የታዛ ድምፆች

ከፌስ ቡክ

ትላንት ምሳ ሰዓት ላይ ነው፤ ሦስት ናቸው፤ ትልቅሮቶ ይዘዋል፤ ላዳ አስቆሙና ሮቶውን ጫኑ። ከዚያ ሩቅመንገድ ይዘውት ሄዱ። ብዙ ጉራንጉር አስገቡትና የሆነቤትጋ ሲደርሱ “ እዚህጋር ነን” ብለው አስቆሙት።

ባለ ታክሲው እቃቸውንም ተሸክሞ አወረደና፤ “ሂሳብ?” ሲል ጠየቀ።

“የለንም!” አሉት። ወርዶ ቢለምን ቢለምን “ዝምብለህ ንካው!” አሉት።

ጭራሽ “እንድንከፍልህ ከፈለክ ዝፈንልን” አሉት። “ዘፈን አልችልም” አለ።

“በቃ እሺ እልል በልና እንሰጥሃለን” አሉት።

“ሰርቼ እኮነው ለምን ታንገላቱኛላችሁ?” ሲል አማረረ። “አንሰማህም” አሉት።

“ጮክ ብለህ እልልል ካላልክ አንሰጥህም ”ሲሉም ይበልጥ አፌዙበት። ተናደደ።

“ተውት በቃ ከላይ አገኘዋለው” ብሎ እየተሳሳቁበት ሳይቀበላቸው ጥሏቸው ሄደ።

ትንሽ እንደ ሄደ ከኋላው ስልክ ጠራ። ዞር ሲል SumsungNot 8+ የተባለ ስልክ “አንሱኝ አንሱኝ… ”እያለእየጮኅ ነው።

ሾፌር መኪናውን ዳር አስያዘና ስልኩን አንስቶት “ሃሎ” አለ።

“ይቅርታ ወንድሜ አንተ ታክሲ ውስጥ ስልክ ጥለን ነበር”የሚል ድምፅ ተከተለ።

“ማን ልበል?” አለ።

“አሁን ያወረድከን…ሮቶውን የጫነው ልጆች ነን… እባክህን ስልክ ጥለን ነው…

”ይሄኔ ይህ የላዳ ሹፌር ምንቢል ጥሩ ነው? “አሁንነዋ እልልልልል ማለት! እልልልልልልልልልል,እልልልልልልል…!” ስልኩን ጆሯቸው ላይ ግጥም!


አንድ ጋዜጠኛ በፍንዳታ የምትባትተውን ይህቺ ሶሪያዊት ታዳጊ ሳቂ ባላት ጊዜ፤ ያሳየችው ገጽታ፤

ቆይ የአንዷን ኮረዳ ደረት….

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top