በላ ልበልሃ

ከሃምሳ ዓመት በፊት መድረክ እና አዲስ ዓመት

ፀሐፌ ተውኔት እና የዜማ ደራሲ ተስፋዬ አበበ ለረጅም ዓመታት ተውኔቶችን አቅርበዋል።

ለታወቁ ድምፃውያን ግጥም እና ዜማ ደርሰዋል።

1965 ዓም. ጀምሮ ተዋንያንን ለመድረክ በማብቃት እንደ ሲራክ ታደሰ፣ አለሙ /አብ፣ ፋንቱ ማንዶዬ፣ ፍቃዱ /ማርያም፣

ይገረም ደጀኔ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ ትዕግስት ግርማ፣ ሐረገወይን አሰፋ እና ሌሎች ታዋቂ ተዋንያንን በማሰልጠን ይታወቃሉ።

በኪነጥበብ ዘርፍ ለአበረከቱት አስተዋጽኦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር / ማዕርግ አግኝተዋል።

ቅድመዝግጅት፡

አቶ ተስፋዬ አበበ፡ ለአዲስ ዓመት ዝግጅት ገና በግንቦት ወር ይጀምራል። ሁሉም ያሰናዳሉ። በተለይ ወታደራዊ ክፍሎች በነበሩት፤ እንዲሁም በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ብሔራዊ ቴአትር)፣ በሀገር ፍቅር፣ በራስ እና በማዘጋጃ (በአዲስ አበባ ቴአትር እና ባህል አዳራሽ) መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይታይ ነበር። በተለይ በሦስቱ ወታደራዊ ክፍሎች በሥራዎች ላይ ጥንቃቄ ይኖራል።

 ድርሰቶች በታይፕራይተር ይፃፋሉ። ድምፃውያን በጥንቃቄ እና በጥብቅ እንዲይዙ ይነገራቸዋል። ዘፈኖች በቴፕሪከርደር ተቀርፀው ወደ ውጭ እንዳይወጡ ይደረጋል። ጋዜጠኞችም ቢጠይቁ አይሰጣቸውም። አዳዲስ ሥራዎች እንዳይሰረቁ በወታደራዊ ፖሊሶች ይጠበቃሉ። ልምምዱ ከቀን ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ይዘልቃል። ላለመበለጥ ሁሉም ይታገላል። የይድረስ ይድረስ ሥራ አይታሰብም።

 እኔ በረጅም ዓመት በሙዚቃና ድርሰት ዝግጅት ኃላፊ ሆኜ በሠራሁበት በፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ እና ቴአትር ክፍል የነበሩት ስመ-ጥር ድምፃዊያን እነ ሂሩት በቀለ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ሙሉቀን መለሠ፣ ዘሪቱ ጌታሁን፣ አሰገደች ካሣ፣ መስፍን ኃይሌ እና ሌሎችም የተሻሉ ሥራዎችን ይዘው ለመቅረብ ይዘጋጃሉ።

በልምምድ ወቅት ከሚሰሩት ሁሌም አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር የምንሠማው “እንቁጣጣሽ እንኳን መጣሽ” የሚለውን የዘሪቱ ጌታሁን ዘፈን የኔ ነው።

 ድምፃውያን በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ በጉራጊኛ፣ በወላይትኛ በሌሎችም ቋንቋዎች ለማቅረብ ይዘጋጃሉ። ተወዛዋዦችም በተመሳሳይ መልኩ አድካሚ ስልጠና ያካሄዳሉ።

የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች ዜማው ተደርሶ ይሰጣቸዋል። ኖታውን እያነበቡ ያጠናሉ።

በልምምድ ወቅት አንዴ የሆነውን አስታውሳለሁ። ለበዓል ሥራ ዝግጅት ላይ ነን። የምናቀርበው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልደት አዳራሽ ውስጥ ነበር።

 ልምምዳችን ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እየመጡ ያያሉ። አንድ ቀን ጥዋት ላይ አንድ የጦሩ የሙዚቃ ክፍል መሣሪያ ተጫዋች ይመለከቱና ያስጠሩታል። አጠገባቸው ሲደርስ ጫማውን ያሳዩታል። በጭቃ ተበላሽቷል። ሥራውን የሚያቀርብበት መድረክ ምን ያህል ክብር እንዳለው ይነግሩታል። የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቹ ልምምዱ ላይ አልታየም። እንደወጣ አልተመለሰም። ንጉሡ ለጥበብ ትልቅ አክብሮት ነበራቸው።

አለባበስ፡-

 አቶ ተስፋዬ አበበ፡- አዲስ ዓመት ሲመጣ በእንቁጣጣሽ ለሁሉም አዳዲስ ልብሶች ይሰፋሉ። ለተወዛዋዦቹ እና ለድምፃዊያን እንደሚዘጋጁ ሁሉ ለኦኬስትራ አባላቱም ያማረ ሱፍ ሙሉ ልብስ፣ ሸሚዝ እና ከረባት ይገዛላቸዋል። አሁን አሁን የተጨማደዱ ልብሶች አድርገው ሲሰሩ በማየቴ ደንግጫለሁ። ሌላው በየቴአትር ቤቱ የአዲስ ዓመቱን ዝግጅት ለመታደም የሚመጣው ሰው እንደነገሩ ለብሶ እንዲገባ አይፈቀድለትም ነበር። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ይነገረዋል። ወንዶች ሙሉ ልብስ ሴቶች ደግሞ የሀገረሰብ ልብስ ለብሰው መምጣት ይኖርባቸዋል። ይህ ደግሞ ለጥበቡ አክብሮት ሲባል ነው።

 እንቁጣጣሽ እና መድረክ፤

 አቶ ተስፋዬ አበበ፡- የመድረኩ ዝግጅት ልዩ ነው። የቴክኖሎጂ ውጤቱ ያን ያህል ባልነበረበት ዘመን በብርሃን መድረኩ ንጋት

“አዲስ ዓመት ሲመጣ በእንቁጣጣሽ ለሁሉም አዳዲስ ልብሶች ይሰፋሉ። ለተወዛዋዦቹ እና ለድምፃዊያን እንደሚዘጋጁ ሁሉ ለኦኬስትራ አባላቱም ያማረ ሱፍ ሙሉ ልብስ፣ ሸሚዝ እና ከረባት ይገዛላቸዋል። አሁን አሁን የተጨማደዱ ልብሶች አድርገው ሲሰሩ በማየቴ ደንግጫለሁ። ሌላው በየቴአትር ቤቱ የአዲስ ዓመቱን ዝግጅት ለመታደም የሚመጣው ሰው እንደነገሩ ለብሶ እንዲገባ አይፈቀድለትም ነበር”

“የገረመኝ የዛሬ ሦስት ዓመት በአንድ ቴአትር ቤት፤ ከሁለት መቶ በላይ ሙያተኞች በአሉበት አንዱን ድምፃዊ በተለያዩ ቋንቋዎች እንቁጣጣሽ ሲያዘፍኑት አይቻለሁ። ይሄ አሳዝኖኝ ነበር።”

እንዲመስል ይደረጋል። መንጋቱን ለማበሰር የወፎች ጫጫታ በተቀረፀ ድምፅ ይሰማል። ከመድረኩ ግራ እና ቀኝ አበቦች ይቀመጣሉ። አበቦቹ ከውጭ በር ጀምሮ ይጎዘጎዛሉ። መድረኩ ልዩ ውበት ይታይበታል። ዝግጅቱ ጳጉሜ መጨረሻ ላይ መቅረብ ይጀምራል። መስከረም አንድ ይቀጥላል። ሁሉም ያዘጋጀውን የአዲስ ዓመት ዘፈንና ውዝዋዜ በየተራ ያቀርባል። በአንድ ሌሊት በየቴአትሩ ቤት እየዞርን ሦስት ጊዜ እንሰራለን። በእዚህ አያበቃም። በሳምንቱ እሁድ ምሽት በመቀጠልም ለመስቀል እናቀርባለን።የኢትዮጵያ ሬድዮ ኋላ ላይም ቴሌቪዥን ሲገባ የአዲስ ዓመት ዝግጅቶችን በቀጥታ አስተላልፈዋል። የመግቢያ ዋጋ ለአንደኛ ማዕርግ አሥር ብር፣ ለሁለተኛው አምስት ብር ነበር። ትዝ ይለኛል 1954 ዓም. በአዲስ ዓመት ሒሩት በቀለ ዘፈኖቿን አቅርባለች። ከእዚያ በፊት ምድር ጦር ነበር የምትሰራው። ያኔ ገና የፖሊስ ሙዚቃ ክፍል እየተቋቋመ ነው። ወደ እኛ እንድመጣ አነጋገርናት። ፍቃደኛ ሆነች። ይሁን እንጂ እንደማይለቋት ነገረችን። እንደ ተፈላጊ አፍነን ወሰድናት። ኮልፌ ከሚገኘው የፖሊስ መኮንኖች ክበብ አንዱ ክፍል አልጋ ገብቶ እዚያው እንድታርፍ አደረግን።

በእንቁጣጣሽ ቀን በአጃቢዎች ተጠብቃ ሥራዋን አቀረበች። ከዓመታት በኋላ ለሥልጠና የመጡት ኔልሰን ማንዴላ ያረፉት እሷ ተኝታበት ከነበረው ክፍል ነበር። አሁን ጥሩ ጅማሬ አያለሁ። ጥሩ እየሞከሩይመስለኛል። የገረመኝ የዛሬ ሦስት ዓመት በአንድ ቴአትር ቤት፤ ከሁለት መቶ በላይ ሙያተኞች በአሉበት አንዱን ድምፃዊ በተለያዩ ቋንቋዎች እንቁጣጣሽ ሲያዘፍኑት አይቻለሁ። ይሄ አሳዝኖኝ ነበር።

የአዲስ ዓመት ምኞት

 አቶ ተስፋዬ አበበ፡- ለውጤት የምንበቃበት አንድነታችንን የምናፀናበት እንደመሆኑ ሁለት ሺህ አሥራ አንድ የዕድገት፣ የብልፅግናና የአንድነት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ። ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት መስክ ይህችን ሀገር ማልማት አለበት። ከእራሱ በፊት የሀገርን ክብርን ማስቀደም ይኖርበታል። ለሀገሩ ማሰብ ይጠበቅበታል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top