ቀዳሚ ቃል

ደበበን ስናስብ …

‹‹ኦሮማይ›› በተሰገኘ መጽሐፍ ሰበብ ለመጥፋት የበቃው በዓሉ ግርማ፤ አጠፋፉ የተለያዩ ሰዎችን ተጠያቂ እንደሚያደርግ ግምታዊ አስተያት ሲሰጥ ቆይቷል:: ዛሬም እውነታው የት እንዳለ ያልታወቀው ይህ ጉዳይ የተለያዩ አካላት እየተወነጀሉበት ይገኛሉ::

 ደበበ ባለበት ኃላፊነት ኦሮማይን ገምግሞ ለህትመት እንዲበቃ ሲፈቅድ በዓሉ የሚወነጀልበትን ሃሳቦች ሆን ብሎ ዘሎታል በሚል ነው የሚወቀሰው:: ይህንን ወቀሳ እሱም በህይወት እያለ በመስማቱ ሲያዝን ኖሯል::

በዚህ ጉዳይ አንድ ጽሑፍ ይዘን ቀርበናል:: ጸሐፊው ደበበ በሕይወት በነበረበት ጊዜ አነጋግሮት የሰጠውን ምላሽ እንዲሁም የዶክተር ታዬን ጥናታዊ ጽሑፍ ዋቢ በማድረግ ያዘጋጀው ነው::

 ገጣሚ፣ ጸሐፊ ተውኔትና መምህር ደበበ ሰይፉ ካለፈ እነሆ 19 ዓመት ተቆጠረ:: በእነዚህ ዓመታት በህይወት እያለ በሙያው ባበረከተው አስተዋጽኦ እሱነቱን በሚያውቁ ዘንድ ሲሞካሽ እንደነበረ ሁሉ፤ እንዲህ ከበዓሉ ግርማ ጋር በተያያዘም ስሙ ሲነሳ መሰማቱ አልቀረም:: እውነቷ እርሱ ዘንድ ያለች ቢሆንም፤ ባልተገባ መንገድ ስሙን ማጠልሸት፤ ካጠፋም እሱነቱን ከወቀሳ ማሸሽ ተገቢ አይሆንም:: ታሪክን ማዛባት ትውልድን ማሳሳት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል:: በጽሑፉ የደበበ ስራዎችና ስብዕናው እጅግ በጥቂቱ ተዳሰዋል::

በግጥምጥሞሽ ሰሞኑን አስራ ዘጠነኛ ሙት ዓመቱን በማሰብ የህይወት ታሪኩና ስራዎቹን የሚዳስስ የዶክመንተሪ ኦዲዮ ሲዲ መዘጋጀቱ ደበበን እንድናስታውስ ያደርገናል:: ይህንን የሚመለከት ዜናም በዚህ ዕትማችን አካተናል:: እንደተለመደው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳች በሌሎች ዓምደኞቻችን የተዘጋጁ ጽሑፎች ግብዣችን ነው:: መልካም ንባብ::

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top