ጥበብ በታሪክ ገፅ

ፒያሳ የአዲስ አበባ ቅድመ ስልጣኔ አሻራ

ፒያሳ ለአሁኗ አዲስ አበባ መሰረት ናት ቢባል ስህተት የለውም:: ለአዲስ አበባ ሆነ ለኢትዮጵያ ዘመናዊነትን ያስተዋወቀች ወይም የመጀመሪያ የሚባሉ ተቋማት ያሏት አንዷ የከተማችን ክፍል ናት:: ስለዚህም እንደ ምስክርነት ሆነው የሚታዩ ብዙ አሻራዎች እናገኛለን:: ከእነሱም ጥቂቶቹን እንመልከት’

• በአዲስ አበባ እና በሀገራችን የመጀመሪያው የሆነ የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ነው:: የተመሰረተውም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1908 ዓ.ም ነው:: የሚገኘውም ፒያሳ ነው::

Taitu Hotel, Piazza, addis ababa ethiopia

 • የሀገራችን የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት ሌፔሮኬ ይባላል:: ወይም ደግሞ ሰይጣን ቤት በመባል ይታወቃል:: የሚገኘውም ፒያሳ ውስጥ ነው::

 • ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ኬክ የተሰራው ፒያሳ ሆኖ #ኤንሪኮ; ኬክ ቤት ነው::

• በአጼ ሚኒልክ ዘመነ-መንግሥት ጊዜ እንደ መገናኛ ኢንፎርሜሽን ሆኖ ያገለግል የነበረው ፖስታ ነበር:: አጼ ሚኒሊክ ከእንግሊዛዊትዋ ንግሥት ቪክቶሪያ መልዕክት ይለዋወጡበት የነበረው ሆኖ፤ የመጀመሪያው ፖስታ ቤትም ፒያሳ ውስጥ ይገኛል::

 • አዲስ አበባ ከተማ ከረጂም ጊዜ ጀምሮ የምትተዳደረው ፒያሳ ላይ በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት ነው::

 • የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዕጣ ሎተሪ ዋና መስራቤት የሚገኘው ፒያሳ ነው:: ስሙም ብሔራዊ ሎቶሪ ይባላል::

• ወደ ማንኛውም የሀገራችን ከተሞች ሆነ ወደ ተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ርቀት የሚለካው ከአዲስ አበባ ሆኖ ከፒያሳ ዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ ነው የሚለካው::

 • አዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መብራት መጠቀም ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዋናው መስራቤቱ ፒያሳ ውስጥ ነው::

• የሀገራችን የመጀመሪያው ባንክ “አቢሲኒያ ባንክ” ይሰኛል:: ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ የጀመረበትም በ1905 ዓ.ም ፒያሳ ውስጥ ነው::

• በሀገራችን ሆነ በአዲስ አበባ የመጀመሪያዎቹ ሙዚቃ ቤቶች ማህሙድ ሙዚቃ ቤትና አያሌው ሞዚቃ ቤት ናቸው:: መገኛቸውም ፒያሳ ውስጥ ነው::

• በአዲስ አበባ በጣት የሚቆጠሩ አውቶሞቢሎች በነበሩበት ዘመን፤ ፒያሳ ዘመናዊ የፓርኪንግ ሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን ነበራት:: አገልግሎት ባይሰጥም አሁንም ድረስ አርጅቶ ይገኛል:: በአሁን ዘመን ግን በሰለጠነው ዓለም ዘመን ሲዘምን ሰውን ማሽን ይተካዋል:: በእኛው አገር ግን ማሽንን ሰው ተክቶት ይገኛል::

ምንጭ- ፒያሳ መጽሐፍ (መሀመድ ሰልማን)

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top