ከቀንዱም ከሸሆናውም

ፈላጊ እና ተፈላጊ

ወዳጅ ወዳጅ ምንም ቢፋቀሩ

እንቁጣጣሽ የለም ሰው ሁሉ ባገሩ

በጣም ብንስፋፋ ፍቅር እንደዋዛ

 ብቻ የኛ ሀገር እንቁጣጣሽ በዛ

“የፍታሔ አዲስ አበባ ሁኖ የድንግል ሀገሩን ዕድል ፈንታዋን ጽዋ ተርታዋን እያሰላሰለ ምናልባት በ1924 ዓም የተቀኘው የአማርኛ ቅኔ ትዝ ሳይለው አልቀረም።” ይላል ዮሐንስ አድማሱ ጽፎት ወንድሙ ዮናስ አድማሱ በአሰናኙት “ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ አጭር የሕይወቱ እና የጽሑፉ ታሪክ” በሚለው መጽሐፍ ውስጥ።

ጣሊያን ሀገራችን በመውረር አዲስ አበባ ሲገባ ዮፍታሔ በስደት ወደ ሱዳን ሔዶ ነበር። ስደት ላይ እያለ ለፊተውራሪ ታፈሰ ሀብተ ሚካኤል ከፃፈው ደብዳቤ እና ዮሐንስ የብላታ መርስኤ ባለቤት እታገኘሁ ባየ እንዳወገኙ ብሎ በመጽሐፉ ካሰፈረው በጥቂቱ የተወሰደው ደግሞ እንዲህ ይላል።

“አዲስ አበባ የሰው ምርጫ ተደርጎመያዝ ሲጀምሩ እኔን በምርጫ ጊዜ ምንም እንደማይለቁኝ አውቃለሁ እና በተሎ ባለቤቴንና ልጆቼን የማሸሽበት ስፈልግ እኔ ቦታ ፍለጋ  ዮፍታሔ ማልዶ ከቤቱ ወደ ጓሮ እዳሪ ወጥቶ ሳለ ጣሊያኖቹ ሲመጡ አይቷቸው ኑሮ፤ ግራ ቀኝ ሳይል በቀጥታ ወደ እነሱ ሔደ። ደግነቱ ዮፍታሔ ንጉሴ መሆኑን አልጠረጠሩም ነበር እና እንዳዩት የዮፍታሔ ቤት የትኛው እንደሆነ ጠየቁት፤ ቤቱን አሳያቸው። አረጋገጠላቸው ”

በሔድኩበት እነሱ እቤቴ ገብተው እኔን ቢያጡ የተገኘውን ዕቃ ዘርፈው ወሰዱ። ይህንንም እቤቴ ሳልደርስ በመስማቴ እንደወጣሁ ቀረሁ። ያገሬ ልጆች በሙሉ በከተማው ውስጥ እየፈለጉኝ መውጫ በማጣቴ 9 ቀን ብርሃን ሳላይ በከተማ ውስጥ አንዱ ወዳጄ ቤት ሰነበትሁ። አለሁበት ቤት ጠላቶቼ ያዩኝ ነበር። እኔ ግን የምሸሸው ተአገራችን ልጆች ነው፤ ጠላቶቻችንም ምኔን ያውቃሉ።

 ዮፍታሔና ብላታ መርስዔ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ እቤታቸው ነበሩ። በዚሁ ቀን ጠቋሚዎች በሁለቱ ላይ የላኳቸው ጣሊያኖች መጡ። ከጠቋሚዎቹ አንዱ ወልደአማኑኤል የሚባል ባንዳ ነበር። ጣሊያኖቹ የመጡት ከወደ ራስ ሥዩም ሠፈር ነበር። ዮፍታሔ ማልዶ ከቤቱ ወደ ጓሮ እዳሪ ወጥቶ ሳለ ጣሊያኖቹ ሲመጡ አይቷቸው ኑሮ፤ ግራ ቀኝ ሳይል በቀጥታ ወደ እነሱ ሔደ። ደግነቱ ዮፍታሔ ንጉሴ መሆኑን አልጠረጠሩም ነበር እና እንዳዩት የዮፍታሔ ቤት የትኛው እንደሆነ ጠየቁት፤ ቤቱን አሳያቸው። አረጋገጠላቸው። ጣሊያኖችም የነገራቸውን ሁሉ ውጠው ወደ ቤቱ ሲሔዱ እሱም እጥፍ ብሎ መንገዱን አሳብሮ ሄዶ አመለጣቸው። ሄዶ ቀበና አደረ። ጠፍቶ ከሰነበተ በኋላ ብላታ መርስኤ አግኝተውት ነበረ።

 ያገኙትን ጽሕሙን እንደመላጨትም እንደማሳደግም አድርጎ የቄስ ልብስ ለብሶ ነበረ። “አስቀድሞ በእጁ ጠቀስ ጠቀስ አደረገኝ፤ መጀመሪያ ለመለየት አልቻልሁም ነበር፣ ኋላ ግን ፈገግ፣ ሳቅ ሲል አወቅሁት” ይላሉ ብላታ መርስኤ። እሱም መንገዱን፣ እሳቸውም መንገዳቸውን ሄዱ። እንደገና የተያዩት ከአምስት ዓመት በኋላ ነበር።

ከዓሊ ቢራ ጀርባ የነበረው

ታላቅ የጥበብ ሰው

ከታዳጊዎች መካከል በድምፁ ቅላፄ ለየት ያለ ሆኖ የተገኘው ዓሊ መሐመድ ሙሳ የሚባል ጠይም ኮበሌ ነው። የቡድኑ ሊቀመንበር የነበረው ሰው “ፋአዲ ቀልቢ” የሚባል የዘመኑን ተወዳጅ የግብፃውያን የዐረብኛ ዜማ “ቢራጳ በርኤ” (መስከረም ጠባ፣ ፀሐይ ሆነ) እንደማለት ነው። ወደ ኦሮምኛ ቀይሮት ፃፈው እና ለታዳጊው ዓሊ መሐመድ ሙሳ ሰጠው። የዘፈኑ አዝማች ወደ አማርኛ ሲተረጎም “መስከረም ጠብቷል የአበቦች መአዛ ያውዳል፣ ምን ጥፋት አለብኝ አምላኬ ሆይ ! ለኔ ምን ይበጃል?”። የሚል ነበር።

 ህዝቡ ዘፈኑን ሲሰማ በከፍተኛ ጭብጨባ ነው የተቀበለው። “ቢስ…ቢስ” እያለ ደጋግሞ እንዲዘፍን አደረገው። በሌሎች መድረኮችም በተመሳሳይ መልኩ ቀጠለ። በሰርግ ቤትም ሆነ በበዓላት ዝግጅት “ቢራጳ በረኤ” እጅግ ተመራጭ ዜማ ሆነ። ህዝቡ እርሱ ያለተዘፈነበትን ዝግጅት ለመታደም እምቢ አለ። የድሬዳዋ ህዝብ በስልጣኑ የታዳጊውን ስም “ከዓሊ መሐመድ ሙሳ” ወደ “ዓሊ ቢራ” ቀየረው።

 ለዚህ ቀጫጫ ልጅ መታወቅ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያደረገው የመጀመሪያ ዘፈኑን ጽፎ የሰጠው ደራሲ ነው። በቀጣዮቹ አመታትም ይኸው ደራሲ እጅግ ውብ የሆኑ ግጥሞችን እየፃፈ በዓሊ ቢራ በኩል ለህዝብ ጀሮ አድርሷል። እንደ “ኮቱ ያ ቢፍቱ ቲያ”፣ “ሲንበርባዳ”፣ “ሲጃሌ ጀላላ ዴይማ”፣ “አማሌሌ” እና ሌሎችንም ምርጥ ዜማዎችን የፃፈውና ከዓሊ ቢራ ጀርባ የነበረው ታላቅ የጥበብ ሰው “አቡበከር ሙሳ” ይባላል።

በኢትዮጵያም ሆነ በኦሮሞ ህዝብ የኪነ- ጥበብ ታሪክ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ገጣሚ፣ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ፣ ጸሐፌ ተውኔት እና የታሪክ ምሁር ነው።

 አቡበከር ሙሳ በ1935 በሐረርጌ ክፍለ- ሀገር በአቦራ (ወበራ) አውራጃ ከዳደር ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው “ሌሌ ገባ” በተሰኘች ትንሽዬ የገጠር መንደር ተወለደ።

በልጅነቱ እስላማዊውንና የዐረብኛ ቋንቋ ትምህርቶችን አጥንቷል። ከእዚያም ለተሻለ ትምህርትና ለሥራ ፍለጋ ሲል የገጠሩን ህይወት ትቶ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ተሰደደ። እጅግ ፈጣን አእምሮ የነበረው ታዳጊ በመሆኑ በድሬዳዋ ከተማ በሚገኝ አንድ መድረሳ በዐረብኛ ቋንቋ አስተማሪነት ተቀጠረ። የመድረሳውን ሥራ እየሠራ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር የ“አፍረን ቀሎ”ን ቡድን መሠረተ።

 አቡበከር ለስምንት ዓመታት ቡድኑን በሊቀመንበርነት በመያዝ በኦሮምኛ ቋንቋ እድገት ከፍተኛ አሻራ ጥለው ያለፉ ሥራዎችን ሠርቷል።

በአፈንዲ ሙተቂ ከተፃፈው “ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ድሬዳዋ” ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ።

የእንግሊዝ ወታደሮችና ሰንደቅ ዓላማችን

የእንግሊዝ መንግሥት ንጉሠ-ነገሥቱ በቅድሚያ አዲስ አበባ እንዲገቡ አልፈለገም። በእዚህ ምክኒያት ከእንግሊዝ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ጃንሆይም ራስ አበበም ቀድመው አዲስ አበባ ለመግባት አልሞከሩም። ስለዚህ ሰሙኑን ልባችን ተሰቅሎ በናፍቆት ስንጠባበቅ የአቶ ዓለመ-ሥላሴ ታናሽ ወንድም ጓንጉል ጎላ የሚባል “ጋሼ እንግሊዞችን ባራት ኪሎ ሲያልፉ አየሁዋቸው” አሉኝ። ይላሉ ተክለፃድቅ መኩሪያ ስለ ህይወት ታሪካቸው በፃፉት “የህይወቴ ታሪክ” በተሰኘው መጽሐፋቸው።

ተክለፃድቅ እንግሊዞችን ፍለጋ ከጓንጉል ጋር በታክሲ አራት ኪሎ ቢደርሱም ሊያገኟቸው አልቻሉም። ላይኛውንም ታችኛውንም ግቢ ተመልክተው ወደ አራዳ ይመለሳሉ። ጓንጉልን አሰናብተው በእግራቸውበማስታወቂያ ሚኒስቴር በኩል ሲያልፉ ከኢጣሊያኖች ለየት ያለች እና አቧራ የጠገበችመኪና ይመለከቱና ጠጋ ብለው ሲያረጋግጡየእንግሊዞች መሆኗ ይገባቸዋል። አጠገቧ ቆመው ሲጠባበቁ የእንግሊዝ መኮንኖች ይመጣሉ።

ከእዚህ በኋላ ወደ ኋላዬ ተመልሼወደ ከተማው ሳመራ ወሬውን ሰው ሁሉሰምቶ በየወገኑ ተሰብስቦ መወያየት መጨፈር መዘመር ሲይዝ እንግሊዞች ደግሞ በየመኪና በየኦቶቢስክሌት በብዛት መግባት ጀመሩ። የደስታው መጯጯህና ግርግርታው ሲቀልጥወዲያው ጄኔራል ካኒንግሃም የእንግሊዝ ንባንዴራ ሲሰቅል ይዘምር በደስታ ይጯጯ ህየነበረው ሰው ባንድ ጊዜ እርጭ አለ።

ጄኔራሉም ነገሩ ገብቶት “አሁን የእንግሊዝ ባንዴራ የሰቀልነው ከተማዋን በወታደርነት የያዘው የእንግሊዝ ጦር ስለሆነ ነው። የናንተን ባንዴራ ግን ወደፊት ንጉሠ- ነገሥቱ ወይም ራሥ አበበ ሲገቡ ይሰቅላሉ ብለን በማሰብ ነው። አሁን ግን ቅሬታችሁ ስለተሰማን እታችኛው ግቢ እንሰቅልላችኋለንና ወደዚያ ሂዱ” ብሏል እና ወደዚያ እንሩጥ ስለተባለ ሰው ሁሉ ያቆመውን ግርግርታና የደስታ ዘፈን መዝሙርም እየዘመረ ወደ ታችኛው ግቢ እየተዥጎድጎደ ወረደ።

ታዲያ እንግዲህ አንቺ ኢትዮጵያ እኛስ ልጆችስ

ምንድን ነን

አመንኩሽ ማለት የማንችል፣

 ፍቅራችን የሚያስነውረን

እዳችን የሚያስፎክረን

ግፋችን የሚያስከብረን

ቅንነት የሚያሳፍረን፣ ቂማችን

የሚያስደስተን

አረ ምንድነን? ምንድን ነን?

አሚኬላ እሚያብብብን

ፍግ እሚለመልምብን

ከአረም ጋር ያፈራን ጊንጦች፣

ከእንክርዳድ ያልተለየን ዘር

ግርዱ ከምርቱ ተማጥቆ፣ ከቶ

ያልተበራየን መከር

ምንድነን? ምንድነን እኮ?

ከሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

“ታሪካዊ ተውኔቶች” መጽሐፍ

ከቴዎድሮስ ተውኔት የተወሰደ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top