የታዛ ድምፆች

ከፌስ ቡክ የጋሽ ስብሐት ጥፊ

ነብቸውን ይማረውና ጋሽ ስብሐት እንዲህ አደረጉ ይባላል::

አንድ ቀን ታክሲ ተሳፍረው ወደ ቤታቸው እየሄዱ ሳለ አጠገባቸው የተቀመጠው ሰው ለካስ ሌባ ኖሯል:: ታዲያ እጁን ወደ ጋሽ ስብሐት ኪስ ዘው ሲደርግ ጋሽ ስብሐት ይይዙታል:: ሌባው ደንግጦ “ ውይ! ይቅርታ የኔ ኪስ

መስሎኝ ነው” አለ::

ጋሽ ስብሐትም የገባቸው ነበሩና ሳያካብዱ ዝምብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ:: ትንሽ ከተጓዙ በኋላም ጋሽ ስብሐት መውረጂያቸው ሲደርሱ “ወራጅ አለ!” ብለው ሲወርዱ ታክሲው እንደቆመ አንድ ነገር ማለት ነበረባቸው:: እና ሌባውን ይዘው ሞቅ ባለ ጥፊ ያናጉታል::

ጯጯጯ!…

ሌባው በጥፊ የናረ ጉንጩን እያሻሸ… “እንዴ ምነው?” ሲላቸው፤

ጋሽ ስብሃትም “ውይ! ይቅርታ የኔ ፊት መስሎኝ እኮ ነው” አሉት የባላል::

ብድር በምድር

ዩኒቨርሲቲ ላይብሬሪ ነው አሉ፤ ልጁ ወደ ልጅቷ ጠጋ ይልና፤ “እሙ እዚህ ጋር ብቀመጥ ቅር ይልሻል?” ይላታል::

ልጅቷም ከመቀመጫዋ ብድግ በማለት ድምጿን ከፍ በማረግ “እኔ እንደማንም ተራ ሴት መሰልኩህ እንዴ አብረሽኝ እደሪ የምትለኝ?” ትልና ቁጭ ትላለች::

ይሄኔ ላይብሬሪ ውስጥ የነበሩት ተማሪዎች በግርምት ልጁ ላይ ያፈጡበታል:: ልጁም በህፍረትና በመሸማቀቅ ቀስ ብሎ ከአጠገቧ ይቀመጣል::

ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ልጅቷ ወደልጁ ጆሮ ጠጋ ብላ “አየህ የሥነ- ልቦና ተማሪ ስለሆንኩኝ ወንድ ልጅን ማሸማቀቅ እችልበታለሁ” ትለዋለች::

ልጁ ወዲያውኑ ከመቀመጫው ብድግ በማለት ጮክ ብሎ “ለአንድ አዳር አምስት ሺ ብር አልበዛም? ፌር አይደለም!” ይልና ቁጭ ይላል::

በዚህ ጊዜ ላይብሬሪ ውስጥየነበረው ተማሪ እሷ ላይ ያፈጣል:: ልጅቷም በህፍረት ኩም ብላ አንገቷን ታቀረቅራለች:: ይሄኔ ልጁ ወደ ጀሮዋ ጠጋ ይልና “አየሽ የህግ ተማሪ ስለሆንኩኝ ሴትን ልጅ ወንጀለኛ ማድረግ አውቅበታለሁ” ብሎ ውልቅ አለ አሉ::

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top