ጥበብ በታሪክ ገፅ

ኢትዮጵያ በጥንታውያን ጸሐፊዎች በጥቂቱ

ከድተው በኢትዮጵያ መሀል እንደሰፈሩ ይተርካል። ካምቤዝ ዳግማዊ የተሰኘ ንጉስ ሰላዮችን ኢትዮጵያን እንዲሰልሉ ልኳቸዋል። ሰላዮቹም ብርቱና ጤናማ ህዝቦችን አይተው እንደተመለሱ በመናገራቸው በመረጃው ተመስርቶ ካምቤዝ ወደ ኢትዮጵያ ወራሪ ጦር ያዘመተ ሲሆን ወታደሮቹ ሳይቀናቸው ተመልሰዋል። የወታደሮቹን ሽንፈት ደፍሮ ማጋለጥ የተሳነው ሄሮዱተስ የካምቤዝ ወታደሮች የተሸነፉት በቂ ዝግጅት ባለማድረጋቸው ነው የሚል ማስተባበያ አስቀምጧል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የወርቅ ክምችት እንዳለ፣ ትልልቅ ዝሆኖች እንደሚገኙ፣ ልዩ ልዩ የዱር ዛፎችም እንዳሏት መስክሯል። ሰዎቻቸው ረጃጅም ያማሩና በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኙ ህዝቦች የበለጠ ረጅም እድሜ እንደሚኖሩ ገልጿል።

 ምንም እንኳ እንደ ሄሮዱተስ ዝርዝር መረጃዎችን ያቀፈ ባይሆንም ስለኢትዮጵያ የፃፈው ማንቶ ነው። ይህ ግብጻዊ ካህን ግብጽን የመራውን ሀያ አምስተኛ ስርወ መንግስት (እንደ ግብጻውያኑ አጠራር “ኩሻዊ ስርወ መንግስት” የሚባለውን “ኢትዮጵያዊ ስርወ መንግስት” ሲል ይጠራዋል። ሌላው ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው ነጥሎ ህዝቦቿን ብቻ የሚመለከት መረጃ ያስተላለፈልን ስትራቦ ነው። ስትራቦ በድርሰቱ አፍሪካውያንና እስያውያን ምንም የሚለያይ ነገር የማይታይባቸው ተመሳሳይ ህዝቦች እንደሆኑ ያስረዳል። ፕሊኒ የተሰኘው ደራሲ ደግሞ ኢትዮጵያ የሚለው ስፍራ ስያሜውን ያገኘው ኢትዮጵ ከተሰኘው የቫልካን ልጅ እንደሆነ ያስረዳል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሴት ንግስታት “ቅንዳኬ” የሚል የማእረግ ስም እንደነበራቸው ይዘግባል። ጥንታዊ ሶርያንና የሜዲትራኒያን አካባቢንም እንደገዙ ያስረዳል። አውሳብዮስ ግሪኮ ሮማዊ ደራሲ ነው። ስለ ኢትዮጵያ የጻፈው ከሌሎች ይለያል። በእነሱ መረጃ መሰረት ኢትዮጵያውያን ከህንድ ሸለቆ ተነስተው በቀይ ባህር አካባቢ የሰፈሩ ናቸው። በአካባቢው ቀደም ሲል በዚህ ስም ይጠሩ እንዳልነበረ ዘግቧል፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top