ጥበብ በታሪክ ገፅ

የባሌው ሸኽ ሁሴንና እስላማዊው ባህል

አንድ – ባሌ  የታሪክ ጸሐፊዎች ‹‹ባሌ›› የሚለው ቃል በታሪክ ከነበረው የባሌ የሙስሊም መንግስት የተወሰደ የሙስሊሞች መንግስትና የአካባቢ መጠሪያ እንደሆነ ጽፈዋል። ባሌ በአገራችን የደቡቡ ክፍል የሚገኝ አካባቢ ሲሆን ሱልጣኔቱም የዛሬዎቹን ጎባ፣ ሲናና ዲንሹ፣ አጋርፋ፣ ጋሴራና ጎሮን ያካተተ እንደነበር ይታመናል። በዘመኑ የባሌ መንግስት ወይም ሱልጣኔ መናገሻም ‹‹ዙላህ›› እንደነበረች ይታመናል። የባሌው መንፈሳዊ መሪ፣ የሸኽ ሁሴን ታሪክ ከዚሁ መንግስት ታሪክ ጋር አብሮ ይተረካል።

ሁለት – ሸኽ ሁሴን ባሌና እስልምና

 Braukamper (1970) እንደዘገበው፣ ሸኽ ሁሴን በደቡብ ኢትዮጵያ የኖሩትና መታወቅ የጀመሩት ከዛሬ ስምንት መቶ አመት በፊት ጀምሮ ነው። ሸኽ ሁሴን ሙሉ ስማቸው ‹‹ሁሴን ኢብራሂም አብደላህ›› ይባላል። በዚያን ዘመን ሸኽ አብደላህ ሶማሌዎችና አረቦች በሚኖሩባት ‹‹መርካ›› በምትባል የሱማሊያ ዳርቻ እስልምናን በማስተማር ይኖሩ ነበር። ልጃቸው ሸኽ ኢብራሂምም የአባታቸውን ፈለግ በመከተል እስልምናን ለማስተማር ወደ ሰሜን ምስራቅ ባሌ ደረሱ። ሸኽ ኢብራሂም በዚሁ በባሌ ልዩ ስሙ አናጂና በተባለ ቦታ ሰፈሩና የአካባቢው ተወላጅ የሆነች ሴት አግብተው ሙሐመድ፣ ሱለይማንና ሁሴን የተባሉ ሶስት ልጆች ወለዱ። ሸኽ ሁሴንም በፈንታቸው ኑረላህ አህመድ፣ ሙሐመድ  ተማም፣ ሱለይማንና አብደላህ የተባሉ አራት ወንድ ልጆችና ፋጢማ የተባለች ሴት ልጅ እንደመለዱ ይታመናል። ከሸኽ ኢብራሂም ሶስት ልጆች ሸኽ ሁሴን ጊዜና ዘመን ተሸግረው በልዩ ልዩ ሁኔታ እስካሁን ይታወሳሉ።

 ስለ ሸኽ ሁሴን ቀጣይ የዘር ትውልድ እስካሁን የተጻፈ መረጃ የለም። የሸኽ ሁሴን ዘር ነን የሚሉ ሰዎች ግን በመላው ኢትዮጵያ እንደሚገኙ ይታመናል። ይሁንና የዘር ሀረጋቸውን በመቁጠር በእርግጥ የሸኹ ትውልዶች ስለመሆናቸው የሚያረጋግጡ መኖራቸውን የጻፈ አላነበብኩም። እነዚህ የሸኽ ሁሴን ዘሮች ነን የሚሉ ወገኖች በሁለት መንገድ ተለይተው ይታወቃሉ። አንደኛው በድህነት የሚኖሩና በየቦታው እየተቀመጡ ድቤ በመምታት የሚለምኑ ናቸው። ‹‹ገሪባ›› በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ሁለተኛው መገለጫቸው ‹‹Y›› የመሰለ ዘንግ ከጃቸው የማይለይ መሆኑ ነው።

ሸኽ ሁሴን የእስልምና እውቀት ችሎታ ብቻ ሳይሆን የቃድሪያ ሱፊ ተከታይ ወልይ ወይም ጻድቅ እንደነበሩ፣ በዚህ ‹‹ኑር ሁሴን/ብርሃናማው ሁሴን›› የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸው ይታመናል። እንደ ሱፊ ወልይነታቸው ባለ ከራማና በዚሁ ከራማቸው ለአማኞቻቸው በረከት ለጋሽ እንደነበሩ ይታመናል።

 ይህ የእስልምና እውቀታቸውና ወልይነታቸው መንታ ባህሪ፣ በአንድ በኩል ከቀደምቱም ሆነ በሳቸው ጊዜ ከነበሩ ዑለማዎች በተሻለ ለመታወቅ፣ ሃይማኖቱን ለማስተማርና ተተኪ ሰባኪዎች ለመፍጠር አስችላቸው እንደነበር ይተረካል። በሌላ በኩል በወልይነታቸው በሚፈጽሟቸው ተአምራቶችና ለአማኞቻቸው በሚያስገኟቸው በረከቶች በዘመናቸው በነበሩ ዑለማዎች ዘንድ ተቃውሞ ይነሳባቸው እንደነበር ከቃል ተረኮቻቸው መረዳት ይቻላል። ያም ሆነ ይህ ሸኽ ሁሴን ሌላ ጊዜ ሸኽ ኑር ሁሴን እየተባሉ ካለፉት ስምንት መቶ አመታት ጀምሮ በከበራና በቃል ታሪክ ዘመን፣ ጊዜና ቦታ ተሸግረው የሚታወሱ መንፈሳዊ ሰብእና የተላበሱ ሰው ለመሆን በቅተዋል። ለስምንት መቶ አመት እየታወሱ፣ እየተዘከሩ ኖረዋል።

  በጠቃላይ በሱፊ ወልዮች ባህሪ እንደሚታየው ሸኽ ሁሴንም በማስተማር ጥበባቸው፣ ባላንጣዎቻቸውን በማሸነፍ ከራማቸው፣ የአማኞቻቸውን የእለት ህይወት በመታደግ በረከታቸው፣ ወዘተ አንጻር እንደሚከተለው ይነበባሉ።

ተረክ አንድ – የከራማ ተረክ

 በአናጂና አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ዑለሞች፣ በሸኽ ሁሴን የትምህርት አሰጣጥና ከራማ ቅሬታና ተቃውሞ ነበራቸው ይባላል። ከእለታት ባንዱ ቀን እነዚህ ሸኾች መንገድ ላይ ከሸኽ ሁሴን ጋር ይገናኙና ክርክር ይገጥማሉ። በክርክር ላይ እንዳሉም በንፋስ የታጀበ ሃይለኛ ዝናብ መጣል ይጀምራል። ሳያባራ ይመሻል። ምሽቱም እየጨለመ ይሄዳል። ዝናቡም እየባሰ፣ ምሽቱም ድቅድቅ ጨለማ እየሆነ ይመጣል። በዚህን ጊዜ የሸኽ ሁሴን ተቃዋሚዎች በዝናቡና በጨለማው ውስጥ ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተቸግረው ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ።

 የዑለሞችን ጭንቀት የተረዱት ሸኽ ሁሴን ‹‹እናንተ ካንተ በላይ እናውቃለን የምትሉ  ዑለሞች ሆይ! እስቲ ከዚህ ጨለማና ዝናብ ወጥተን ወደ ቤታችን መሄድ እንዲንችል መላ ፍጠሩ›› ይሏቸዋል። የሸኽ ሁሴን ተቃዋሚ የሆኑ ዑለሞችም ሸኽ ሁሴንን ‹‹እርስዎ ከቻሉ ከዚህ ጉድ ያውጡን›› ይሏቸዋል። ሸኽ ሁሴንም ከተቃዋሚ ዑለሞች ተገልለው ሶላት ከሰገዱና ዱኣ ካደረጉ በኋላ የግራና የቀኝ ትከሻቸውን መታ መታ ሲያደርጉት በትከሻቸው ላይ ልዩ የሆነ ብርሃን ይፈልቃል። ዝናቡም ይቆማል። ሸኽ ሁሴንም ከትከሻቸው በፈለቀው ብርሃን ጥቅጥቁን ጨመላ እየገለጡ ተቃዋሚዎቻቸውን ወደ ቤቶቻቸው አስገቧቸው ይባላል። ይህ የሸኽ ሁሴን የከራማ ዝርው ተረክ በሚከተለው የቃል ዜማ እየተዜመ ይገኛል። (ዜማው በኦሮምኛ ቋንቋ የቀረበ በመሆኑ በትክክል የተጻፈ ስላልመሰለኝ ለተፈጠረው ስህተት አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃሉ።)

 መቃ በሌሱፍ ኪተኒ ዱከንቲ ጀበናን

 ጨኩ ኢሳፊ ኢብሲ ኑሪ ነቢ ኬኛን።

ትርጉሙ

ስሙን ልታጠፉ ተነስታችሁ ጨለማው ቢነግስ፣

 በትከሻው ላይ አበራው ነቢ የኛ ኑር።

ተረክ ሁለት – የበረከት ከራማ ተረክ

ሸኽ ሁሴን በከራማቸው የተቸገሩ ይረዱ እንደነበሩ ይታመናል። በዚህም የተለየ ብቃታቸው የተቸገረውና የተጨነቀው ከችግሩና ከጭንቁ እንዲገላገል፣ የታመመው እንዲሽር፣ ያጣው እንዲያገኝ፣ ቀሪ ህይወቱ እንዲሰምርለት ወዘተ በሸኽ ሁሴን ይማለዱ ነበር ይባል። ይህ ብቃታቸው በሚከተለው የቃል ታሪካቸው በዝርው ይተረካል፣ በዜማም ይዜማል።

 በአንድ ወቅት በአናጂና የምትኖር አንዲት እርጉዝ ሴት ምጧ ይጠናባታል። ለሰባት ቀን ያህል ዘመድ አዝማድ ተሰብስቦ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተው አብረዋት እየተሰቃዩ መውለዷን እየጠበቁ ይከርማሉ። በመጨረሻ ዘመድ አዝማዱ ሁሉ ተስፋ ቆርጠውና ተሰላችተው ‹‹ተስፋ የላትም›› ብለው ጥለዋት ይተኛሉ። በምጥ የምትሰቃዬው ሴትም ብቻዋን ጭንቅ ውስጥ ትገባለች። በዚሁ ጭንቅ መሀል ሸኽ ሁሴንን ታስታውሳለች። ‹‹ሸኽ ሁሴን የእውነት እርስዎ የአላህ ወልይ ከሆኑ ከዚህ ጭንቅ አውጡኝ›› በማለት የሸኽ ሁሴንን ስም ደጋግማ እየጠራች ትማጸናለች። በዚሁ ጸሎቷ ውስጥ እንዳለችም በሰላም ከምጧ ትገላገላለች።

 ተረክ ሶስት – ጠላትን የመከላከል ከራማ ተረክ

 ሸኽ ሁሴን ለሌሎች ብቻ ሳይሆን በሳቸው ላይ የሚነሳን ጠላት የመከላከል ልቅና እንደነበራቸው ይታመናል። በአንድ ወቅት በሳቸው ላይ የተነሱ ሽፍቶችን የተከላከሉበት የከራማ ተረክ የሚከተለውን ይመስላል።     

“ይህች ሴት ሸኽ ሁሴን ዛፍ ስር ተቀምጠው ሲጸልዩ አይታቸው ኖሮ ‹‹እዚያ ናቸው›› ስትል በጣቷ በመጠቆም ታሳያቸዋለች። ሽፍቶቹም ሸኽ ሁሴን ወደተቀመጡበት ዛፍ ሲንደረደሩ በያሉበት ከነፈረስና መሳሪያቸው ይንጋይ ይሆናሉ። ሴትዮዋም በጀርባዋ እንስራ እንዳዘለችና እጇን እንደዘረጋች በቆመችበት ደርቃ ትቀራለች”

በአንድ ወቅት ባሌ ውስጥ ሽፍትነት ይነግሳል። እነዚህ ሽፍቶች የድሃውን ንብርት በመዝረፍ፣ ነፍስ በማጥፋት አካባቢውን ያስመርራሉ። በዚህን ጊዜ ሸኽ ሁሴን የሽፍቶቹን አሰቃቂ ድርጊት በመቃወም እነዚህን ሽፍቶች ፈጣሪ እንዲያጠፋላቸው ሌት ተቀን ሶላትና ዱኣ ማድረግ ይጀምራሉ። ይህ የሸኽ ሁሴን ድርጊት ሽፍቶቹ ጆሮ ይደርሳል። ሃይላቸውን አሰባስበው ሸኽ ሁሴንን ማደን ይጀምራሉ። ሸኹ ብዙውን ጊዜ ያዘወትሩበት የነበረውን የአይነጌን ዋሻ አካባቢም ያስሳሉ። ሽፍቶቹ በዚሁ ቦታ ሲዘዋወሩ መንገድ ላይ አንዲት ውሃ ቀድታ የምትመለስ ሴት ያገኙና ሸኽ ሁሴን የት እንደሚገኙ ይጠይቋታል። ይህች ሴት ሸኽ ሁሴን ዛፍ ስር ተቀምጠው ሲጸልዩ አይታቸው ኖሮ ‹‹እዚያ ናቸው›› ስትል በጣቷ በመጠቆም ታሳያቸዋለች። ሽፍቶቹም ሸኽ ሁሴን ወደተቀመጡበት ዛፍ ሲንደረደሩ በያሉበት ከነፈረስና መሳሪያቸው ይንጋይ ይሆናሉ። ሴትዮዋም በጀርባዋ እንስራ እንዳዘለችና እጇን እንደዘረጋች በቆመችበት ደርቃ ትቀራለች።

 ሸካሆ ሸኽ ሁሴን አቲ ነቢ ዱጋ

 ነመከስ ህንቡለኔ አካ ዱጋ ጉጋ

 ትርጉሙ

 ሸካችን ሸኽ ሁሴን አንተ እውነተኛው ነህ

 ላንተ ያልተገዛ ሰው እንደ ዲንጋይ ይደርቃል።

 ሸኽ ሁሴን ሃይማኖታቸውን የማስተማር፣ ተቃዋሚያቸውን የመርታት ልዩ ጥበብ ነበራቸው ተብሎ ይታመናል። በአንድ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም በቀጥታና ፊት ለፊት ከመናገር ይልቅ ለተጠየቅ ወይም ሎጂክ ቅድሚያ ይሰጡ እንደነበር የቃል ታሪኮቻቸው ተረኮች ይገልጻሉ። ለዚህ ጥበባቸው የሚከተሉትን የቃል ተረኮች እንመልከት።

 ተረክ አራት – የማስተማር ጥበብ

 ሸኽ ሁሴን ከማስተማር የተረፈ ጊዜያቸውን አዘውትረው ዱኣ/ጸሎት በማድረግና በሶላት/ በስግደት ያሳልፉ፤ ሌሎችም የእርሳቸውን አርኣያ እንዲከተሉ ያዙ ነበር ይባላል።

ከእለታት በአንድ ቀን፣ በዚህ ድርጊታቸውና ትእዛዛቸው ግራ የገባው ደረሳ /ተማሪ/ ‹‹ሸኽ ሁሴን እርስዎ ለምን ብዙ ጊዜ ሶላትና ዱኣ ያበዛሉ? እኛንም ሶላትና ዱኣ እንዲናበዛ ያዙናል?›› ሲል ይጠይቃቸዋል። ሸኽ ሁሴንም ለጥያቄው መልስ ከመስጠታቸው በፊት በጣታቸው ወደ አንድ ዛፍ ያመለክታሉ። ዛፉ ወደ አንድ አቅጣጫ ያዘመመ ነበር። ‹‹ዛፉን ታየዋለህ? ዛፉ ቢቀረጥ ወደ የት የሚወድቅ ይመስልሃል?›› ሲሉ ይጠይቁታል።

 መልስን አልጠብቁም ‹‹ዛፉ የሚወድቀው ወደ አዘመመበት በኩል ይሆናል። እንግዲህ አንተም ከኃጢአትና ከወንጀል እርቀህ፣ በሶላትና በዱኣ ከአላህ ጋር ተቃርበህ ብትሞት ነፍስህ ለጀነት የመሆን እድሏ የሰፋ ይሆንልሃል›› ሲሉ ሶላትንና የዱኣን ጥቅም አስተማሩት ይባላል።

Cerulli (1971) ‹‹እስልምና ትላንትና ዛሬ›› በተባለው መጽሀፉ ውስጥ ሸኽ ሁሴን ጅብሪል በህይወት በነበሩበት ዘመን የነበሩ ዑለማዎች በጫትና በጠጅ ላይ የተለየ አቋም ነበራቸው። ዑለሞቹ ጫት መቃምና ጠጅ መጠጣት ክልክል አይደለም ብለው ያምኑ ነበር። ሸኽ ሁሴን ደግሞ ጫት መቃምም ሆነ ጠጅ መጠጣት ክልክል ነው የሚል አቋም ነበራቸው። በዚህ የተነሳ ከሸኽ ሁሴን ከባሌ ዑለሞች ጋር ውዝግብ ይገቡ፣ ክርክር ይገጥሙ፣ ተከራክረውም ይረቱ ነበር ይባላል። ይህ አቋማቸውና ተከራክሮ የመርታት ጥበባቸው በሚከተለው ቃል ታሪክ ይታወሳሉ።

ተረክ አምስት – ሸኽ ሁሴንና የጠጅ መጠጥ

ሸኽ ሁሴን ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ሲያስተምሩ በአካባቢው የሚኖሩ ዑለማዎች የሸኹን መምጣት ይሰማሉ። እነዚህ ሸኮች ጠጅ ከማር ስለሚሰራ ሙስሊሞች ቢጠጡት ይበቃል የሚል እምነት ነበራቸው። እናም ሸኽ ሁሴንን በዚህ ጉዳይ ያላቸውን አቋም ለማወቅ ሲሉ ሸኹ የሰፈሩበት ቦታ ይሄዳሉ። ሸኽ ሁሴንም ዑለማዎቹን ለምን እንደፈለጓቸው ይጠይቋቸዋል።

  ‹‹እርስዎ ስለ ጠጅ ያለወትን አመለካከት ለማወቅ ነው››

 የእናንተስ አመለካከት እንዴት ነው›› ሲሉ ይጠይቃሉ።

 ‹‹እኛማ ጠጅ ሀላል ነው፤ ወይን ደግሞ ሀራም ነው እንላለን››

 ‹‹ወይን ለምንድን ነው ሃራም የሆነው?››  ‹‹አእምሮን ስለሚረብሽ››

 ‹‹ጠጅስ አእምሮን የሚረብሽ ቢሆን ምን ልትሉት ነው?››

 ‹‹ጠጅ አእምሮን የሚረብሽ ቢሆንም ሃላል ነው እንላለን››።

 የዑለሞቹን መልስ ከሰሙ በኋላ ‹‹አላህ ሆይ

“በአናጂና በእነዚህ ሁለት የከበራ ወቅቶች ከመላው ኢትዮጵያ፣ ከኬኒያ፣ ከሱማሊያ፣ ከኢራቅ ወዘተ የሚመጡ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ አማኞች ይታደሙበታል። የከበራው ተሳታፊዎች በእምነት፣ በዘር፣ በቋንቋ፣ በእድሜ፣ በጾታ፣ በሙያ፣ በማእረግ ወዘተ የተወሰኑ አይደሉም። ለሁሉም አይነት የህብረሰተብ አይነት ክፍት ነው።”

በእኔና በእነዚህ ዑለሞች መካከል የሚፈርድ ሰው ላክልን›› ሲሉ ዱኣ ያደርጋሉ። በዚሁ መካከል አንድት በጀርባዋ ልጅ ያዘለች ሴት ወደ እነሱ አቅጣጫ ትመጣለች። አጠገባቸው እንደደረሰች ‹‹አሰላሙአለይኩም/ ሰላም ለሁላችሁም ይሁን›› ስትል ሰላምታ ታቀርባለች። ሁሉም ‹‹ወአለይኩሙሰላም/ ሰላም ላንቺም ይሁን›› ሲሉ ይመልሳሉ። ሴትዮዋ በመቀጠል ‹‹በጀርባየ ስላዘልኩት ልጅ ጉዳይ መላ እንዲትሰጡኝ ነበር አመጣጤ›› ትላለች። ‹‹ምን ሆነ›› ይሏታል።

  ‹‹በአንድ ወቅት ልጄ ጠጅ ጠጥቶና እራሱን ስቶ ይመጣል። አብሬው እንዲተኛ ይታገለኛል። እኔኮ እናትህ ነኝ ብለውም ሊሰማኝ አልቻለም። በሃይል አስገድዶ ደፈረኝና አረገዝኩ። ይህን በጀርባየ ያዘልኩትንም ልጅ ወለድኩ። አሁን ምን ባደርግ ይሻለኛል፣ መላ ስጡኝ›› በማለት ገጠመኟን ተረከችላቸው።

 ወደ ዑለማዎቹ ዞረው ‹‹ይህ እውነት ከሰማችሁ በኋላ አሁንስ ስለ ጠጅ ያላቸው አመለካከት እንዴት ነው›› ሲሉ ጠየቋቸው። ዑለሞቹም የግዳቸውን ጠጅ ክልክል እንደሆነ አመኑ።

 ተረክ ስድስት – ሸኽ ሁሴንና ጫት መቃም

 ዑለማዎቹ ከሸኹ ጋር ለክርክር ሲቀርቡ የሚቻላቸውን ያህል ተዘጋጅተው፣ በዚህም ሊረቷቸው ተማምነው ነበር።   

መጠጥ ሀራም እንደሆነ፣ መጠጥ የሚጠጣም ሰው እንደሚጠሉ፣ አባካኝም እንደሚሉት ሰማን። ጫትን በሚመለከት ከነችግሮቹ ሲያወግዙ አልተሰሙም። መጠጥ ሀራም ከሆነ ጫትም ሀራም መሆን ነበረበት። ለምን ቢሉ፣ ጫት ጀነት/ገነት የማያስገቡ አራት ባህሪያት አሉት። አንደኛው ጫት የምግብ ፍላጎት ይዘጋል። እራስን በምግብ መቅጣት ለእሳት ይዳርጋል። ሁለተኛው የጫት ባህሪ ሰውን ብቸኛ ያደርጋል። ሰውን መጥላት ደግሞ ኃጢአት ነው። ሶስተኛው የጫት ባህሪ እንቅልፍ ማሳጣቱ ነው። በጫት ሰበብ እንቅልፍ ማጣት እንደ ኃጢአት ይቆጠራል። አራተኛው የጫት ባህሪ የወሲብ ፍላጎት ማሳጣቱ ነው። ይኸም ከኃጢያት ነው።

መጠጥን በሚመለከት ግን ከጫት የተለየ ለጀነት የሚያበቁ አራት ጠቀሜታዎች ነው። አንደኛ መጠጥ የምግብ ፍላጎት አይዘጋም። ምግብ መመገብ ደግሞ የሚወደድ ነው። ሁለተኛ መጠጥ ሰውን ቸር ያደርጋል። ለጋስነት ደግሞ ከሚወደዱት ነው። ሶስተኛ መጠጥ ደስተኛና ተጫዋች ያደርጋል። ይኸ ደግሞ የጀነት ሰዎች ባህሪ ነው። አራተኛ መጠጥ የወሲብ ስሜትን ያነቃቃል። ይህም የሚወደድ ነገር ነው። መጠት እነዚህ ሁሉ መልካም ባህሪዎች እያሉት ከጫት በተቃራኒ ተመድቦ እንዴት ሀራም ሊሆን ይችላል?

ሸኽ ሁሴን በዑለሞቹ የቀረቡ የክርክር ነጥቦችን ከሰሙ በኋላ

 ሸኽ ሁሴን፡- እናንተ ዑለሞች ሆይ! ከልብ ሆናችሁ አዳምጡኝ። ከእናንተ መካከል ነብዩ የጀነት መሆናቸውን የሚጠራጠር አለን?  በአንድ ድምጽ የለም አሉ።

  ነብዩ አዘውትረው ይስቁ ነበርን?  

አይስቁም ነበር።  

ነብዩ አብዝተው ይበሉ ነበርን?

 አይበሉም ነበር።

 ነብዩ ወሬ ያበዙ ነበርን?

  አያበዙም ነበር።

  ነብዩ ወሲብ የተጠመዱ ነበርን?

  አልነበሩም።

  እንግዲህ ጫት የሚቅም ሰው ባህሪ ለነብዩ ባህሪ የቀረበ ነውን? ወይስ መጠጥ ለሚጠጣ ሰው ባህሪ? ሲሉ በአመንክዮ ያፋጥጧቸዋል። ዑለሞቹም የሸኹ መልስ ይገባቸውና ‹‹ያሉት እውነት ነው›› አሏቸው ይባላል።

ሶስት – አናጂና የሸኽ ሁሴን ማእከል

በ Braukamper (1970) ዘገባ መሰረት ‹‹አናጂና›› ሸኽ ሁሴን የተወለዱበትና የሞቱበት ቦታ እንደሆነ ይታመናል። አናጂና ‹‹ድሬ ሸኽ ሁሴን›› እየተባለም ይጠራል። አናጂና የሸኽ ሁሴን የእስልምና ማሰራጫና ማስፋፊያ ማእከላቸውም እንደነበር ይታመናል። ከዚያም አልፎ በሱፊ ልማድ መሰረት አናጂና የዚያራና የህዝባዊ ማእከል ሆኖ ይገኛል።

 ሸኽ ሁሴን አናጂና በህይወት በነበሩበት ጊዜ መስጊድ ነበራቸው። ያን ዘመን የሚገልጽና በሳቸው ጊዜ የተመሰረተ ነው የተባለ መስጊድ አሁንም አለ። በሱፊ ማእከሎች እንደሚደረገው ሁሉ ሸኹ በመስጊዱ የሃይማኖት ማስተማሪያና ማሰልጠኛ እንዲሁም የሃድራ መቀመጫ አድርገውታል። በስልጠናው እነ ሶፍ ዑመር ይጠቀሳሉ። በሃድራው የተራውን ህዝብ ከየአቅጣቻው የሚመጣውን ህዝብ እስልምናን ለማስተዋወቅ፣ በተረኮቻቸው እንደተገለጸው በዱኣቸው በረከት ለማስገኘት ተጠቅመውበታል።

 ሸኽ ሁሴን ከዚህ አለም ከተለዩ በኋላ እሳቸውን የተካ ባለ ከራማ ስለመኖሩ እስካሁን የታወቀ ነር የለም። ነገር ግን በሳቸው ስም በባሌ በአናጂና፣ በአሩሲ በደበል ኑርና በሰኪና፣ በሀረርጌ በመተጉዲሳ በየአመቱ የዚያራና የህዝባዊ ከበራዎች ይፈጸማሉ።

 በአናጂና የዚያራና የህዝባዊ ከበራው በአመት ሁለት ጊዜ ይካሄዳል። አንደኛው የዚያራ ጊዜ ሸኽ ኑር ሁሴን ተወለዱ የተባሉበት ቀንና ወር ሲሆን፣ ወሩ ነሀሴ፣ ቀኑ የወሩ መጀመሪያ ማክሰኞ ነው። የከበራው ስምም ‹‹ኢጃ ሸኽ ሁሴን/የሸኽ ሁሴን አይን›› እየተባለ ይጠራል። ሁለተኛው የዚያራ ጊዜ ‹‹ኢደል አክበር/ ታላቁ ክብረ በአል›› በሚል ስያሜ ይጠራል። ይህ ክብረ በአል ከእስልምና ማእዘናት አንዱ ከሆነው የአረፋ መንፈሳዊ ጉዞ ወቅት የሚካሄድ ነው። በዚህ የተነሳ ክብረ በአሉ ከእስልምና የጨረቃ አቆጣጠር ጋር ወርና ቀኑ ይለዋወጣል። (ይህ ‹‹ኢደል አክበር/ ታላቁ ክብረ በአል›› ሁለት ገጽታና አንድምታ ያለው ነው። አንደኛው ወደ መካ ሄደው ሐጅ ለመፈጸም አቅም ያልነበራቸው ሙስሊሞች እንደ ማካካሻ እንዲፈጽሙት ተደርገዋል የሚል ነው። ሁለተኛው ሙስሊሞች በአንድ በኩል ሀጅ እንዳያደርጉ ለመከላከል፣ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ሙስሊሞች የማይኖሩባት ‹‹የክርስቲያን ደሴትነቷን›› ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም ሙስሊሞች በሐጅ ሰበብ ወደ መካ ሄደው ስለ ሃይማኖታቸው የነበራቸውን እውቀት እንዳያበለጽጉ በአናጂና ታጥረው እንዲቀሩ የተደረገ ፖለቲካዊ ሴራ ነው የሚል ነው።)

በአናጂና በእነዚህ ሁለት የከበራ ወቅቶች ከመላው ኢትዮጵያ፣ ከኬኒያ፣ ከሱማሊያ፣ ከኢራቅ ወዘተ የሚመጡ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ አማኞች ይታደሙበታል። የከበራው

“‹‹ዛፉን ታየዋለህ? ዛፉ ቢቀረጥ ወደ የት የሚወድቅ ይመስልሃል?›› ሲሉ ይጠይቁታል። መልስን አልጠብቁም ‹‹ዛፉ የሚወድቀው ወደ አዘመመበት በኩል ይሆናል። እንግዲህ አንተም ከኃጢአትና ከወንጀል እርቀህ፣ በሶላትና በዱኣ ከአላህ ጋር ተቃርበህ ብትሞት ነፍስህ ለጀነት የመሆን እድሏ የሰፋ ይሆንልሃል›› ”

ተሳታፊዎች በእምነት፣ በዘር፣ በቋንቋ፣ በእድሜ፣ በጾታ፣ በሙያ፣ በማእረግ ወዘተ የተወሰኑ አይደሉም። ለሁሉም አይነት የህብረሰተብ አይነት ክፍት ነው።

 በእነዚህ ከበራዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በርካታ ልማዳዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ድርጊቶች ይፈጸማሉ። ወደ ሸኽ ሁሴን የመቃብር ቦታ ለዚያራ የሚመጡ ሁሉ፣ ሸኹ በአይን ባይታዩም በመንፈሳቸው የሚያዩ፣ የሚሰሙና ለችግር የሚደርሱ ናቸው ብለው ያምናሉ። ከዚህ በረከታቸው ለመካፈል ሲሉ ስለት ይሳላሉ፣ ስለት ያገባሉ። እንደ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዶሮ ወዘተ የመሳሰሉ እንስሳት እያረዱ ድሃ ያበላሉ። ገንዘብ፣ ጨርቅና ሌሎች ቁሶች ለድሃ ያከፋፍላሉ። ሁሉም በያሉበት ቡድን ፈጥረው ጫት እየቃሙ በሚሰጠው ወይም በሰጠው እምነት ላይ ነው። ተቃዋሚዎቹ ሸኽ ሁሴን የእስልምና አስተማሪና መንፈሳዊ መሪ እንጂ እርሳቸው ተመላኪ ወይም በረከት ሰጪ አልነበሩም የሚል ነው። ሁለተኛው ተቃውሞ ከላይ በተረኮቹ እንደተገለጸው፣ ሸኽ ሁሴን ጫትን የመሳሰሉ (በሳይንስም የተረጋገጡ) አስካሪና አደንዛዥ እጾች አጥብቀውና ከልክለው ሳለ በአሁኑ ወቅት የእነዚህ በሸኹ የተከለከሉ ድርጊቶች የሚፈጸሙ መሆናቸው ነው። ሶስተኛ ለሸኽ ሁሴን የተሰጠው እምነትም ሆነ በከበራ ማእከሎቹ የሚፈጸሙ ልዩ ልዩ ድርጊቶች ከሌሎች እምነቶች የተወረሱ ወይም የተቀዱ እንጂ የእስልምና ባህል መገለጫዎች አይደሉም የሚል ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top