ጣዕሞት

ስለ ደበበ ሰይፉ የተዘጋጀው ኦዲዮ ዶክመንተሪ ተመረቀ

መምህር፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ ገጣሚና ባለ ቅኔው ረዳት ፕሮፍሰር ደበበ ሰይፉ ካለፈ እነሆ 19 ዓመታት ተቆጠረ:: በእነዚህ ዓመታት አልፎ አልፎ በአንዳንድ ሚዲዎች ስለ ማንነቱና ስራዎቹ በጥቂቱ ከመነገሩ ባለፈ ማንነቱ ተተንተኖ የቀረበበት ሁንታ አልተስተዋለም::

ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለፈው ግንቦት 1/2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል በሚገኘ ተስፋዬ ገሠሠ አዳራሽ ስለ ደበበ የህይወት ታሪክና ስራዎቹ አዘጋጅቶ ያስመረቀው ኦዲዮ ሲዲ ግን ደበበ በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ማንነቱ እየታሰበ እንዲኖር የሚያስገድድ ነው ተብሏል::

80 ደቂቃ የሚፈጀው በዚህ ኦዲዮ ዶክመንተሪ ስለ ደበበ ማንነት ሚገልጹ 10 ሰዎችን ቃለ መጠይቅ ጨምሮ ደበበ በራሱ አንደበት ያነበባቸው ግጥሞች፣ የሂስ ንባቦቹና ልሎችም የድምጽ ግብአቶች ተካተውበታል::

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የደበበ ታናሽ ወንድም አቶ አበበ ባሰሙት ቃል፤ እስከዛሬ ስለ ደበበ ማንነትና ስራዎቹ ሲነገሩ የነበሩት እጅግ ጥቂቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የኦዲዮ ዶክመንተሪ ስራው ግን የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል:: ወደፊት የደበበን ሁለንተናዊ ማንነት ምገልጽ መጽሐፍ ታትሞ ለንባብ መብቃትን እንደሚመኙ የጠቆሙት አቶ አበበ፤ ለዚህም ስኬት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::

 የተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኤክስኩቲቭ ፕሮዲውሰር እዝራ እጅጉ እንደተናገረውም፤ ሲዲው በድርጅቱ ወጪ የታተመ ሲሆን፤ ወደፊትም ትውልዱን ለአገር በጎ ከሰሩ ሰዎች ጋር ይበልጥ ለማስተዋወቅ ተግቶ ይሰራል::

ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን ከዚህ ቀደም የ15 የሀገር ባለውለታዎችን ታሪክ በዲቪዲና በኦድዮ ሲዲ ያሳተመ ሲሆን፤ ታሪካቸው ከተሰራላቸው ባለውለታዎች መካከልም ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ፣ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን፣ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የሚጠቀሱ ናቸው::

ፍቃዱ ሃውልት ቆመለት

በኢትዮጵያ የመድረክ ቴአትር፣ በተከታታይ ቴሌቭዥ ድራማና ትረካ የትረካ ብቃቱ ሁሌም ስሙ ስነሳ የሚኖረው ፊቃዱ ተክለማሪያምን በህይወት ካጣነው እነሆ 10 ወራት ተቆጠረ:: ከሙያዊ ብቃቱ በዘለለ በሰብአዊ ድርጊቱ ብዙዎች ሚደንቁትና የሚያከብሩት ፍቃዱ፤ በኩላሊት ህመም ምክንት ህይወቱ እስካለፈበት ዕለት ድረስ ለሌሎች ተመሳሳ ችግር ውስጥ ላሉ ሲጨነቅ እንደነበር ተስተውሏል::

 አጼ ቴዎድሮስን ጨምሮ በተለያዩ ቴአትሮች ላይ እንደ ንጉስ ሆኖ ሲጫወት የሚዋጣለት ፍቃዱ፤ ህልፈቱ የአገራችን ቴአትር ጥበብ እድገትን እንደጎዳ ብዙዎች ይናገራሉ:: ከ40 ዓመታት በላይ በጥበቡ ዘርፍ ሲቆይ አያሌ ወጣት ተዋናዮችን እንዳፈራም ነው የሚነገርለት::

መልካም የሰራ ሁሉ ስሙ ከመቃብር በላይ እንደሚኖር ሁሉ፤ ፍቃዱም በስራው ስሙ ሁልም ሲነሳ ይኖራል:: ሰሞኑን አጽሙ ባረፈበት መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላስ ካትድራል የተሰራለትም የመታሰቢ ሃውልት ይህንኑ የሚመሰክር ነው::

 በርካታ አርትስቶች፣ አድናቂዎቹና አክባሪዎቹ በተገኙበት ለምረቃ የበቃው ሃዊልቱ እሱነቱን ስናስብ እንድንኖር ያስገድዳል::

የጋዜጠኞች ማህበር 50ኛ ዓመት ተከበረ

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞ ማህበር የተመሰረተበት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩ ቤልዩ በዓል ሰሞኑን በስካ ላይት ሆቴል በደማቅ ሁኔታ ሲከበር፤ ‹‹ ምን ሰራና ነው ደፍሮ የሚከብረው፤ የባከናቸውን ዓመታት በምን ሊወራርድ ነው?…›› የሚል ትችትና ወቀሳ በአንዳንድ ተሳታፊዎች ተሰንዝሮበታል:: ማህበሩ የሚጠበቅበትን ያህል እንዳልሰራና በዚህም መወቀሱ አግባብነት እንዳለው የጠቀሰው የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ መሰረት አታላይ በበኩሉ፤ ‹‹ተባብረን የማህበራችንን አላማ እናሳካ›› ሲል ጥሪ አቅርቧል:: በዚሁ መርሃግብር ላይ የተገኙት የማህበሩ መስራችና በተለያዩ ዘመናት ማህበሩን በሊቀመንበርነት የመሩት አንጋፋ ጋዜጠኞች አቶ ከበደ አኒሳ እና አቶ ማዕረጉ በዛብህ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማህበሩ ይዞት የተነሳው ዓላማ የጋዜጠኛውን መብትና ነጻነት ማስከበር ሲሆን፤ ከምስረታው ጀምሮ ባሳለፋቸው ዘመናት ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት መሰናክሎች እንደነበሩበት አውስተዋል:: ማህበሩ የዘመኑን አገራዊ ለውጥ ተጠቅሞ በአገሪቱ ዴሞክራሲና…..

‹‹የምድራችን ጀግና›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በብዝሃ ህይወትና አካባቢ ጥበቃ ረገድ ባከናወኗቸው ተግባራት ስማቸው ከአገር አልፎ ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቀው የዶክተር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር ህይወት ታሪክና ስራዎቻቸውን የሚገልጸው መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል::

በስድስት ክፍል ውስጥ ባሉ 28 ምዕራፎች ሁለንተናዊ ማንነታቸውን የዳሰሰው የመጽሐፉ አዘጋጅ ዘነበ ወላ፤ ርዕሱን ‹‹የዓለማችን ጀግና›› ብሎታል::

 ላለፉት 20 ዓመታት ስለ ዶክተር ተወልደብርሃን ህይወት ሲያጠና፣ ስራዎችቻቸውን ሲመረምር፣ ማህበራዊ መሰተጋብራቸውን ሲከታተል እንደነበረ ለዝግጅት ክፍላችን የገለጸው ዘነበ፤ ከብዙ ድካም በኃላ መጽሐፉ ለህትመት መብቃቱ እና ትውልዱ በልጥ እንድያውቃቸው ማድረጉ ደስታ እንደሚሰጠው ተናግሯል::

 የተወሰኑ ፎቶግራፎችና የሰነድ ማስራጃዎች ያሉት ይህ መጽሐፍ 520 ገጽ ያለው ሲሆን፤ በ200 ብር እየተሸጠ ይገኛል::

 ዘነበ ከአሁን ቀደም ለንባብ ካበቃቸው መጽሐፎች ውስጥ ‹‹ማስታወሻ›› የዶክተር ተወልደ ወንድም የስብሃት ገብረእግዚአብሔር ታሪክ ይገኝበታል::

ኤጀንሲው 75ኛ ዓመቱን አከበረ

ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕት ኤጀንሲ /ወመዘክር/ የተመሰረተበት 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩ ቤልዩ ክብረ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ የተከበረውም ካለፈው ሚያዚያ 23 እስከ 27/2011 ዓ.ም ነበር::

 በመጻሕፍት ዓወደ ርዕይ፣ በቅርስ ጉብኝት፣ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ደራሲያን ስራዎች የሂስ መድረክ ከህብረተሰቡ ጋር በዓሉን ያከበረው ኤጀንሲው፤ የዓመታት ጉዞው ንባብን በማበረታታት፣ ዕውቀትን በማስተላለፍና የነቃ ማህበረሰብን በመፍጠር ረገድ ኤጀንሲው አመርቂ ስራን ሰርቷል ተብሏል::

 ‹‹ከጠበቅነው በላይ በተሳካ ሁኔታ በዓላችንን አክብረናል›› ሲሉ በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹት በኤጀንሲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታዬ፤ ከኤጀንሲው የዕድሜ አቻ የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ጋር በትብብር ማክበሩ ከፍተኛ ድምቀት እንደሰጠው ተናግረዋል::

 ኤጀንሲው የንባብ ባህልን ለማሳደግ፣ አገራዊ የጽሑፍና የሰነድ ቅርሶችን ጠብቆና ተንከባክቦ ለተተኪው ትውልድ በአደራ ለማስተላለፍ የያዘውን ሰፊ ዕቅድ ለመተግበር በብርቱ እንደተነሳሳም ነው ገለጹት::

 ታህሳሥ 25/1936 ዓ.ም በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተመርቆ ለህዝብ አገልግሎት መሰጠት የጀመረው ወመዘክር፤ለበሪካታ ደራሲዎችና ጋዜጠኞች ባለ ውለታ እንደሆነ ይታወቃል::

ሃሳቢን በነጻነት መግለጽ መብት እንዲከበር በኩሉን ኃለፊነት እንድወጣ መክረዋል::

ከተለያዩ ሚዲዎች የተውጣጡ ጋዜጠኞችና ሀላፊዎች በተገኙበት በዚሁ መረሃግብር፤ ለመስራች ጋዜጠኞቹ ምስጋናና የእውቅና መታሰቢያ ተበርክቶላቸዋል::

 በዚሁ መድረክ የነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ያቀረበው የ ‹‹እንዋሃድ›› ጥያቄ በማህበሩ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን፤ አፈጻጸሙ ግን ጥናትና ተጨማሪ ምክክር እንደሚጠይቅ በመድረኩ ተገልጿል::

ራስ አበበ አረጋይ የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ለተደራሲያን ቀረበ

በጋዜጠኛና ደራሲ አጥናፍሰገድ ይልማ ተዘጋጅቶ ለህትመት የበቃው ይህ መጽሐፍ ‹‹የታሪክ ቅርስና ውርስ›› የሚል ርዕስን የያዘ ነው::

 በስድስት ክፍል ውስጥ ባሉ ሰላሳ ስምንት ምዕራፎችና በስራቸው ባሉ ሌሎች በርካታ ንዑስ ርዕሶች የጀግናው አርበገኛ ራስ አበበ የተጋድሎ ታሪክ፣ አገራዊ አስተዋጽኦ እና ግላዊ ባህሪያቸው ተተንትኖ ቀርቧል::

 ደራሲው ከአሁን ቀደም ለህትመት ካበቋቸው መጻሕፍት ውስጥ ‹‹የህይወቴ ሚስጥር›› የተሰኘ ግለ ታሪካቸውና ‹‹አብቶ እያሱ››የሚል ልጅ እያሱ ታሪክ ይገኝበታል::

ይህ ራስ አበበ ታሪክ መጽሐፍ 350 ገጽ ሲኖረው፤ በብር 250 በመሸጥ ላይ የገኛል::

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top