ከቀንዱም ከሸሆናውም

መምህር አብራራው ማነው?

እንደዛሬው የኤፍ ኤም ሬዲዮ ባልተስፋፋበት በዚያ ዘመን (1950 ችና 60ዎቹ) ዓመታት አንዲቷ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ከፍተኛ ክብር ነበራት። የመረጃ፣ የመዝናኛ እና የትምህርት ሰጪነቷ ዋጋ ትልቅ ነው። ያልጠናበት ደሃ ካልሆነ በስተቀር በአዲስ አበባና የክፍላተ አገራት ከተሞች አብዛኞቹ ሰዎች ቤት ትንሽዬዋ ፊሊፕስ ወይንም ግሩንዲንግ ሬዲዮ አትጠፋም ነበር። እንደ አንድ የቤተሰብ አባል የምትታይና የምታሳሳም ነበረች። ታዲያ ሬዲዮኗ እንድትወደድ ካደረጉት ፕሮግራሞች መካከል የመምምህር አብራራው ፕሮግራም ተጠቃሽ ነው። ብዙዎች በአካልና በዋና ስሙ የማያውቁት መምህር አብራተራው፤ ከአድማጮች ለሚቀርብለት ማናቸውንም ጥያቄዎች በሚገባ በማብራራት አድማጮችን ያስደስታል።

 ዛሬም በሕይወት ያሉና በቅርብ የሚያውቁት ወዳጆቹ እንደሚናገሩት፤ መምህር አብራራው ትክክለኛ ስሙ መንግስቱ መኮንን ነው።

የቤተክህነት ትምህርት ያለውና የማይሰለች አንባቢ ነበር። ሰኔ 10/1957 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣ ላይ እንደሰፈረው መረጃ ከሆነ ደግሞ ፤ ከሚያዚያ 1/1954 ዓ.ም እስከ የካቲት 1957 መጨረሻ 65 ሺ ጥያቄዎች ለመምህር አብራራው ደርሰውታል። ከእነዚህ ውስጥ 15 ሺ ጥያቄዎች መልስ እንደሰጠባቸው ራሱ መምህር አብራራው (መምህር አብራራው) ተናግሯል።

ጥያቄዎቹ ማህበራዊ፣ ጾታዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ሳይንሳዊ፣ ፖለቲካዊ ዓለም አቀፋዊና ሌሎችም ሊሆኑ ይችላል። ከእነዚህ ውስጥ በዝተው የተገኙት የፍርድ ቤት ጉዳይ፣ በየ መንግስት መስሪያቤቶች የሚስተዋለው ቢሮክራሲ የመጀመሪያ ረድፍ ላይ ሲገኙ፤ የሴተኛ አዳሪዎች መብዛት፣ የመጠጥ ቤቶች መበራከት፣ የጋብቻ መርከስና የባህል መፋለስ በተከታይነት በዝተው የተገኙ መሆኑን ራሱ መምህር አብራራው በጋዜጣው ላይ በሰጠው ቃል አብራርቷል።

በቀልድና በጨዋታ አዋቂነቱ ብቻ ሳይሆን በታዋቂ ጋዜጠኝነቱና ታሪክ ጸሐፊነቱ የሚታወቀው ጳውሎስ ኞኞ አስደናቂ የዓለም ዙሪያ ክስተቶችን «አስደናቂ ታሪኮች» በሚል ተከታታይ ዕትም መጽሐፉ ሲያስደምመን ኖሯል። አጤ ምኒልክ በተሰኘው የታሪክ መጽሐፉ ደግሞ፤ ስለ አገራችን ካሰፈራቸው ድንቅ ነገሮች እነዚህን ታነቧቸው ዘንድ መረጥንላችሁ።

ቀንዳሙ ሰው

በአጤ ምኒልክ ዘመን አንድ ቀንድ ያለው ሰው ነበር አሉ። ይህ ሰው ገንዘብ እየተቀበለ ቀንዱን ለሰዎች ያሳያል። ገንዘብ ካልሰጡት ግን ቀንዱን በጨርቅ ሸፍኖ ይውላል። ይህንን ሰው አጤ ምኒልክ አይተው፣ በቀንድ አበቃቀሉ ተደንቀው እርሳቸውም እንደሌሎች ሰዎች ገንዘብ ሰጥተውት ልብስ አልብሰውታል።

ግዙፉ ቡሃቃ

እንጦጦ ማሪያም ህንጻ ቤተክርስቲያን ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር ታላቅ ድግስ ነበር። ለዚህ ድግስ እንጀራ ለመጋገር የተዘጋጀው ሊጥ ማቡኪያ (ቡሀቃ) አንዱ ብቻ እስከ 40 ኩንታል ዱቄት ድረስ የሚያስቦካ ነበር። የቡሀቃውን ትልቅነት ለማወቅ አርባ ኩንታል ዱቄት ለማቡኪያ የሚገባበትንም ውሃ አብሮ ማሰብ ነው። ሊጡ በሚወጣበት ጊዜ ሊጥ አውጪዎቹ ቡሃቃው ላይ በመሰላል እየወጡ ነበር አሉ የሚያወጡት። ለዝግጅቱ ምን ያህል ቡሃቃ አገልግሎት እንደሰጠ ጳውሎስ ባይገልፅም፤ በዚህ ግዙፍ ድግስ ምን ያህል ሰው ሊታደም እንደሚችል፣ በድግስ ዝግጅቱ ምን ያህል ሰው ተሳትፎ እንደሚኖረው አብሮ ማሰብ ነው እንግዲህ?

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top