የታዛ ድምፆች

ከፌስ ቡክ የልብ አፍቃሪ

ሚስት ባልዋ ከስራ ወደ ቤት ሲመጣ ትንሽ ልታናድደው ታስብና እጥር ምጥን ያለች ደብዳቤ ጽፋለት አልጋ ላይ አስቀምጣለት አልጋው ስር ትደበቃለች። ባል በስራ የደከመ ሰውነቱን እየጎተተ ወደ ቤቱ ገብቶ ሚስቱን ሲጠራት አቤት የሚለው በማጣቱ ተኝታ ይሆናል ብሎ ወደ መኝታ ቤት ሲገባ ሚስቱ የጻፈችለትን ደብዳቤ ያገኛል። ደብዳቤው ‹‹ ሌላ ሰው ስለወደድኩ ካሁን በኃላ ካንተ ጋር መኖር ስለማልፈልግ ቤቱን ትቼልህ ሄጃለው›› ይላል ። በዚህ ጊዜ ባል ሆዬ ፈገግ ይልና ወዲያው ስልኩን አውጥቶ ደወለ።

‹‹ ሀይ የኔ ቆንጆ እንደነገርኩሽ ያቺ ጅል … ሚስቴ በራሷ ጊዜ ትታኝ ሄደች። ደስ አይልም? … መጣው ጠብቂኝ ›› ብሎ ስልኩን ዘግቶ ከቤት ይወጣል። ሚስት ብሽቅ ብላ ከአልጋ ስር ትወጣለች :: ከዚያም የተንጨረጨረች ምን ማድረግ እንዳለባት እያሰላሰለቸው አልጋው ላይ ስታማትር ሌላ ደብዳቤ ታገኛለች:: ፈጥና ስታነበው እንዲ ይላል ‹‹ የኔ ማር አልጋ ስር እንደተደበቅሽ አውቂያለው፤ አሁን ወይን ገዝቼ እስክመጣ ቆንጆ እራት ሰርተሽ ጠብቂኝ:: እወድሻለው የኔ ቆንጆ ››

 ኩሸት

አንደኛው ውሸታም “የዛሬ 10 ዓመት አባቴ በህንድ ውቅያኖስ ላይ በመርከብ ሲንሳፈፍ የእጅ ሰዓቱ ወድቆበት ከ10 ዓመት በኋላ ሲመለስ በዋና ውኃ ውስጥ ገብቶ ሲፈልግ ሰዓቱ ምንም ሳይሆን እየሰራ አገኘው” ይለዋል::

 ሁለተኛው ውሸታም ቀበል አድርጎ “ይገርምሃል የኔም አባት በዚሁ ውቅያኖስ ላይ ሲንሳፈፍ ወድቆ ከ10 ዓመት በኋላ ምንም ሳይሆን በሕይወቱ ዋኝቶ ወጣ” ይለዋል::

 በዚህ ጊዜ አንደኛው ውሸታም፤ “እንዴት ያንተ አባት ሳይሞቱ ውኃ ውስጥ ይህን ያህል ዘመን ሊኖሩ ቻሉ? ደግሞስ ምን እየሰሩ ቆዩ?” በማለት እየጬኸ ውሸታምነቱን አጋኖ ሲናገር፤ ሁለተኛው ውሸታም ተረጋግቶ “ውኃ ውስጥ እንኳን ሳይሆን አሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ነው የቆዬው፣ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ያንተን አባት ሰዓት እንዳይቆም እየወጣ ይሞላ ነበር›› ሲል መለሰለት::

አንደኛው ውሸታም ‹‹የኔ አባት በእርሻው ቦታ ላይ አውሮፕላን የሚያህል ጥቅል ጐመን አምርቶ አንደኛ ወጣ›› ይላል:: ሁለተኛው ውሸታም አተኩራራ ‹‹የኔም አባት እኮ በጋራዣችን ውስጥ ትልቅ አፍሪካን የሚያህል ብረት ድስት አምርቶ ተሸለመ›› ሲል ይመልሳል:: በዚህ ጊዜ አንደኛው ውሸታም “እንዴት! አፍሪካን የሚያህል ብረት ድስት ምን ያደርግላቸዋል?›› ብሎ ጠየቀው:: ሁለተኛው ውሸታም እንደተለመደው ቀብረር ብሎ “ታዲያ! ያንተ አባት ጥቅል ጐመን በምን ይቀቀላል?›› ሲል መለሰለት::

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top