ጥበብ በታሪክ ገፅ

ጥበብ በአምባገነኖች እጅ

ቺንሺ ያንግ የተባለ የቻይና መሪ ያለፈ ነገር እና ታሪክ ረብ የለሽ ነው ብሎ ያምን ነበር። ያለፈውን ታሪክ ከራሱ ዘመን ጋር እያነፃፀረ፤ የሚጽፉ እና የሚተቹ ምሁራንን በእጅጉ ይጠላል። የቆዩ መጻሕፍትን ሰብስቦ ያቃጠለው ይህ መሪ፤ አራት መቶ የሚደርሱ ምኹራንንም እንደ ዳመራ ሰብስቦ አቃጥሏቸዋል።

ከዚህ መሪ በኋላ ስሙ በክፋት ገዝፎ የተሰማው መሪ አዶልፍ ሂትለር ነው። ግንቦት 10 ቀን 1933 በናዚ ወጣቶች ቡድን አማካኝነት 25 ሺህ የሚደርሱ መጻሕፍት በርካቶች በተገኙበት፤ ያልተገኙት ደግሞ ሥነ-ስርዓቱን በቀጥታ የሬድዮ ሥርጭት እንዲከታተሉ አድርጎ ዳመራውን በርሊን ላይ ለኩሷል። ሂትለር የህን ያደረገው የአይሁድ ሥራዎች ለጀርመንም ሆነ ለአለም አይጠቅሙም ከሚል እኩይ ዕሳቤ ነው። እናም፤ የበርካታ ታዋቂ ደራሲዎች ሥራዎችም ተቃጠሉ። ከተቃጠሉት መጽሐፍት ውስጥ የአልበርት አነስታይን፣ የሄለር ከለር፣ የሲግመንድ ፍሩድ፣ የካርል ማርክስ እና የኧርነርስት ሄሚንግዌይ ይገኙበታል።

 አምባገነኖች እንዲህ እና ከዚህም በላይ የሚነገርባቸው ነውረኞች ናቸው። ይህ ማለት ግን ኪነት እና ከያኒያንን ስለሚፈሩ ብቻ ወይም ለጥበብ ባዳ ሆነው አይደለም። ለምሳሌ ያህል ሂትለር ሰዓሊ እንደሆነ ኮሌጅ እንዲገባ ቢፈቀድለት ኖሮ፤ የአለም ጦርነት ላይከሰት ይችል ነበር። ስፔይንን የመራው አምባገነን ጀነራል ፍራንሲስኮ ፍራንኮም ከሞተ በኋላ የሰራቸው ስዕሎች መገኘታቸው የልጅ ልጁ ባሳተመው መጽሐፍ ላይ ተጠቅሷል። ይህ ጀነራል በአንድ እጁ ግድያ በሌላው ውበት ነበር የሚያስተናግደው። በተለይ ጭንቀቱን ለመቀነስ ይጠቀም የነበረው ለረጅም ሰዓታት ክፍሉን ዘግቶ ብሩሽ በመያዝ ነበር።

 የእኔ ጀግና ናፖሊዮ ቦናፓርቲ ነው; የሚለው አምባገነን አውግስቶ ፒኖቼ ጥሩ አንባቢ ነው ብሎ ለመመስከር ቢከብድም፤ ቤተ-መጽሐፍቱ ውስጥ 50 ሺህ የሚደርሱ መጻሕፍትን ማሰባሰቡ በዋዛ የሚታይ አይደለም።

 አምባገነኖች ሁለት ሦስተኛ በሚሆነው የክፋት ውሃ የተቀመሙ ቢሆኑም፤ በጥቂት የሰውነት ክፍላቸው የማይታይ ደማዊ በጎነት ሊተነፍሡ ይችላል። የዛሬ ርዕሰ-ጉዳይም ይሄው ነው። የተወሰኑ አምባገነን መሪዎችን መርጦ ስለ ጥበብና ህይወታቸው ክፍል መመልከት።

 ሀ. ሁጎ ቻቬዝ

 የቬኒዙዌላው መሪ ሁጎ ቻቬዝ በደንብ የሚታወቀው ብዙ በማውራቱ ነው። ቤትም ሆነ በመንገድ ላይ ለረጅም ሰዓታት ሳይታክት ያወራል። በሳምንት በአማካኝ ለ40 ሰዓታት ህዝባዊ ንግግር ያደርጋል። ወጣ ባለው ንግግሩም ዓለም አሳምሮ ያውቀዋል። ከመሠለው ማንንም ከመዘርጠጥ ወደኋላ አይልም።

 ለምሳሌ ጆርጅ ቡሽ በተ.መ.ድ ንግግር ካደረገ በኋላ እሱም እንዲናገር ዕድል አግኝቶ ነበር። በዚህ ጊዜ ሠይጣኑ ትናት እዚህ መጥቶ ነበር፣ ልክ እዚህ ጋ፣ ለዚያም ነው ቦታው ድኝ ድኝ የሚሸተው; ብሎ ነበር። በ2006 ኢራንን ሲጎበኝ የሚከተለውን ተናገረ። “እስራኤሎች ሂትለርን አብዝተው ይተቻሉ፤ ነገር ግን ራሳቸው እየሠሩ የሚገኙት ከሂትለር ጋር ተመሳሳይ ነው። እንዲያውም ናዚ ከሠራው ይበልጣል” ይህ ንግግር ከፍተኛ ዓለም-አቀፍ አቧራ አስነስቶ ነበር። ቻፌዝ በራሡ ድክመት ላይም ሳይደብቅ ተናጋሪ ነው። በአንድ ወቅት “እኛ ከስብሰባ ወደ ስብሰባ እንዘላለን፤ ህዝባችን ግን ከገደል ወደ ገደል እየሄደ ነው” ብሎ ነበር። በሌላ ወቅትም “የፖለቲካ ድክመት እያሳየን ይመስለኛል፤ ልክ ነው የፖለቲካ ቪያግራ ያስፈልገናል” በሏል።

አለም በግልፅ ከሚያውቀው ማንነቱ ውጪ፤ የንባብ ተሰጥኦ አለው። “የንባብ ሱሰኛ ነኝ፤ ያለ ንባብ መኖር አልችልም፣ ልክ እንደ እጽ ሱሶኞች” የሚለው ቻፌዝ፤ ስላነበባቸው እና ተፅእኖ ስለፈጠሩበት ደራሲያንም በእጅጉ ነው የሚያወራው። በነገራችን ላይ ደጋግሞ ያነበባቸውና ሌሎችም እንዲጋሯቸው ሃሳብ የሚሰጥባቸው ሠባት መጻሕፍት አሉ።

. የቪክቶር ሁጎ – ሊስሚሰራብል . የሳርቫንቴስ – ዶን ኪሆቴ . የሚካኤል ሙር – ዱድ፣ ዌር ኢዝ ማይ ካንትሪ?

 . የፍሪቲ ኦፍ ካፕራ – ዘር ተርኒንግ ፓይንት

 . የጋልብሬዝ – ዘ ኢኮኖሚክስ ኦፍ ኢኖሠንት ፍራውድ

 . የጀርሚረፊን – ዘ ሃይድሮጅን ኢኮኖሚ

 . የሙአመር ጋዳፊ – ዘ ግሪን ቡክ ናቸው። ቻቬዝ በሀገሪቱ በሚደረጉ የድህነት ስብሰባዎች ላይ ከሁጎ ምንዱባን መጽሐፍ ላይ እየጠቀሰ በመግቢያነት የሚገልፀው በደስታ ነው። የሰርቫንቴስ ዶን ኪ ሆቴም ሌላው የንግግር ማዳመቂያው ነው። ሰዎች ኢ-ፍትሃዊ አሠራሮችንና ጉዳዮችን አጥብቀው እንዲዋጉ የኪሆቴን ተግባራት ይጠቃቅሳል። የጆን ኬኔዝ ጋልብሪዝን “ኢኮኖሚ ኦፍ ኢኖሠንት ፍራውድ” ትምህርት ቤት እንዳነበበው ይናገራል። ደራሲው ሶሻሊስት ባይሆንም የካፒታሊዝንም ኢኮኖሚ የሚተች ነው። ቻፌዝ አሜሪካንን ለሚተቸው መጽሐፍ ልዩ ፍቅር አሳድሯል። ለዚህም ይመስላል በየሳምንቱ እሁድ በሚቀርበው “ሄሎ ፕሬዝዳንት” በተባለው ፕሮግራሙ “እኔም ጋልብሬዝ ነኝ” በማለት አስተያየት የሚሰጠው። ቻፌዝ የጋዳፊን መጽሐፍ ብርቱ አድናቆት እንዳነበበው የመሰከርችው ባለቤቱ ናት። ከ1984 እስከ 1993 ውሽማው የነበረችው የታሪክ ፕሮፌሰር ሚስ ማርክስ ማን፤ “መኪና ሲያሽከረክር እንኳ ድምፄን ከፍ አድርጌ መጽሐፍ እንዳነብለት ያደርግ ነበር” ብላለች።

 ቻፌዝ የንባብ ባህል በሀገሪቱ እንዲስፋፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይህን ልምድ እሱ እንደሚጠራው አብዮታዊ የንባብ ዕቅድ ለማስፋፋት የተጠቀመበት ሥልት አራት የቀለም ኮዶች ናቸው። ግቡም በመሠረታዊ የሶሻሊዝም እሴቶች ላይ የጋራ ድርጊቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ ነው።

 በዚሁ መሠረት የመጀመሪያው የንባብ ደረጃ “ቀዶ ቡድን” የሚባል ሲሆን፤ አንባቢዎች አብዮታዊ መሪዎች ሲፃፃፉ የነበሯቸውን ደብዳቤዎች እንዲተዋወቁ እና እንዲረዷቸው ይደረጋል። በዚህ ደረጃ የሚመረጡ የንባብ መሪዎች አንባቢዎቹ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲያነቡ ማበረታት ይጠበቅባቸዋል።

አንባቢዎች ከፍ ሲሉ ወደ ሁለተኛው ደረጃ ማለትም ወደ አረንጓዴው ቡድን; ይቀላቀላሉ። በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ አንባቢ የካፒታሊስትን ምንነት በመረዳት እና በመተንተን ዙሪያ ያጠነጥናል።

 ሦስተኛው ደረጃ “ቡርቱካናማ ቡድን” ነው። ይህ ቡድን በተናጠልም ሆነ በቡድን የሶሻሊስትን አብዮትንና የአብዮትን ፕሮጀክት በማጠናከር ዙሪያ አስተዋጽኦውን ያበረክታል። አራተኛው ደረጃ “ጥቁር ቡድን” ነው። ይህ ቡድን ኢምፔሪያሊስቶች በርዕዮተ-ዓለምም ሆነ በባህል ላይ ሊያደርጉ የሚሞክሩትን ወረራም ሆነ ጥቃት የመከላከል እና ሀሳቡን ለሌሎች የማጋራት ኃላፊነት ይጠበቅበታል።

 አንድ መቶ የተመረጡ መጻሕፍት ለንባቡ ባህል የመጠቀሙን ተግባር እውን በማድረግ ረገድ በመንግሥት የሚደገፉ አሳታሚ ድርጅቶችም ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። ከሚታተሙ መጻሕፍት ውስጥ 25 ሺህ ኮፒ ያህሉን ለመላው ቬኒዚዌላ ያሰራጫሉ።

 ለ. ሳዳም ሁሴን

 በጣም ያነባል። ከፊዚክስ እስከ ፍቅር ተኮር ሥራዎች ድረስ ፍላጎቱ ናቸው። የጡት አባት፣ ሽማግሌው እና ባህሩ የተሰኙት ሥራዎችን ደጋግሞ አንብቧቸዋል። በፖለቲካዊ ብቃቱ በእጅጉ የሚያደንቀው ዊኒስተን ቸርችልን ነው።

ሳዳም ከአንባቢነቱ በተጨማሪም የራሱን ልቦለዶች እና ሌሎች ሥራዎች ለንባብ ማብቃቱ ልዩ ያደርገዋል። Zabibah and the king, The Fortified castle, begone Demons እና Men and the city ዋነኛዎቹ ሥራዎቹ ናቸው።

 ሳዳም ዘቢባ እና ንጉሡን ከማሳተሙ በፊት በሀገሪቱ ለሚገኙ ፕሮፌሽናል ጽሑፎች ረቂቁን በትኖ ነበር። ይህም በአንድ በኩል ሥነ-ጽሑፋዊ ትህትናውን፤ በሌላ በኩል ለመማር ዝግጁ ነኝ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተጠቅሞበታል። ይሁን እንጂ አንድም ሠው ደፍሮ እውነተኛ አስተያየት አልሠጠውም። ጽሑፉ አማተርሽ ቢሆንም ገምጋሚዎቹ ጨዋ አስተያየት ከጥቂት ማሻሻያ ሀሳብ ጋር መወርወርን ነው የመረጡት።

 ሳዳም በፊልሞችም ይዝናናል። በተለይ ሚስጥራዊ ግድያ እና ሴራ አዘል ለሆኑ ስራዎች ላይ ልዩ ፍቅር አለው። The day of the jakal, Enemy of state እና The conversation ተጠቃሾች ናቸው። ወደ ሌሎች ሀገሮች ብዙ የሚሄድ ባለመሆኑ ይህን መሠል ፊልሞች ማየቱ ስለ ዓለም ያለውን አስተሳሰብን ይገመግምበታል ይሉታል።

 ሲኤን ኤን፣ ስካይ፣ አልጄዚራና ቢቢሲ የውጪ ቴሌቪዥን ምርጫዎቹ ናቸው። የሀገሩን ጣቢያ ይበልጥ በመከታተል ወይም በመገምገም ደግሞ የመጀመሪያው መሪ ሳያደርገው አይቀርም። ሁለት ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ፖለቲካዊ እና የመንግሥት ተግባራት እንዴት ሳይጋጩ እንደሚሄዱ ለመገምገም ሲሆን፤ ሁለተኛው ከግሉ የስብዕና ግንባታ ጋር ይያያዛል። ሚዲያው ፖለቲከኛውንና ደራሲውን ሳዳም በምን መልኩ እየገነባ መሆኑን መገንዘብ ይፈልጋል። እንሆ አንዲት ምሳሌ፡-

 የሳዳምሁሴን ፀሐፊ አልባዛዝ ቢሮ ትደውልና ፕሬዝዳንቱ ለሆነ ጉዳይ ሊያነጋግሩህ ይፈልጋሉ; ትልና ስልኩን ትዘጋለች። የሚዲያ ኃላፊ፣ ኤዲተር እና ደራሲው አልባዛዝ ሀሳብ ውስጥ ወደቀ። አልባዛዝ የ25 ዓመት ወጣት እያለ ነበር የመጀመሪያውን የአጫጭር ልቦለዶች ስብስቦች ያሳተመው። ጋዜጣ ላይ በሚጽፋቸው ተነባቢ መጣጥፎቹም ይታወቃል።

አልባዛዝ ወደ ኋላ ተጉዞ ማሰብ ጀመረ። አዎ! ሳዳም ሁሴን ም/ሊ/መንበር የነበሩ ጊዜ በጠሩት ስብሰባ ላይ ተያይተው ነበር። በወቅቱ የሰጡት ያልተጠበቀ አስተያየት በደስታ አስፈንጥዞት ነበር። “ጋዜጣ ላይ ከምትጽፋቸው መጣጥፎች የተወሰኑትን አንብቤያለሁ፣ መጽሐፍህንም አውቀዋለሁ፣ ጥሩ ናቸው” ወጣቱ ጸሐፊ ጆሮውን ማመን አቅቶት ነበር። ሳዳም ቀጠሉ “እስር ቤት እያለሁ የኧርነስት ሄሚንግዌይንን ሁሉም ልቦለዶች አንብቤያቸዋለሁ፣ በተለይ የምወደው ሽማግሌውና ባህሩን ነው” አልባዛዝ ሲቃ እንደተናነቀው ያስታውሳል። ይህ ለኢራቅ አዲስ እና ታላቅ ዜና እንደሆነ ገመተ። ሥነ- ጽሑፍን የሚያነብ እና የሚረዳ ፖለቲከኛ በመገኘቱ ተአምር ሆኖ ተሰማው።

 ይህን እያንሰላሰለ ለግማሽ ሰዓት ፀሐፊዋ ቢሮ ተጎልቶ ቆየ። የባለ ሥልጣናቱ መግባትና መውጣት ጋብ ሲል ወደ ውስጥ እንዲዘልቅ ተነገረው። በወታደራዊ ልብስ የገዘፉት ሳዳም እጃቸውን እንኳ ለሠላምታ እንዳልዘረጉለት ሲገነዘብ አመጣጡ ጥያቄ እንዳለበት አሠበ።

“እንደምን ሠንብተሃል?”

“ደህና ነኝ” አልባዛዝ በትህትና መለሰ።

“ይኸው የርስዎን ትዕዛዝ ለማዳመጥ ተገኝቻለሁ” ሳዳም በአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ እየተላለፈ ስለሚገኝ የግብፅ ኮሜዲ ፊልም አቤቱታ ማቅረብ ጀመሩ።

“የማይረባ ሥራ ነው። ይህን ለህዝባችን ማሳየት የለብንም!” አልባዛዝ ማስታወሻ ያዘ።

“የእኔን ስም የሚያወድሱ አንዳንድ ዘፈኖች በቲቪ ለማስተላለፍ አንተ ፈቃጅ እንዳልሆንክም እረዳለሁ” አልባዛዝ በፍርሀት እና ድንጋጤ ክው አለ። በተሻሻለው የአሠራር ፖሊሲው መሠረት ከደረጃ የወረዱ ግጥሞችንና ዘፈኖችን የቅርጫት ራት ማድረግ  ጀምሮ ነበር።

“የተከበሩ ፕሬዝዳንት እስካሁን ግጥሞችንና ዘፈኖችን እያስተላለፍን ነው፤ ነገር ግን አንዳንዶች ሚዛን የማይደፉ ባለመሆናቸው እንዳይተላለፉ ተደርገዋል።”

“ ተመልከት!” አሉ ሳዳም እያቋረጡት።

 “አንተ ዳኛ አይደለህም!”

“ አዎ ዳኛ አይደለሁም”

“ሲኤን ኤን፣ ስካይ፣ አልጄዚራና ቢቢሲ የውጪ ቴሌቪዥን ምርጫዎቹ ናቸው። የሀገሩን ጣቢያ ይበልጥ በመከታተል ወይም በመገምገም ደግሞ የመጀመሪያው መሪ ሳያደርገው አይቀርም። ሁለት ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ፖለቲካዊ እና የመንግሥት ተግባራት እንዴት ሳይጋጩ እንደሚሄዱ ለመገምገም ሲሆን፤ ሁለተኛው ከግሉ የስብዕና ግንባታ ጋር ይያያዛል”

እና ህዝቡ ለእኔ ያለውን ፍቅር እና ስሜት እንዴት ነው እንዳይሰማለት የምታደርገው?!”

 የአልባዛዝ የልብ ዱለቃው ከሩቅ ይሰማ ነበር። በፊቱ ላይ ደም የሚጎርፍ፣ በወታደሮች ተጎትቶ ተወስዶ የሚረሸን መሠለው። ብዕር የጨበጠው እጁ ሳይታወቅ መንቀጥቀጥ ጀምሯል።

“በፍፁም! አንተ የዚህ ነገር ዳኛ አይደለህም”

“እሺ ጌታዬ!”

 ደራሲው እና አዘጋጁ በፍርሀት ማስታወሻ መያዙን ቀጠለ።

“ ለመገናኛ ብዙኃንና ለኪነ-ጥበብ ሰፊ ነፃነት መስጠት ያስፈልጋል፤ ቁጥጥሩ የሚጠብቅበት ሁኔታ ሊኖር አይገባም።”

“እሺ ጌታዬ!”

“ጥሩ አሁን ሁሉ ነገር ግልፅ ሆኖልሃል?”

“አዎ ጌታዬ”

አልባዛዝ በድንጋጤ እንደወጣ ወደ ቢሮው አምርቶ ግጥምንና ዘፈኖችን የተመለከተውን ፖሊሲ ሰረዘ። በዚያው ምሽት ለሳዳም ሁሴን መታሰቢያ የተዘጋጁ ግጥሞች

“ሲኤን ኤን፣ ስካይ፣ አልጄዚራና ቢቢሲ የውጪ ቴሌቪዥን ምርጫዎቹ ናቸው። የሀገሩን ጣቢያ ይበልጥ በመከታተል ወይም በመገምገም ደግሞ የመጀመሪያው መሪ ሳያደርገው አይቀርም። ሁለት ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ፖለቲካዊ እና የመንግሥት ተግባራት እንዴት ሳይጋጩ እንደሚሄዱ ለመገምገም ሲሆን፤ ሁለተኛው ከግሉ የስብዕና ግንባታ ጋር ይያያዛል”

እና ዘፈኖች በሙሉ የቲቪ ፕሮግራም መቅረብ ጀመሩ።

 ሐ. ስታሊን

 ልክ እንደ ብዙዎቹ የጆርጂያ ህፃናት ሎሴብ ጃረሊሽፈሊ ያደገው ብሔራዊ ግጥሞችን በማዳመጥ ነው። በ1894 በኦርቶዶክስ ሰሚናር ውስጥ ከተመዘገበ በኋላ የጎቴ እና ሼክስፒር ትርጉም ሥራዎችን ለታዳሚዎች አንብቧል፡፡

 በ1895 ዕድሜው 17 ሲሞላ የፍቅር ግጥሞችን መጻፍ ጀመረ። በሥራዎቹ የተገረመው ገጣሚው አሊያ ሻፍሻፍዛ አምስት  የሚደርሱ ግጥሞቹን በሚያሳትመው መጽሔት ላይ ሶስሎ በሚል ብዕር ስም አሳትሟል።

 ስታሊን ግጥሞቹን ወጥሮ በሚሠራበት ዘመን ስታሊን ኢፕግራም; የተባሉ ምፆታዊ ግጥሞችን በስፋት ይጽፍ ነበር። አንዳንዶች ይህን ክሪምሊን ሃይላንደር በማለት ይጠሯቸዋል። ምስጢር ላይ የተመረኮዙ በመሆኑ ብዙዎች እንደበፊተኞቹ የስታሊን ሥራዎች ፍቅርና የላቀ መረዳት አልነበራቸውም። ጥቂቶቹን ለግንዛቤ ያህል፤

 .Our lives no longer feel ground under them At ten paces you can’t hear our words.

 The ten thick warms his fingers. His words like measures of weight.

ስታሊን ከንባብ አንፃር የግራ ክንፍ ዘመም ሥራዎች ላይ ቢያተኩርም የቆዩ የሩሲያና የምዕራብ ዓለም ሥራዎችን አጣጥሟል። በ1920ዎቹ በፖለቲካ ተቀናቃኝ የነበሩት ሌኒን፣ ትሮትስኪ እና ዚኖቪቭ ሥራዎች ላይ ግዜ ይወስድ ነበር። በ1930ዎቹ ግን ትኩረቱን በሶቪየት ሥነ-ጽሑፍ ላይ በማድረግ እነ ማክሲም ጎርኪን፣ አሌክሳንደር ፋዴቭ፣ ቶልሰተይ፣ ሚካኤል ሽኮሎቭ እና የመሳሰሉትን ማጥናት መርጧል። ከአብዮት ሰራሽና ልቦለዶች በተጨማሪም በታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ኢኮኖሚክስ እንዲያውም ወታደራዊ ነክ ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ነበረው። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላም በኢኮኖሚ፣ ወታደራዊ እና ሥነ-ልሳን ዙርያ በተደረጉ ውይይትና ክርክሮች ላይ በሠፊው ይሳተፍ ነበር።

 ስታሊን ፀሐፊዎችን በሁለት መልኩ ነበር የሚገነዘባቸው። የሚወደዱ እና የሚፈሩ በሚል ስሜት። ስታሊን በአንድ ወቅት “ደራሲዎች የሰው ነፍስ መሃንዲሶች ናቸው” ሲል መስክሯል። “የነፍስ ምርት ከታንክ ምርት የበለጠ አስፈላጊ ነው” ማለቱም ተመዝግቧል።

 በሌላ በኩል ግን የእሱ ፓርቲ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ሥጋት ስለሚያድርበት በማሰር እንዲወገዱ ይፈልግ ነበር። ለአብነት ያህል ገጣሚው ኦሲፕ ማንደልስታም፣ የሙዚቃ አቀናባሪው ዲሜትሪ ሾስታኮቪች፣ ደራሲ እና ጸሐፊ ተውኔት ሚካኤል ቡልጋኮፍ እንዲሁም የፊልም ዳይሬክተሩ ሳርጌ አይዘንስታይን ተለይተው የታሰሩ እና ከፍተኛ ውሳኔ የሚጠብቁ ባለሙያዎች ነበሩ። ሆኖም ስታሊን እስረኞቹን አልፎ አልፎ ስልክ እየደወለ ያፅናናቸው ሲሆን፤ ሳይጎዱ እንዲያዙም ያስጠነቅቅ ነበር። በግጥሞቹ ተሳልቆ የታሰረው ማንደልስታም እንደዚያም ሆኖ በስታሊን ዘወትር ይደነቅ ነበር። የሞት ፍርድ ባያገኘውም ጉላግን ወኽኒ ቤት ልኮ ነበር። ነገር ግን የቀን ሥራ መስራት ከባድ መሆኑን የተገነዘበው ስታሊን በነፃ፤ እንዲለቀቅ

“ከአብዮት ሰራሽና ልቦለዶች በተጨማሪም በታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ኢኮኖሚክስ እንዲያውም ወታደራዊ ነክ ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ነበረው። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላም በኢኮኖሚ፣ ወታደራዊ እና ሥነ-ልሳን ዙርያ በተደረጉ ውይይትና ክርክሮች ላይ በሠፊው ይሳተፍ ነበር”

እስከ ማድረግ ደርሷል።

ስታሊን እዚህ እና እዚያ በሚረግጠው ህይወቱ ምክንያት እስከ ሩስያ አብዮት ድረስ የግሉን ቤተ- መጻሕፍት ማደራጀት የቻለ አልነበረም። በኋላ ላይ ግን ረዳቱንና ጸሐፊውን እንዲያስተባብሩ በማድረግ ክሪሚሊን ጽ/ቤቱን ጨምሮ ለሁለት መዝናኛ ቦታዎቹ የሚፈልጋቸው መጻሕፍት እንዲሰበሰቡ አድርጓል። መጻሕፍቱ ስታሊን የሚል ጽሑፍ እና ቁጥር እንዲይዙ ተደርጓል። ስታሊን በ1953 ከሞተ በኋላ በቤተ-መጻሕፍቱ በተቆጠረ መረጃ መሠረት 19,500 መጻሕፍት ተገኝተው ወደ ተለያዩ ቦታዎች እንዲበተኑ ተደርጓል።

በነገራችን ላይ ጃጊሊሽፊሊ ወደ ፖለቲካው አለም ከገባና መጠሪያውን ስታሊን ካስባለ በኋላ ግጥም መፃፍ አቁሞ ነበር። የሰጠው ምክንያት ደግሞ መሰላቸትን ነው። ግጥም የበዛ አትኩሮት እና ትዕግስት ይፈልጋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top