ጣዕሞት

ከ ጠ/ሚኒስትር አቢይ አንደበት

“ፓሪስን ከመጎብኜቴ በፊት ፓሪስን በንባብ ያስተዋወቀኝን ሰው ከደጅ አገኘሁት። በእናንተ መካከል ሆኖ ሃሳብ መሰንዘር ቀላል አይደለም። ብዕርና እስክርቢቶ እንድናገናኝ ያበረታታችሁን፣ ከማንበብ ውስጥ ጥበብ፣ እውቀት እንደሚፈልቅ መንገድ ያሳያችሁን ታላላቅ ሰዎች እዚህ ውስጥ አላችሁ።”

 “ የሰው ልጅ ተፈጥሮን ማንበብ ከመጀመሩ በፊት ከሌሎች የዱር እንስሳት የማይለይ፣ በተናጠል የሚኖር፣ የማህበር ኑሮ የሶሻል ኑሮ የማያውቅ፣ ጥቃት በየቀኑ የሚያጋጥመው፣ ከአደጋም የተነሳ ቁጥሩ ያልበረከተ ሕዝብ ነበር። የሰው ልጅ ተፈጥሮን አንብቦ እሳት ከፈጠረ በኋላ እሳቱን ለመሞቅ በጋራ ከመሰብሰብ ነው ቋንቋ የተፈጠረው።”

 “ ሰው እየበዛ ሲሄድ በንግግር ሃሳብ መጋራት ብቻውን በቂ ስላልሆነ ነው በሥዕል፣ በቅርፅ ኋላም በፊደል ሃሳብን ከሽኖ በጽሑፍ ማቆየት፣ ለትውልድ ማሸጋገር አስፈላጊ የሆነው። ሰው ተፈጥሮን ማንበብ ካልቻለ፣ ንባቡን ማጋራት ካልቻለ፣ ሕይወት መቀጠል አይቻለውም።”

 “ ታዋቂው ደራሲ ማክሲም ጎርኪ በንግግሩ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ጎልቶ የሚወጣው ‘ጥበብና ሳይንስ ሕይወትን ለማንበብ ተዋህደው የሚገኙበት አንድ ስፍራ ቢኖር እሱ መጽሐፍ ነው’ ይላል።”

“ መጽሐፍ ብርቱ፣ እጅጉኑ አድማጭ የሆነ በምክንያት መከራከር የሚችል ጓደኛ ነው። ከእውነተኛው ከሰው ጓደኛ የሚለየው ከተከራከረ በኋላ የማያማና የማያማርር መሆኑ ብቻ ነው።”

 “ብዙ ጊዜ በችግር፣ በመከራ ወቅት እንድንሸጋገር በብዙው የረዱን መጻሕፍት የእናንተ የሥራ ውጤቶች ናቸውና እውቀት ብቻ ሳይሆን ጥበብ ብቻ ሳይሆን በጓደኛነትም ብዙዎቻችን ልንላመዳቸው የሚገቡ በጣም ጠቃሚ ሃብቶች ናቸው።”

“ የማንበብ ባህል በገጠር ውስጥ የቄስ ትምህርት ቤት፣ መድረሳ ትምህርት ቤት እየተባለ ልጆች እየተማሩ እያነበቡ፣ ስለደራሲያን እያወጉ፣ እየጓጉም እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል። በአሁኑ ጊዜ እውቀት ደርጅቶ የሚቀርብበት መጽሐፍ አንባቢ እያገኘ ስላልሆነ በከፍተኛ ደረጃ የሃብት እጦት ብቻ ሳይሆን የጭንቅላት ድርቀትም እያጋጠመን ነው።”

 “ ተፈጥሮ አድሎ የሰጠንን አገር ተገንዝበን ተጠቅመን ልንለወጥ ያልቻልንበት ዋነኛው ምስጢር ጥበብን የመፈለግ፣ እውቀትን የመፈለግ ዝንባሌያችን ፍራንክ ከመለቃቀም ጋር ሲነፃፀር እጅግ የተለያየ በመሆኑ ነው።”

 “ ደራሲያን በሰላ ብዕራችሁ ትውልድ ማስተማር፣ የሚያቁ ግን የማያውቁ ሰዎች ካሉ እነሱን መሞገት፣ የናንተ ትልቅ ሃላፊነት መስሎ ይሰማኛል።”

 “ በእናንተ ጥበብ ውስጥ ፖለቲካ ሊዳሰስ ይገባዋል፤ ሃይማኖት ሊዳሰስ ይገባዋል፤ ግብረገብነት ሊዳሰስ ይገባዋል፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ትውልድ ለማዳንና ይህቺን ሃገር የማስቀጠል ሃላፊነት ከማንም በላይ በሚጽፉ፣ ከምንም በላይ ደግሞ በጥሩ ማየት ማስተዋል፣

“መጽሐፍ ብርቱ፣ እጅጉኑ አድማጭ የሆነ በምክንያት መከራከር የሚችል ጓደኛ ነው። ከእውነተኛው ከሰው ጓደኛ የሚለየው ከተከራከረ በኋላ የማያማና የማያማርር መሆኑ ብቻ ነው።”   ጥበብን ማየት በሚችሉ ሰዎች ሃላፊነት የወደቀ መሆኑን እንድትገነዘቡ በአንክሮ ማሳሰብ እፈልጋለሁ።”

 “ ኢትዮጵያ ውሰጥ ወጣቶች ለማንበብ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት የሳሳበት አንድ ምክንያት ብራንዲንግ ነው። ጽሑፍ ለመጻፍ ደራሲያን ፣ ሃሳብ አፍላቂዎች ፣ የፈለቀን ሃሳብ ከወረቀት ጋር የሚያዋህዱ ፣ ድርሰት ሆኖ ከወጣ በኋላ የሚያሳትሙ ፣ የሚያከፋፍሉ መልሰውም የሚያነቡ አሉ። ይሄ ሰንሰለት ነው። ከዚህ ውስጥ አንዱ ሲበጠስ ጠቅላላ ኢንዱስትሪው ይወድቃል።”

 “ ጸሐፊዎች አንዱ ራሳችሁን ማክበሪያ መንገድ ጸሐፍትን ማክበር ነው። የመጣውን ጽሑፍ ምክንያታዊ ሆኖ ማየስ የሙያ ግዴታ ነው። መጻፉን በራሱ እያደነቅን መሆን አለበት። … መጻፍ የሚደነቅ ነገር፣ ማንበብ የሚያስወድስ ነገር መሆኑን እየተናገርን፣ እዚያ ውስጥ ደግሞ የሚታዩ ስህተቶች ካሉ ነቅሶ ማውጣትና ማረም ተገቢ ይሆናል።”

 “ መጽሐፍ ብሔርን ከብሔር የሚያገናኝ፣ ባህልን ከባህል የሚያስተሳስር ድልድይ ነው፣ መጽሐፍ ሰውና ሰው እንዲከባበር እንዲዋደድ የሚያደርግ ትልቅ ሃብት ነው።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚኒስትርነታቸው ወቅት  በሁለተኛው “የንባብ ለህይወት” የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ላይ ካደረጉት ንግግ 

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top