የታዛ ድምፆች

ከፌስ ቡክ

በቀልደኝነታቸው የሚታወቁት አለቃ ገብረሐና በጣም አጭር ናቸው ይባላል። ሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያሽ ደግሞ ሲበዛ 1ሜትር ከ80 ናቸው። መንገድ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ ወይዘሮ ማዘንጊያሽ ሠማዩን አይተው አለቃ ዝናብ ሊዘንብ ነው መሰለኝ ይሏቸዋል። ከዚያ አለቃ ከኋላቸው ኩስ ኩስ እያሉ ሲመልሱላቸው! «እኔ ምን አውቃለሁ ለሰማዩ ቅርቡ አንቺ ነሽ» አሏቸው ይባላል።

አንድ ቀን አንድ ባለፀጋ አባት ድሆች እንዴት እንደሚኖሩ ለማሳየት ልጁን ከከተማ ይዞት ይወጣል። እጅግ ዝቅተኛ በሚባለው የድሆች ስፍራም ላይ ሁለት ቀንና ሁለት ለሊቶችን አሳለፉ። ከጉዞው በተመለሱ ጊዜ አባት ልጁን ጠየቀ።

 “ ጉዞው እንዴት ነበር?”

 “ግሩም ነበር“ ልጁ መለሰ።

 “ድሆች እንዴት እንደሚኖሩ ተመለከትክ?”

 “አዎን “ ልጅ ይመልሳል።

 “ እስቲ ከጉዞው ምን እንደተማርክ ንገረኝ!

  ልጁም እንዲህ መለሰ። “እኛ አንድ ውሻ ሲኖረን እነሱ አራት ውሾች አሏቸው። እኛ የአትክልቱን ስፍራ ግማሽ የሚሆን መዋኛ ገንዳ ሲኖረን እነሱ መጨረሻ የሌለው ጅረት አላቸው። እኛ ፋኖሶችን ወደ አትክልት ስፍራ ማምጣት ሲኖርብን እነሱ ለምሽት ክዋክብት አሉላቸው። የኛ መናፈሻ እስከ ደጃፉ የሚደርስ ሲሆን እነሱ ሙሉ አድማስ አላቸው። የምንኖረው ጥቂት በሆነ ስፍራ ሲሆን እነሱ ግን ከእይታችን በላይ የሆነ ወሰን አላቸው። እኛ ምግባችንን እንገዛለን እነሱ ግን ያመርታሉ። እኛ በግንብ ተከልለለን ንብረታችንን ስንጠብቅ እነሱ የሚጠብቃቸው ጓደኛ አላቸው።”

አባትዬው ምንም ቃል መናገር አልቻለም። ልጁ ግን ቀጠለ።

 “አመሰግናለሁ አባዬ ፤ ምን ያህል ደሃ መሆናችንን አሳይተኸኛል። “

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top