፕን” ታደርግና ሆዱ ውስጥ ያሉ “አፕሊኬሽኖች” ታወጣለህ።”

አባት: ጉድ ነው! እሽ ከዛስ?”

ልጅ: ” በመጨረሻ “አፕሊኬሽኖችን” ታወጣና “ፎልደር” ላይ ማስቀመጥ ነው።”

አባት: “ስጋው ሰሃን ላይ ታስቀምጠዋለህ ማለትህ ነው ኪኪኪኪ… ከዛስ?”

ልጅ: ” በመጨረሻም “ላይክ” ያደረግነውን የስጋ አይነት ወደ ሆዳችን “መፖሰት” ነው።

አባት: ” አንድ ነገር ረስተሃል ልጄ..ጎረቤቶቻችን “ሼር” እንዲያደርጉ “ኢንቫይት” ማድረግ አለብን!”

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

ደብረ ያሬድ አሳታሚ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በንግድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም መሰረት ተመዝግቦ በየወሩ የሚታተም በስነ-ጥበብ፣ ባህልና ትውፊት፣ ታሪክና ቅርስ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መፅሔት በ2009 ዓ.ም ተቋቋመ።

አዘጋጅ

 ስራ አስኪያጅ ፦ ዕቁባይ በርሀ
ማኔጂንግ ኤዲተሮች ፡- መኩሪያ መካሻ | ዓለማየሁ ገ/ሕይወት
ዋና አዘጋጅ ፡- ደረጄ ትዕዛዙ
አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 540
Meshetu61@gmail.com ስ.ቁ:- 0925427696

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ

ፒያሳ ቸርችል ጎዳና ከካቴድራል ት/ቤት ፊት ለፊት ካንትሪ ታዎር 7ኛ ፎቅ
ስ.ቁ:- +251 18296194 ፋክስ:- +251 11266736
ኢሜል: debreyaredpublisher@gmail.com

To Top