ከቀንዱም ከሸሆናውም

የሚዛን ድንጋይ የለኝም

አንድ ዳቦ ጋጋሪ ከአንድ ገበሬ ሁልጊዜ አንድ ኪሎ ቅቤ ይገዛ ነበር::

 አንድ ቀን ዳቦ ጋጋሪው ገበሬው የሚሸጥለት አንድ ኪሎ ቅቤ በትክክል አንድ ኪሎ መሆኑን ለማረጋገጥ ቅቤውን ሊመዝን ይወስንና ቅቤው አንድ ኪሎ አለመሆኑን ይደርስበታል::

ዳቦ ጋጋሪው በሁኔታው በጣም ስለተበሳጨ ገበሬውን ፍርድ ቤት ያቆመዋል!

ዳኛው ገበሬውን የሚሸጠውን ቅቤ እንዴት እንደሚመዝን ጠየቀው::

 ‹‹የተከበሩ ዳኛ፣ እኔ ኋላቀር ገጠሬ ነኝ:: ቤቴ ውስጥ ሚዛን እንጂ የሚዛን ድንጋይ የለኝም›› በማለት መለሰ::

‹‹ታዲያ ቅቤውን እንዴት ነው የምትመዝነው?›› በማለት ዳኛው ጠየቁት::

 ‹‹የተከበሩ ዳኛ፣ ዳቦ ጋጋሪው ከኔ ቅቤ ከመግዛቱ በፊት እኔ ከሱ አንድ ኪሎ ዱቄት እገዛዋለሁ:: ሁልጊዜ ቂቤውን ሊወስድ ሲመጣ ከሱ የገዛሁትን አንድ ኪሎ ዱቄት ሚዛን ላይ በማስቀመጥ እኩል ክብደት ያለው ቅቤ መዝኜ እሸጥለታለሁ:: ጌታዬ – ለዚህ ችግር ተጠያቂ እኔ ሳልሆን ዳቦ ጋጋሪው ነው›› በማለት መለሰ::

የታሪኩ ፈትል – በህይወት ውስጥ የምናገኘው ለሌሎች የሰጠነውን ያክል ነው! ‹‹በሰፈሩት ቁና ተመልሰው ይሰፈራሉ›› እንዲል ያገሬ ሰው! (ይህ መሳሊያዊ ምክር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሰምና ወርቅ ኪነ ፕበብ ምሽት አንደኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከተናገረው የተቀነጨበ ሲሆን፤ ምንጭ ያደረግነውም የጌጡ ተመስገንን ፌስ ቡክ ገጽ ነው)የውበት ሳሎኔ

ከኛ ወዲያ ፍቅር…..
>
ደሞ ለመፃፍ!

ሰልፊ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top