አድባራተ ጥበብ

የሙዚቃችን ነገር

በተለያዩ ጊዚያት በሚዘጋጁት መድረኮች ድምፃውያን ለአድማጮች የሚያደርሱት ነጠላ ዜማ ይሁን አልበም መነጋገሪያ ሆነው ቆይተዋል። አብዛኞቹ የዘፈን ግጥሞች እንደነገሩ የተፃፉ መሆናቸውን፤ ዜማዎቻቸው ቶሎ ተደምጠው እንደሚጠፉ ይነገራል። በቅርቡ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አዘጋጅነት በሙዚቃ ባለሙያው አብርሃም ወልዴ አቅራቢነት “ሙዚቃና ማህበራዊ ፋይዳው” በሚል ርዕስ

“በሀገራችን እንደ ጽሑፍ፣ እንደ ሥዕሉ ሁሉበሙዚቃውም በተለይ በዜማ በኩል ጥንታዊነቱቢነገርም፤ በየዘመኑ፣ በየሥርዓቱ የነበሩ እና አሁንምያሉ ባለሞያዎች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ማንሳትቢችሉም፤ ማሻሻል እና ማሳደጉ ላይ እምብዛምእንዳልተሰራ ተሳታፊዎቹ ጠቁመዋል።”

የተካሔደው ውይይት የግጥም እና ዜማ ዝግጅቶች፤ በባለሙያዎች እይታ ጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ምን እንደነበሩ የሚያተኩር ነበር።

 ዛሬም ብዙዎቹ ያልተደከመባቸው፤ የባለ ሞያ እጆች ያላረፈባቸው ግጥሞች እና ዜማዎች እንደሚደመጡ እንዲሁም በጥንቃቄ መሠረት እንዳለባቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡

አልፎ አልፎ በወጉ ለአድማጭ የሚደርሱ ነጠላ ዜማዎች እና አልበሞች የመኖራቸውን ያህል፤ ተደጋግመው የሚሰሙ ሳይሰለቹ ለተወሰኑ ጊዚያት የሚቆዩ ዜማዎች መታጣታቸው ተነግሯል።

 ምንም እንኳን አሁን ያለበት ደረጃ አሳሳቢ እንደሆነና በአዲስ መልክ ሞያው ላይ መሠራት እንዳለበት ቢጠቆምም ይህ በየዘመኑ ያለ እና ጠንክረው የሰሩ ሲቀጥሉ ደካማዎቹ እንደሚቀሩ ባለሞያዎች ሀሳብ ሰጥተዋል።

 በሀገራችን እንደ ጽሑፍ፣ እንደ ሥዕሉ ሁሉ በሙዚቃውም በተለይ በዜማ በኩል ጥንታዊነቱ ቢነገርም፤ በየዘመኑ፣ በየሥርዓቱ የነበሩ እና አሁንም ያሉ ባለሞያዎች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ማንሳት ቢችሉም፤ ማሻሻል እና ማሳደጉ ላይ እምብዛም እንዳልተሰራ ተሳታፊዎቹ ጠቁመዋል።

 ሞያውን በተመለከተ ለማበረታታት እና ለማሻሻል በተወሰኑ ጊዚያት መሥፈርት አውጥተው የሚሸልሙ ድርጅቶች አነስተኛ መሆናቸው፣ ተጨማሪ የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች ያለመኖራቸው፣ ተከታታይ የውይይት መድረኮች ያለመዘጋጀታቸው ከሌሎች ሞያዎች ጋር ያላቸው ቀረቤታና ዝምድና በወጉ ያለመፈተሹ፣ በተደጋጋሚ ለሚነሡ ተመሳሳይ ችግሮች ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ባለሞያዎች ነግረውናል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top