ጥበብ በታሪክ ገፅ

የሴት ተዋናይንት ጉዞ ወደ ፕሮፌሽናሊዝም- በኢትዮጵያ

ትያትር የሚባል ነገር ወደ ኢትዮጵያ የገባው ዳግማዊ ምኒልክ የአውሮፓን ስልጣኔ ወደ አገር ለማስመጣት ካላቸው ፍላጎትና ከአድዋ ጦርነት ጋር በተያያዘ ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። ጃንሆይ አድዋ በዘመቱበት ወቅት የራስ መኮንን ጦር መቀሌ ከመሸገዉ የጣሊያን ጦር ጋር ይገጥማል። በጦርነቱ ላይ የራስ መኮንን ልዩ ጸሃፊ ይሰዋል። ልዩ ጸሃፊው ታናሽ ወንድሙን፣ ህጻኑን ተክለሀዋርያት ተክለማርያም ዋየህን ይዞ ነበርና የዘመተው፣በጸሃፊያቸው ሞት ክፉኛ ያዘኑት መኮንን ህጻኑን ወደራሳቸው ድንኳን አስመጥተው እንደልጃቸው ይንከባከቡታል ። ከአድዋ ድል በሁዋላም በሚቀመጡበት ፈረስ ላይ አፈናጥተውት እያጫወቱት ሀረር ግዛታቸው ይወስዱታል። እዚያም እቤታቸው ያኖሩታል። በዚያ መሀል ከሩሲያ ልኡካን ጋር ይገናኙና አገራቸው ወስደው እንዲያስተምሩት ያግባቧቸዋል። እሽታቸውን እንዳገኙ አጼ ምኒልክን ያማክራሉ። ይፈቀድና ተክለሀዋርያትም ከፈረንጆቹ ጋር ወደሩሲያ ሄዶ የጦር ትምህርት ይማራል። ከአመታት በኋላ በመድፈኛ ኮሎኔልነት ተመርቆ ወደአዲስ አበባ ይመለሳል።

 አንድ ቀን ታዲያ ከከንቲባ ሂሩይ የተላከ የግብዣ ደብዳቤ ይደርሰዋል።- “ይምጡና ትያትር ይመልከቱ” የሚል። በደስታ ተነስቶ ቴራስ ሆቴል (የዛሬዉ የሜጋ ትያትር አዳራሽ) እንደታደመ የቀረበው ትርኢት ትያትር ሳይሆን ዘፈንና ጭፈራ ሆኖ ያገኘዋል። ዘፈንና ጭፈራ እንደትያትር በመቆጠሩ ቅሬታ ያሳድርበታል። በአዉሮፓ የተስፋፋውና የተለመደው ትያትር በአገራችን ባለመተዋወቁም ያዝናል። ይህን ክፍተት ለመሙላት ሲል አዉሮፓ ውስጥ ባየው ድራማ መልክ የአውሬዎች ኮሜዲያ መሳለቂያ የተሰኘ ተውኔት ደርሶ ልጆችን በማለማመድ ያዘጋጃል። በተውኔቱ ውስጥ ሴት ገጸባህርያት ቢኖሩም፣ ዘመኑ ሴት ከአደባባይ እንድትወጣ የማይፈቅድ ነበርና የሴቷን ሚና የተወኑት ወንዶች ልጆች ነበሩ። እንዲያ ሆኖ ልኡል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን በተገኙበት ለመኳንንቱና ለመሳፍንት አሳይቶ ጉድ! አስባለ፤-በ1914 የመጀመር ወራት ላይ።

 በማግስቱ ግን ያጋጠመው ያላሰበው ነበር። አንዱ ወሸከቴ ንግስት ነገስታት ዘውዲቱ ዘንድ ቀርቦ ‹ይሄ ነገር መንግስትዎን የሚነካ ነው።› ብሎ ሹክ አለ። ንግስት ነገስታት ቱግ! አሉና ልኡል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንንን አስጠርተው መመሪያ ሰጡ። ‹በል ይሄ የተክለሀዋርያት ተክለ ማርያም ነገር ዳግመኛ እንዳይታይ። ደግሞ አጽፎ ሸጧል አሉ›። አልጋወራሽ ወዲያው ተክለሀዋርያትን አስጠርተው በንግስት ነገስታት ቅሬታ ድራማው መታገዱን ገለጹለት። የታተመው ተውኔት ተሰብስቦ ታሰረ። ትያትር በአገራችን ገና በመጀመሩ የመንግሰት ኩርኩም ቀመሰ።

 ከዚያ በሁዋላ ትያትር የሚባልን አስፈሪ ነገር ማን ይነካ! ያኔ በነበሩት ሁለት ትምህርት ቤቶች( ዳግማዊ ሚኒልክ እና ተፈሪ መኮንን ት/ ቤት) ውስጥ ብቻ ፈረንጅ መምህራን የታዋቂ ደራሲያንን ተውኔቶች ቀንጨብ እያደረጉ ከእንግሊዝኛ ወደአማርኛ በማስተርጎም በክፍል ውስጥ ልጆች እንዲማሩበት ያደርጉ ነበር። ዮፍታሄ ንጉሴና መላኩ በጎሰው የሚባሉ ከጎጃም የመጡት ሁለት ደብተራዎች የአማርኛና የግብረገብ አስተማሪ ሆነው ተቀጥረው ነበርና የተተረጎሙትን ተውኔቶች እንዲያለዝቡ እየታዘዙ፣ እግረመንገዳቸውን ከተውኔት ባህርያት ጋር ሊተዋዋቁ በቁ። እነሱም መንገዱን ተከትለው፣ደግሞም ከቤተክህነት ዜማና ውዝዋዜ ጋር አዋዝተው፣ ንግስት ነገስታትን አስፈቅደው ድንቅ ድራማዎችን መመደረክ ጀመሩ።

 ይሁንና፣ ሴት ገጸባሕርያትን የሚተውኑ ሴት ተማሪዎችን ለማግኘት አልቻሉም ነበር። የነበራቸው አማራጭ፤ መልኩ ያማረን ተማሪ ቀሚስ አልብሰው፣ ሻሽ አሳስረው ሴት ማስመሰል ነበር። ያኔ ተደራሲው ወንዱ እንደሴት ሲጫወት አውቆ እንዳላወቀ ይሆን ነበር። ትያትር እንዲያ እያለ ለአስራ አንድ አመታት የወንድ ብቻ መድረክ ሆኖ ከቆየ በኋላ በዮፍታሄ ልዩ ጥረት ችግሩ ትንሽ ተቀረፈ። ወቅቱ ሴቶች እንኳንስ ህዝብ በተሰበሰበበት መድረክ ላይ ወጥቶ መጫወት ይቅርና፣ቀና ብለው ሰው ካዩ የሚወገዙበት ነበር። ሌላው ቀርቶ በአንድ ክፍል ውስጥ ከወንዶች ጋር ተደባልቀው ለመማር የማይፈቀድላቸው ዘመን ነበር። ለሴት ውበትዋ፣ ክብርና ሞገሷ አንገት መድፋትና አይን አፋርነት በነበረት ዘመን ዮፍታሄ ሴት ተማሪዎችን አግባብቶ ለማደፋፈርና የቤተሰባቸውን ይሁንታ ለማግኘት መቻሉ በኢትዮጵያ ትያትር ታሪክ ውስጥ እንደፋና ወጊ- ፈር ቀዳጅ የሚያስከብረው ነው።

 ዮፍታሄ የቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ዲሬክተር ሆኖ እንደተሾመ ፣ህዳር 11 ቀን 1925 በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተገነባው የመጀመርያው ያገራችን ከፊል- መደበኛ የትያትር አዳራሽ «TÃTa› መድረክ ላይ በዳዲ ቱራ ተውኔት ውስጥ ሴት ተማሪን ለመጀመርያ ጊዜ አስተወነ። ቀጸላ አንዳርጌ የጅፋሬን ገጸባህርይ፣ አሰለፈች ማሞ ደግሞ አያንቱን ሆነው በመተወን ተደራሲን አስደምመዋል። ቀጸላ አንዳርጌ ሶረቲዬ የሚለውን ዜማዊ ድራማ ታወርድ በነበረበት ወቅት የሰው አድናቆት እጅግ የላቀ ነበር። አብሯት ሲተውን የነበረው በለጠ ገብሬ እንደገለጸው፤-

 ቀጸላ አንዳርጌ በተሳተፈችባቸው ትርኢቶች ሁሉ የኮከቦች ኮከብ ለመባል የበቃች ግንባር ቀደም አርቲስት ነበረች። ይህም በአነጋገር ችሎታዋ ፣ባቀራረብ ስልቷና ከሊቁ ደራሲ ባጠናችው ጣፋጭ ዝማሬዋ ማራኪነት ብቻ ሳይሆን፣በተፈጥሮ ጸጋ በታደለችው አይን አገላለጽዋ፣ ብሩህ ጠይም መልኳ፣ሙሉ ቅርጽ አካሏና ጠቅላላ እንቅስቃሴዋ እድምተኞችን አይን የሚስብ ልዩ ተሰጥ ስላጎናጸፏት ነበር።

 በሀምሌ1926 በቀረበው የዮፍታሄ የህዝብ ጸጸት የመየት በልዩ ጉዳት ሴት ተማሪዎች የመሸታ ቤት አስተናጋጆችን፡- እመየት በልዩን፣ እመየት ቸኮለችና እመዬት አርምጃቸውን ተመስለው በሚያስደንቅ ሁኔታ ተውነዋል። ቀጸላ አንዳርጌ እመየት በልዩን ሆና በመተወን አንደኛ ወጥታ የወርቅ ዘቦ፣ ቦርሳና የብር ሰአት ከንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ተሸልማለች። አሰለፈች ማሞ እመየት †¢K‹” መስላ ድንቅ በመተወኗ እንዲሁ ሁለተኛ ተሸላሚ ሆናለች‹:: ጸዳለ ሸዋረጋ እመየት እርምጃቸውን ተጫውታ ተሸልማለች። አሰለፈች ማሞ ስላሳየችው የትወና ብቃት በበለጠ ገብሬ እንዲህ ያስታውሳል፡-

እመየት ቸኮለች የሚል ስም ተሰጥቷ እንደ ጠጅ ኮማሪት ሆና ስትጫወት ሀር ነዶ መሳይ ክምር ጎፈሬዋን በደንብ አበጥራ፣ በጥበብ ኩታና በአሸብሻቦ ቀሚስ ሽቅርቅር ብላ ሳብ ረገብ ባለው ሽንጥና ዳሌዋ እያረገረገች በጠጪዎች መሀል ሽርጉድ በማለት አይነገብ አይኖቿን ግራና ቀኝ ሰረቅ፣ነጫጭ ጥርሶቿን ፍልቅ እያደረገች ስትሽኮረመም ፍጹም አራዳዋን የነጋድራስ ቀጸላ ልጅ መስላ የታየችው አሰለፈች ማሞ ነበረች። 

 በአንድ ቀን አከታትላ በተጫወተችባቸው ሁለት ተውኔቶች የነበራትንም ክህሎት እንደሚከተለው ያስረዳል፡- በሌላው መድረክ ላይ ከቅዱሳን እንስት

“ፋሺስት ኢጣሊያን ሚያዝያ 27 ቀን 1928 አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ትያትረኛው ሁሉ ለአርበኝነትና ለስደት በመውጣቱ ለአምስት አመታት የትያትር እንቅስቃሴ ተቋረጠ። ዮፍታሄ ስደት ላይ ሱዳን በነበረበት ወቅት ሴትና ወንድ ወጣቶችን በሙዚቃና በትያትር አደራጅቶ እንግሊዝ አገር እንዲወስድ ስደት ላይ የነበሩት ንጉሰ ነገስቱ አዘውት የነበረ ቢሆንም፣ሁኔታው ሳይፈቅድለት ቀርቶ አላሳካዉም።”

አንዷን ተመስላ በቀረበች ጊዜ፣ አንደወንጌሉ ቃል ራሷን ሸፍና፣እስከ አግር ጥፍሯ ድረስ የተዘናፈለ የጥንቱን ያገር ልብስ ግርማ ተጎናጽፋ፣ምእመናንን ሁሉ በታላቅ ትህትና ስታገለግልና ድኩማን ነዳያንን በርህራሄ ስሜት ከልብ ስትረዳ የተመለከተና፣በለስላሳ ድምጹዋ የሚፈልቀውን መንፈሳዊ ቃላት የሰማ ሰው ሁሉ፣ ሁለቱንም ተውኔት በተለያየ ጠባይ የተጫወተችው አንዲቷ አሰለፈች መሆኗን ለማመን እስኪቸግር ድረስ፣ የብልህነት ችሎታዋን በስራ ያሳየች ንቁ ባለሙያ ነበረች።

 ከዚያም ኋላ በነበሩት ጥቂት አመታት በዮፍታሄ፣ በመላኩ በጎሰው፣ በሀዲስ አለማየሁ የተደረኩት ስድስት ተውኔቶች ሴቶችን ስለማሳተፍ አለማሳተፋቸው የታወቀ የለም። የጣሊያን ወረራ እየተቃረበ በመሆኑም፣ የእነዚህ ትያትረኞች ትኩረት ከትያትር አቅርቦት ይልቅ፣ ሀምሌ 17 ቀን 1927 አራዳ ጊዮርጊስ በተመሰረተው የሀገር ፍቅር ማህበር ጸረ ወረራ የቅስቀሳ ተልእኮ ላይ ሆኗል። ህዝብ ወረራውን እንዲመክት፣ዮፍታሄና በመላኩ ከባልደረባዎቻቸው ጋር ከአራዳ ጊዮርጊስ በታች በነበረው ሜዳ ላይ ዲስኩር በማድረግ፣ግጥም በማንበብ ህዝቡን ሲያነቃቁ፣ ሴቶቹ እነ ሸዋረገድ ገድሌ፣አሰገደች ከበደና አበበች ጨርቆሴ በመሀል በመሀል ሽለላ፣ ፉከራና ቀረርቶ እያሰሙ ህዝብን ለአርበኝነት ለመቀስቀስ ያበረከቱት አስተዋጽኦ እጅጉኑ ውጤታማ ነበር። ሴት አርበኞቹ የእንግሊዝ ቅድ ሱሪ ላይ ኮት ደርበው፣ ሽጉጥ ታጥቀው፣ በየተራ ወደህዝብ መሀል እየገቡ‹ ለውዲቱ አገሬ እሞታለሁ፣ከወንድሞቼ ጋር ዘምቼ እዋጋለሁ፣ዘራፍ! ዘራፍ1› እያሉ እየተንጎራደዱ ሲፎክሩ የታዳሚ ወኔ ይግል ነበር።

ፋሺስት ኢጣሊያን ሚያዝያ 27 ቀን 1928 አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ትያትረኛው ሁሉ ለአርበኝነትና ለስደት በመውጣቱ ለአምስት አመታት የትያትር እንቅስቃሴ ተቋረጠ።

ዮፍታሄ ስደት ላይ ሱዳን በነበረበት ወቅት ሴትና ወንድ ወጣቶችን በሙዚቃና በትያትር አደራጅቶ እንግሊዝ አገር እንዲወስድ ስደት ላይ የነበሩት ንጉሰ ነገስቱ አዘውት የነበረ ቢሆንም፣ሁኔታው ሳይፈቅድለት ቀርቶ አላሳካዉም።

ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ከንጉሰ ነገስቱ ጋር፣ አርበኛውና ስደተኛው በድል አድራጊነት አዲስ አበባ በገባ ከጥቂት ወራት በኋላ ማለትም ሀምሌ 20 ቀን 1933 ዮፍታሄ አፋጀሽኝ የተባለውን ተውኔት አዘጋጅቶ የቤተ-መንግሥት ግብር በተሰናዳበት (ምናልባትም ዛሬ የዩኒቨርሲቲ ባህል ማእከል አዳራሽ በሆነው) ባሳየበት ወቅት እንደ 1920ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ሴት ተማሪዎችን አላሳተፈም። የአፋጀሺኝ ሴት ገፀ-ባህርይ ያስወከለው በለጠ ገብሬ በተባለ የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተማሪ ነበር። ዮፍታሄ በዚያን ወቅት የትምህርት ቤት መምህርና ዲሬክተር ስላልነበረ ሴት ተማሪን ለመመልመል ሁኔታው ሳያመቸዉ ቀርቶ ይሆናል- ይህ የሆነው። በለጠ ገብሬ ኢትዮጵያን የተመሰለችውን አፋጀሽኝን በሚያስደንቅ ሁኔታ በመጫወቱ ከጃንሆይ ሰላሳ የማርያ ትሬዛ ብር ተሸልሟል። እንደሴት በመተወን ባሳየው ችሎታ ከበሬታን አግኝቶ፣ መንግስት በ1934 የጀግኖች ማህበር ትምህርት ቤትን ( የአሁኑን የአርበኞች ት/ ቤት) ሲከፍት በትያትርና ሙዚቃ መምህርነት ሊቀጠር በቃ። እዚያም ሳለ ባዘጋጃቸው በራሱ ተውኔት – ላም ሲበዘበዝ ጭራውን ያዝ፤የምን መፍዘዝ ፣ በመምህር አርአያ ወልደ ጻድቅ አዶንያስ ፋሽስት እና በአፈወርቅ አዳፍሬ ላገር መሞት ተውኔቶች ውስጥ የሴት ገጸባህርያትን የተወኑት ወንዶች ተማሪዎች ነበሩ። በላገር መሞት ተውኔት ውስጥ እናት ኢትዮጵያን ተመስሎ እንደሴት የተጫወተው እጓለ ዘውዴ ንጉሰ ነገስቱን በማስደነቁ ሀምሳ ማርያ ትሬዛ ብር ተሸልሟል። (በነገራችን ላይ ‹ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፣የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ› የሚለው ግጥም በዚሁ በአፈወርቅ አዳፍሬ ተውኔት ውስጥ የሚገኝ ሀይለቃል እንጂ ብዙዎቹ እንደሚጽፉት ዮፍታሄ ንጉሴ የገጠመው ግጥም እይደለም።)

ዮፍታሄ፣ ከዚያ በኋላ ህይወቱ እስካለፈችበት እስከ ሀምሌ 1ቀን 1939 ባዘጋጃቸው ሶስት ተውኔቶች ማለትም ዓለም አታላይ፣እያዩ ማዘን፣ እና ዕርበተ ፀሐይ ውስጥ የሴቶቹን ሚና ያጫወተው ወንዶች ተማሪዎችን ነበር። አለም አታላይ ውስጥ እንደ ሴት የተወነውን ልጅ ፣‹በሴት አንቀጽ ሆኖ አይኗን ስልምልም፣ ቅንድቧን ስብርብር እያደረገች በሰራችው ስራ ስታስቅ ነበር› ተብሎ የወቅቱ ጋዜጣ አድንቆታል።

በ1934 በሻህ ተክለማርያም፣ የመጀመርያውን ሁለገብ ፕሮፌሺናል የስነጥበብ ማእከል፣የሀገር ፍቅር ማህበርን (የዛሬውን ሀገር ፍቅር ትያትር) እንዲያቋቁም ሀላፊትን እንደተሰጠው ከመለመላቸው 40 ከያንያን ውስጥ 14 ሴቶች ነበሩ። (በሻህ ተክለማርያም ተማሪ ሳለ በዮፍታሄ ተውኔቶች ውስጥ ተውኗል። ‹በዚያን ዘመን ከዮፍታሄ ድራማዎች አንዱን ክፍል ሲጫወት፣ኢትዮጵያ ባንዲት ቆንጆ ተመስላ የጥንቱን ጀግኖቿን ድፍረትና ወኔ በወጣት ልጆቿ መንፈስ ውስጥ ለመቅረጽ፣ጥንታውያኑን በፍቅር አምሳል ‹ ናናና ..ናና ናና ናና! ና!ና!… እያለች የሰቀቀን ዜማዋን ለማሰማት እጇን በማርገብገብ በጠቀሰችው ጊዜ የጀግኖቹን መንፈስ የተመሰለው ተናፋቂ አርበኛ በሻህ እንደመረዋ የሚያስተጋባ ወንዳወንድ ድምጹን ዘለግ አድርጎ በመልቀቅ ‹ነይ! ነይ! ነይ!ነይ! ነይ! ነይ! ነይ! ነይ!.› እያለ በትካዜ ሲያንጎራጉር አድማጩን ሁሉ አፍዝዞ የግል ትዝታ ሰመመን አስይዞታል› የተባለለት ነው።)

በሻህ ተክለማርያም የመለመላቸው በአብዛኛው በየመሳፍንቱና በየመኳንንቱ ድግስ ላይ፣ እንዲሁም በየኮማሪቱ ቤት እየዘፈኑ በማዝናናት የሚታወቁ አዝማሪዎችን ሲሆን፣ እነሱም ንጋቷ ከልካይ፣ ሽሽግ ቸኮል፣እታገኘሁ ሀይሌ፣ አሰለፈች ሙላት፣ ዘነበች ግዛው፣ ማናህሌ ማሞ፣በየነች አሊ፣አለሚቱ ተፈራ፣ ከበቡሽ ይመር፣ዘነበች መንገሻ፣በላይነሽ ውብአንተ፣ደመቀች አሊ፣ወርቄ መንገሻና አሰገደች ለማ ነበሩ። ይሁንና እነዚህ ሴት ከያንያን ከድምጻዊነትና ተወዛዋዥነት አልፈው በድራማ ውስጥ ለመተወን በወቅቱ የነበረው ማህበረሰባዊ ጫና ነጻ አላደረጋቸውም ነበር።

በእንዲህ ያለ ሁኔታ አመታት ቆይቶ፣በ1939 ሌላ ትያትር ቤት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተከፍቶ አገልግሎት በጀመረበት ወቅትም ቢሆን ሴቶችን በተዋናይነት ከመድረክ ለማጫወት የተመቸ አልነበረም። ሴቶች ድፍረት አንሷቸው ይሆናል በሚል አስተሳሰብ በየመሸታ ቤቱ በማስተናገድ ድፍረትን ገንብተዋል የሚሏቸውን ሴቶች እያግባቡ ጥቂቶችን ለማለማመድ ቢሳካላቸውም፣ የድራማው ማሳያ ቀን ሲቃረብ እየጠፉ አቅርቦቶች ተስተጓጉለዋል። እንደምንም ተብሎ ግን፣ ዝነኛዋን ኮማሪት አሰገደች አላምረውን በማዘጋጃ ትያትር ማደራጃ መድረክ፣ አሰለፈች ሙላትን በሀገር ፍቅር ማህበር መድረክ አንዳንዴ በአጃቢነት ለማሰለፍ ተችሎ ነበር። የማዘጋጃ ትያትር ማደራጃ ከወንዶች በተሻለ ክፍያ ዘበናይ ዘለቀንና አስካለ ብርሀኔን ለተዋናይነት ቢቀጥርም ነገሩ አልጥም ብሎዋቸው ስራቸውን ሊለቁ ተገደዋል።

ስለዚህም እንደዱሮው የትምህርት ቤት ትያትር ልማድ፣ ወንዶች የሴቶችን ገጸባህርይ ሊጫወቱ ግዴታ ሆነ።

በሁለቱ ትያትር ቤቶች እንደ ሴት ይተውኑ ከነበሩት ውስጥ ተስፋዬ ሳህሉ፣አውላቸው ደጀኔ፣ተፈራ አቡነወልድ፣መአዛ ማሞ፣ ወዳጀነህ ፍልፍሉ፣ሀይለ ልኡል ገብረማርያም፣ጌጤ ታደሰ፣ ስለሺ ገብረ ስላሴ፣ለማ ወርቄ፣ኢዩኤል ዮሀንስ፣ግርማ ብስራት፣ፍሬው ሀይሉ፣ክፍሉ ሀይሌ፣ ፍቅሬ አየለ፣ተፈራ በለው፣መርአዊ ስጦት፣በጋሻው

“ስንዱ፣የኑሮ ስህተት በተሰኘው ተውኔቷ ስለተወኑት ሴት ተማሪዎች በአድናቆት ስትገልጽ ‹ውህበት ረዳ የምታምር ሴት ልጅ መሆንዋን ማን ጠረጠረ-መምህር አረጋዊን ሁና ስትጫወት። አስቴር አስፋው መልአከሞትን ግርማ ባለው አኳኋን ሰየመች።.. አጸደ ዮሀንስ ልጅ አማረን ሰየመች። ምንም አስቸጋሪ ጨዋታ ቢሆንም በደህና ተወጣችው።› ብላለች”

ተክለማርያም፣ተረፈ መታፈርያ፣መኮንን አበበ፣ሳህሉ አዝነህ፣ክፍሉ ሀይሌና አበራ ደስታ የሚታወሱ ናቸው። እንዳውም ተሰፋዬ ሳህሉ ትያትር የጀመረው በአፈወርቅ አዳፍሬ ነጻነት ተውኔት የአርበኛ ሚስት ሆኖ ነው። በቀጣዮቹ አበይት ሴት ገጸባህርያትን ፣እንደ እናት ኢትዮጵያ፣አፋጀሽኝ፣ እቴጌ ጥሩወርቅ የመሳሰሉት ሲተውን ፣እንደሱው ታደሰ ጌጤ እቴጌ ጥሩወርቅን፣ሀይለ ልኡል ገብረማርያም እቴጌ ተዋበችን ተመስለው ተጫውተዋል። ወንድ ሆነው እንዲያ ያሉትን አበይት ሴት ገጸባህርያት ለረጅም ሰአት ለመጫወት መቻላቸው የሚያስገርም ነው።

ሴት ለመምሰል የሴት አልባሳትንና ጌጣጌጥ ተውሰው፣ ቀሚስ ለብሰው፣ መቀነት አስረው፣ ጺም ያበቀሉት ጺማቸውን ተላጭተው፣ኩል ተኩለው፣በሻሽ ጸጉራቻን ሸፍነው፣ ወይ ገርዳሳ አስረው ነበር የሚተውኑት። ለዚህ መደብ በአብዛኛው የሚመረጡት ልጅነት የነበራቸው ወንዶች ስለነበሩ፣ለተወሰነ ጊዜ የሴት ድምጽን ለማስመሰልና እንደ ዘመኑ ሴት ለመቅለስለስ አይቸገሩም ነበር። ኋላ እየጎረመሱ ሲሄዱ ድምጻቸው እየተፈታተናቸው ወንድ መሆናቸውን ለተደራሲ እያሳበቀ ማህበራዊ ኑሮዋቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ተስፋዬ ሳህሉ ይናገር ነበር። ተስፋዬ፣ በመንገድ ሲሄዱ ሆነ በቁብነገር ማህበራዊ ግንኙነት ወቅት በተጫወታቸው ሴት ገጸባህርያት ስም ‹አፋጀሽኝ! እቴጌ ጥሩወርቅ! እቴጌ ተዋበችን! ..› እየተባል መጠራት ስነልቦናዊ ጫና ፈጥሮበት እንደነበረ በቅሬታ አስታውሷል። በመንገድ ላይ ለመሄድ ነጻነት እያጣም እራሱን በአለባበስ ለመለወጥ ያደርግ የነበረውን ጭንቀት ሲያስታውስ ይበሳጭ ነበር። ምሬቱ የከፋው ግን በአውላቸው ደጀኔ ላይ ነበር። በአራዳ ዘበኛነት ተቀጥሮ እያገለገለ እያለ ወደ ማዘጋጃ ትያትር ክፍል ሲዛወር ደስታ ተሰምቶት ነበር። ወዲያው ሴት ገጸባህርይን እንዲወክል በአለቆቹ በመታዘዙ ከፋው። ክፋቱ የበዛበት በማህበራዊ ህይወቱ ዉስጥ እንደሴት መታየቱ ነበር። ስለሁኔታው በዝርዝር እንዲያስረዳ ሲጠየቅ በብስጭትና በቁጣ ‹ ወጊድ! አታስታውሰኝ፣ መራር ህይወቴን ከዚህ በላይ ላስታውስ አልፈልግም› ብሎ ጠያቂን ባለበት ጥሎ መሄዱ እውነት ነው።

 በዚህ ዘመን በኋላም እስከ 1960ዎቹ መጀመርያ በተቃራኒው ወንድ ተማሪዎች በየጠቅላይ ግዛቱ በተከፈቱ ትምህርት ቤቶችና መለስተኛ ኮሌጆች ሴትን ተመስለው ተውነዋል። ለምሳሌ በ1962 በባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ የጸጋዬ ገብረመድህን የእሾህ አክሊል ውሰጥ፡-

ከመሀል ወደቀኝ ሲል ብርሀነ መዋእ ( የፊልመኛው ዮናስ አባት) ያቀፋት እንጂነር ገበየሁ አያሌው (ኋላ የባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ዲን የሆነው)፣ ወደግራ እንጂነር ዮሀንስ ዮሴፍ ያቀፋት እንጂነር ናይእግዚ ተሰፋ ጽዮን፣ ወደጥግ ኢንጅነር ደርሰህ ልየው)።

በጠቅላይ ግዛት የጎላ እንቅስቃሴ ይታይባቸው ከነበሩት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የጎሬ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ትምህርት ቤት አንዱ ነው። በወላጆች ቀንና በየአውዳመቱ ተማሪዎች እርስ በርስ በመደጋገፍ የታተሙ ተውኔቶችን ይደርኩ ነበር።

ይህ ድራማ በጎሬ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ትምህርት ቤት እስካውት ተቀነባብሮ ለነጻነት በአል ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ የቀረበ ነበር። ከጣሊያኖች መካከል አርበኛው ሲወድቅ በድንጋጤ እራሷን የያዘችን ሴት( ደግሞ የሀዘን ስሜት ማንጸባረቅ ሲገባት ሣቅ ያመለጣትን) በ1960 የተወነው ወንድ ተማሪ ነው። ተወናዩን ያወቀ የአመት ታዛ መጽሄት ይሸለማል።

 በተቃራኒው ደግሞ በእቴጌ መነን የሴት አዳሪ ትምህርት ቤት ከ1934 እስከ 1945 ድረስ ሴቶች የወንድን ገጸባህርይ በሚያስደንቅ ሁኔታ ይተውኑ ነበር- ታሪክ ለዘመኑ በፈጠራት ስንዱ ገብሩ አማካይት። ስንዱ ገብሩ በህጻንነቷ ስዊዘርላንድና ፈረንሳይ ውስጥ ትያትር አይታለች። ከዚያም ተመልሳ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ውስጥ የስነጽሁፍ አስተማሪ ሆና፣ የዮፍታሄን ተውኔት አደራረክ በቅርበት ተከታትላለች። ባለቤቷ በሹመት ሀረርጌ ጠቅላይ ግዛት ሲዛወሩ አብራቸው በመሄዷ፣ ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር ለሽምቅ ውጊያ ከጥቁር አንበሳ አርበኞች ግንባር በመቀላቀሏ፣ በዚሁም ሰበብ ጣሊያን አገር በአዚናራ ደሴት በመታሰርዋ ከተውኔት ክትትሏ ርቃ ነበር። ከነጻነት መልስ በደሴ የስህን ትምርት ቤት ዲሬክተር እንደሆነች ልጃገረዶች እንዲተውኑ ማበረታታት ጀመረች፡ ፡ወደ የአዲስ አበባ ተዛውራ የእቴጌ መነን የሴት  አዳሪ ትምህርት ቤት ምክትል ዲሬክተር እንደሆነች፣ ከአመት በፊት ሴት ተማሪዎቹ በፈረንጅ ዲሬክተር አማካይነት መንፈሳዊ ድራማ አዘጋጅተው  በገና እለት ለንጉሰ ነገስቱና ለቤተሰባቸው በቤተመንግስት ውስጥ እንዳቀረቡ ሰማች። የትምህርት ቤቱ ዋና ዲሬክተር ከሆነች በኋላ ተውኔት መጻፍ ጀምራ ከ1939 አስከ 1947 ድረስ ከሀያ የሚበልጡ ተውኔቶችን በሴት ተማሪዎች አስተውናለች። በትምርት ቤቱ ወንድ ተማሪ ስለማይማር እንደ አጼ ተዎድሮስ፣አጼ ምኒልክና አጼ ሀይለስላሴ ያሉትን አበይት ወንድ ገጸባህርያት ተመስለው የሚጫወቱት ሴቶች ተማሪዎች ነበሩ። በ1939 በግራዚያኒ ጊዜ የየካቲት አደጋ የሚል ተዉኔት ጽፋ ንጉሰ ነገስቱ በተገኙበት በትምህርት ቤቱ ውስጥ አሳየች። ሴቶቹ በቅጥር ግቢያቸው ሳይወሰኑ በርካታ የውጭ ተመልካች በታደመበት በኢትዮጵያ ሲኒማም ውስጥ ተውነዋል። በዚህ ተውኔት ውስጥ ፈለቀች ሀይሌ እንደ አብረሀም ደቦጭ፣ ውህበት ረዳ እንደሞገስ አስገዶም፣ አስካለ ደምሴ እንደ ወንድሜነህ በመተወን ህዝቡን አስገርመዋል።

ስንዱ፣የኑሮ ስህተት በተሰኘው ተውኔቷ ስለተወኑት ሴት ተማሪዎች በአድናቆት ስትገልጽ ‹ውህበት ረዳ የምታምር ሴት ልጅ መሆንዋን ማን ጠረጠረ-መምህር አረጋዊን ሁና ስትጫወት። አስቴር አስፋው መልአከሞትን ግርማ ባለው አኳኋን ሰየመች።.. አጸደ ዮሀንስ ልጅ አማረን ሰየመች። ምንም አስቸጋሪ ጨዋታ ቢሆንም በደህና ተወጣችው።› ብላለች። ሴቶች ሻገር ብለው በ1942 እና 1943 ንጉሰ ነገስቱ በተገኙበት በእንግሊዝኛ መተወናቸው ጉድ አሰኝቶም ነበር። ከዚያም በኋላ ኮከብህ ያውና ያውና ያው ያበራል ገና በተሰኘ ተውኔቷ ሴቶችን አስተውናለች።

በመሀሉ ሴትን በመደበኛ ትያትር የማስተወን ሙከራ ቀጠለ። ይህም ቀደም ሲል በማዘጋጃ ትያትር ማደራጃ ተቀጥራ፣ ትወና ሳይመቻት ቀርቶ ስራዋን በለቀቀችው ዘበናይ ዘለቀ አማካኝነት ነበር። ዘበናይ ስራዋን ከመልቀቁዋ በፊት ሌላ ተተኪ ሴት እንደምታቀርብ ለማዘጋጃ ትያትር ማደራጃ ሀላፊዎች በገባችው ቃል መሰረት የ14 አመት ኮረዳ የሆነችዋንና የበየነ መርእድ ትምህርት ቤት የ4ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችዋን ሰላማዊት ገብረ ስላሴን አባብላ ወደ ትያትር ቤቱ ላከቻት።

 ሰላማዊት ገብረ ስላሴ የተግባር ፈተና እንደተፈተነች ውዲያው ማለፏ ተነገራት። በዚህ መደሰት ሲገባት ከተፈታኞቹ ውስጥ ሴት እሱዋ ብቻ በመሆኗ፣ተገቢ ያልሆነ ነገር ውስጥ እንደገባች ተሰምቷት ለአንድ ወር ያህል ጠፋች። ኋላ ሰዎች እየተላኩ አባብለዋት በ1941 በከፍተኛ ደመወዝ ማለትም በ11 ብር ተቀጠረች። ወዲያው ግን ወደ ትወና አልተሰማራችም። ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸው የጻፉትን ሳልሳዊ ዳዊት የተሰኘ ድራማ በፊልም ለመቅረጽ ታስቦ ስለነበረ ሰላማዊት በፊልም ትወና ስልጠናና ልምምድ ላይ እንድታተኩር ተደርገ። የፊልሙ ምኞት ሳይሳካ ሲቀር ሰላማዊት በብርሀኑ ድንቄ የሳባ ጉዞ ተውኔት ውስጥ ዋና ሴት ገጸባህርይ የሆነችውን ንግስት አዜብን በ1943 በሚያስገርም ሁኔታ ተጫወተች። በዚህም፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ተዋናይ በፕሮፌሽናል ደረጃ በኢትዮጵያ መድረክ ብቅ አለች። ትያትር በአገራችን በተጀመረ በ29 አመት የተጓደለው ተሟላ። ቀጠለችና የሚኒስትር ግርማቸው ተክለሀዋርያትን (ትያትርን ለመጀመርያ ጊዜ በአገራችን ያስተዋወቀው የተክለሀዋርያት ልጅ) ቴዎድሮስ ተውኔት ዋና ገጸባህርይን እቴጌ ጥሩወርቅን በመተወን ለሴት ትወና ጽኑ መሰረት ጣለች። የቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ትያትር እንደተከፈተ ወደዚያው ተዛውራ ከ15 በላይ በሆኑ ተውኔቶችና ፊልሞች ተወነች። ጃንሆይም ሸልመዋት ነበር። አስናቀች ወርቁ በሁለተኛ ሴት ተዋናይነት እንድትከተላትም አርአያ ሆነችላትና፣ እነሆ የመድረክ አንድ ጣጣ በዚህች ታሪካዊ ሴት ልጅ ተወገደ። ይገርማል! ዘመን የራስዋን ባለታሪክ እንዴት እንዴት አድርጋ ነው የምትቀምመው፡፡

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top