አጭር ልብወለድ

ኪነ-ጥበብ እና ኃላፊነት

ጸሐፌ ተውኔት፣ ተርጓሚ እና አዘጋጅ ማንያዘዋል እንዳሻው፤ የብሔራዊ ቴአትር ቤት ዋና ሥራ አስኬያጅ ሆኖ ሲሾም በርካታ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ሞያውን ለመደገፍ፣ የተመልካቹን ስሜት ለመረዳት ቅርብ እንደሆነ መስክረው ነበር። ለአራት ዓመት ያህል ከሰራ በኋላ መቀጠል አልቻለም። እንዳሰበው አልሆነለትም። የሥራ መልቀቂያ በማስገባት ቴአትር ቤቱን ለቆ ወጣ።

ሰሞኑን የቴአትር ቤቱ ዋና ሥራ አስኬያጅ ሆኖ ሲሾም ደግሞ ወደ ኃላፊነቱ ለምን እንደተመለሰ ጠይቀነው ነበር። አሁን ያለው ሁኔታ አበረታች በመሆኑ ሞያውን ለማገዝ ተመልሼያለሁ ብሎናል።

 ማንያዘዋል የተወለደው አዲስ አበባ ነው። እስከ 12ኛ ክፍል በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ተምሯል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቴአትር አርትስ የመጀመሪያው ዲግሪውን አግኝቷል። ወደ ጀርመን ሀገር በመሔድ ከ Humboldt ዩኒቨርሲቲ በቴአትር አርትስ በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቋል። ከእዚያ መልስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ሆኖ ቆይቷል።

ማንያዘዋል ከ20 በላይ ተውኔቶችን የአዘጋጀ ሲሆን ከእነዚህ መካከል በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ከተተረጎሙት የሼክስፒር ሥራዎች “ማክቤዝ”፣ “ሐምሌት” እና “ጁሊየስ ቄሳር”ን እንዲሁም The bear በሚል ርዕስ አንቷን ቼኾቭ ፅፎት፤ መንግሥቱ ለማ የተረጎሙትን “ዳንዴው ጨቡዴ” ን፣ የራሱን “እንግዳ” የተሰኘ ተውኔት እና በተጨማሪም “six characters in search of an Author” የተሰኘ የluigi Pirandello ጽሑፍ በመተርጎም አዘጋጅቷል።

 በቪዲዮ ፊልም “ዴዝዴሞና”፣ “አሸንክታብ”፣ እና “ሰናይት” የተሰኙትም እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከታዩት የ Harold Pinter [ሀሮልድ ፒንተር] ሥራ የሆነውን “the birthday party” “ልደት” በሚል የተተረጎመውንና በጊ.ደ.ሞፓሳ ተደርሶ

“በፊልም ሥራ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ምርጥ የዓመቱ ዳይሬክተር በመባል እንዲሁም በፊልም እና በቴአትር ዝግጅት የworld intellectual property organization (wipo) የፈጠራ ሥራ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል”

በአውግቸው ተረፈ የተተረጎመውን “የአንገት ጌጡ”ን በተጨማሪም ሌሎች ራሱ የፃፋቸው እና የተረጎማቸው ሥራዎች ቀርበውለታል። ከእነዚህ በተጨማሪ በscreen play በኩል “A wingless Bird“ን “ዴዝዴሞናን እና አባትየው” የተሰኙትን ሊያቀርብ ችሏል።

 ማንያዘዋል የጎተ ኢንስቲትዩት ባሳተማቸው መጽሐፎች በቡድንና በግሉ ወደ አማርኛ ከተረጎማቸው በተጨማሪ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር የትርጉም ሥራዎቹን ለንባብ አብቅቷል።

 በፊልም ሥራ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ምርጥ የዓመቱ ዳይሬክተር በመባል እንዲሁም በፊልም እና በቴአትር ዝግጅት የ “world intellectual property organization (wipo)” የፈጠራ ሥራ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

 “አባትየው” በተሰኘው አጭር ፊልሙ ከሰባት የአፍሪካ ሀገሮች መካከል በፊልም ጽሑፍ አፃፃፍ ውድድር አሸንፎ ፊልሙ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ በተለያዩ የቴሌቪዥን ቻናሎች በዓለም ላይ ለዕይታ በቅቷል።

 ባለፈው ዓመት “እንግዳ” የተሰኘው ተውኔት ከተመረጡ የምሥራቅ እና የምዕራብ አፍሪካ ቴአትሮች ስብስብ ውስጥ ተካትቶ “African Theatre six plays from East and west Africa” በሚል በእንግሊዝ ሀገር ታትሞለታል። ጸሐፌ ተውኔት፣ ተርጓሚ እና አዘጋጅ ስለሆነው ማንያዘዋል እንዳሻው ኃላፊነት ያነጋገርናቸው ባለሞያዎች፤

 የብሔራዊ ቴአትር ዋና ሥራ አስኬያጅ መሆኑ በኪነ-ጥበብ በተለይም በተውኔቱ በኩል የተሸሉ ሥራዎች እንዲታዩ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top