ጣዕሞት

ኢትዮጵያዊት ሞዴል ፋና ዘርፉ በአለም አቀፍ ውድድር ተቀላቀለች

ኗሪነቷን በእንግሊዝ አገር ያደረገችው የማስታወቂያ ሞዴሊንግ ባለሙያ ደሊና ገዙ በአለም ቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆኑት እንደ ADIDAS, LOREAL UK, BBC, T-MOBILE, VODA Phone, BOOBI BROWN, BLACKBERRY ካሉ አምራቾች ጋር እንዲሁም እንደ Cosmopolitan magazine, Glamore magazine, Channel4, Novotel ባሉ የፋሽን መፅሄቶች ላይ ሽፋን አግኝታለች። ‘ADIDAS IS ALL IN’ በተባለው ማስታወቂያ ላይም ደሊና ገዙ እውቅ ከሆኑት ከተዋናይት ኬቲ ፔሪ እና ከኮከብ ኳስ ተጫዋቹ ዴቪድ ቤካም ጋር በጥምረት ሰርታለች። ኢንተርናሽናል ሞዴል ደሊና ገዙ የተሰማራችበትን የፋሽን እና ሞዴሊንግ ኢንዱስትሪ በመጠቀም በአገራችን ውስጥ

ሂድን ቢውቲ ኦፍ ኢትዮጲያ የሞዴሊንግ ውድድር ለአሸናፊዋ ዓለም አቀፍ የሞዴሊንግ ስራ ስምምነት በሽልማት መልኩ እንደሚሰጥ ቃል በገባው መሰረት አሸናፊዋ ሞዴል ሊንድነ ሰቱበ ከተሰኘ አለማቀፍ የሞዴሊንግ ኤጀንሲ ጋር ስምምነት በመፈጸም ለስራ እንግዚዝ አገር መከተም ችላለች

ያሉ ወጣት ሴቶችን ችሎታና ብቃት በማገዝ ህልማቸውን ለማሳካት አልማ ተነስታለች። በዚህም መሠረት፤ በመጀመሪያው ዙር የሂድን ቢውቲ ኦፍ ኢትዮጵያ ውድድር ሞዴል ፋና ዘርፉ ዳዴ የተባለች ጠንካራ ወጣት ኢትዮጵያዊትን ወደአለም አቀፉ የሞዴሊንግ ኢንዱስትሪ ለማቀላቀል ችላለች። ሂድን ቢውቲ ኦፍ ኢትዮጵያ የሞዴሊንግ ውድድር ለአሸናፊዋ ዓለም አቀፍ የሞዴሊንግ ስራ ስምምነት በሽልማት መልኩ እንደሚሰጥ ቃል በገባው መሰረት አሸናፊዋ ሞዴል ሊንደን ስታብ ከተሰኘ አለማቀፍ የሞዴሊንግ ኤጀንሲ ጋር ስምምነት በመፈጸም ለስራ እንግሊዝ አገር ለመክተም ችላለች። በዚህ ውድድር 2000 የሚደርሱ ወጣት ኢትዮጵያውያት የተካፈሉ ሲሆን፤ እጅግ ፈታኝ ዙሮች ከተከናወኑ በኋላ በድምር ውጤት የዚህ ውድድር የመጀመሪያ ምእራፍ አሸናፊ ሞዴል ፋና ዘርፉ ዳዲ ልትሆን ችላለች። ሞዴል ፋና ያላት ማራኪ ውበት፣ እጅግ መልካም ሰብእና እንዲሁም ከፍ ያለ በራስ መተማመን እና በየዙሮቹ የነበሩትን ፈተናዎች በብቃት መወጣቷ የአሸናፊነቷ ዋና ምክንያት ሆኗል። ስለአገሯ ታሪክ እና ባህል ያላት ጥልቅ እውቀት እና ፍቅርም ለአሸናፊነቷ ሌላኛው ግብአት ነበር።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top